አልኮሆል ያለአግባብ መጠቀም እና ጥገኛ መሆን በህይወትዎ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል።
አልኮሆልን ያለአግባብ መጠቀም ማለት አልኮልን ከመጠን ያለፈ ወይም በብዛት መጠቀም ሲሆን፤ የአልኮሆል ጥገኛነት ለተወሰነ ጊዜ አልኮሆልን ያለማቋረጥ ሲጠቀሙ እና በዚህ ምክንያት ሰውነትዎ ሲለወጥ የሚፈጠር ነው፡፡
የአልኮሆል ጥገኛ ከሆኑ ካልጠጡ ሊታመሙ ወይም የተለየ ስሜት ሊሰማዎት ስለሚችል አልኮሆል መጠጣትን ማቆም ከባድ ይሆንብዎታል።
አዘውትረው አልኮሆል በብዛት የሚጠጡ ሰዎች የአልኮሆል አጠቃቀም መታወክ ተብሎ የሚጠራውን ሊያዳብሩ ይችላሉ።
አልኮሆል ያለግባብ መጠቀም እና ጥገኝነት:-
ከመጠን በላይ መጠጣት ወደ ሱስ ሊያመራ ይችላል፤ በመደበኛነት ለመስራት አልኮሆል እንደሚያስፈልጎ ሊሰማዎት ይችላል፤ ጠዋት ላይ ከስራዎ በፊት፣ በቀን ወይም ምሽት ከስራ ወደ ቤት እንደገቡ አልኮሆል እንዲጠጡ የሚያስገድድ ስሜት ሊሰማዎት ይችላል።
የአልኮሆል አሉታዊ ተጽዕኖ:-
ደካማ የስራ አፈጻጸም፣ ሥራ ማጣት፣ የገንዘብ ችግሮች፣ የመኪና አደጋ ተጋላጭነት፣ ከጓደኞች እና ቤተሰብ ጋር ያለ ግንኙነት ላይ ችግሮች መከሰት፣ ስራ ባልደረቦች፣ ጓደኞች እና ቤተሰብ አመኔታ እና ክብር ማጣት ይጠቀሳል።
እንዲሁም ለረጅም ጊዜ መጠጣት ሰውነትዎን እና አዕምሮዎን በዘለቄታዊነት ይጎዳል፤ እንዲሁም የዕድሜ ልክ የጤና ችግሮችን ያስከትላል እነዚህም በጉበትዎ ወይም በቆሽትዎ ላይ የሚደርስ ጉዳት፣ የልብ ችግር፣ የደም ግፊት ወይም የስትሮክ ችግር፣ የካንሰር ህመም፣ ኢንፌክሽኖችን የመከላከል አቅም መቀነስ ናቸው፡፡
በተጨማሪም የአንጎል ወይም የነርቭ ጉዳት፣ የመንፈስ ጭንቀትና ያለጊዜ ሞት ያስከትላል፡፡
አልኮሆልን ያለግባብ መጠቀም መንስኤዎች:-
የአልኮሆል መጠጥ ያለአግባብ የመጠቀም የቤተሰብ ታሪክ ያለው፤ የመንፈስ ጭንቀት ወይም ሌሎች የአዕምሮ ጤና ሁኔታዎች መኖር፣ ገና በልጅነት መጠጣት መጀመር፣ ብዙ ጊዜ ከመጠን በላይ መጠጣት፣ በልጅነት ጊዜ የስሜት ቀውስ፣ ጭንቀት እና ያልተረጋጋ የቤተሰብ ህይወት ማጋጠምና ብዙ ጊዜ ከሚጠጡ ሰዎች ጋር ጊዜ ማሳለፍ ናቸው።
የአልኮሆል ጥገኝነት ችግር እንዳለብዎ ካሰቡ መጠጣት ለማቆም መወሰን፡-
አልኮሆልን በተደጋጋሚ መጠጣት ከተለማመዱ ይህን ማድረግ በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡
መጠጣትን የመተው ምልክቶች መታየት ከጀመሩ ከጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ወይም ከምያምኑት ሰው ጋር መነጋገር አስፈላጊ መሆኑን ከዘውዲቱ ሆስቲታል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
እነዚህ ምልክቶች ጭንቀት፣ መንቀጥቀጥ፣ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽ፣ ላብ ወይም መተኛት አለመቻልን ሊያካትቱ ይችላሉ።
አልኮሆል ያለአግባብ መጠቀም ለማቆም በማህበራዊ ስብሰባዎች እና አልኮሆል ባለባቸው ቦታዎች አልኮሆል ያልሆኑ መጠጦችን ለመጠጣት ይምረጡ፤ በትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባሉ አልኮሆልን በማያካትቱ በሚወዷቸው እንቅስቃሴዎች ላይ ብዙ ጊዜ ያሳልፉ፡፡
ኢትዮጵያ ከሰው ኃይል ልማት በመጀመር የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለማልማት የጀመረችውን ጥረት እንደሚደግፍ የቻይና የኒውክሌር ኃይል ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሊጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በቤጂንግ የሚገኘውን የኒውክሌር ምርመር እና ሪአክተር ማዕከል እንዲሁም የቻይና የኒውክሌር ኃይል ባለስልጣንን ጎብኝተዋል፡፡
ከጉብኝታቸው በኋላም ከባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሊዩ ጂንግ ጋር ከዚህ በፊት በሁለቱ ሀገራት መካከል የኒውክሌር ኃይልን ለሰላማዊ ዓላማ ለማዋል የተደረጉ ስምምነቶች መሰረት በተለይም ከሰው ሀብት ልማት አኳያ በትብብር መሥራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ቻይና የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ጥቅም በማዋል ረገድ ከደረሰችበት የዕድገት ደረጃ ላይ ኢትዮጵያ መድረስ እንደምትፈልግ ያስረዱት ሚኒስትሩ÷ እስከ አሁንም በዘርፉ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን ለማሰልጠን እያደረገች ላለው ድጋፍ በማመስገን ትብብሯ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በኒውክሌር ትምህርት እና ምርምር ዘርፍ ከቻይና ዩኒቨርሲቲዎች እና ተቋማት ጋር በትብብር የሚሠሩበትን ዐውድ ለማስፋት በሚቻልበት አግባብ ላይም መክረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የኒውክሌር ኃይል ኤጀንሲ (አይ ኤ ኢ ኤ) ጋር በቅርበት እየሠራች መሆኗን በመግለጽ ከተቋሙ ጋር በኢትዮጵያ የአፍሪካ የስልጠና ማዕከል ለመገንባት ኢትዮጵያ ለኤጀንሲው ያቀረበችውን ጥያቄ ባለስልጣኑ እንዲደገፍ ጠይቀዋል።
ሊዩ ጂንግ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ከሰው ኃይል ልማት በመጀመር የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለማልማት የጀመረችውን ጥረት እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል፡፡
በመስከረም ወር በፎካክ በሚደረገው ስብሰባ በአፍሪካ ኅብረት፣ በዓለም አቀፉ የኒውክሌር ተቋም እና ቻይና መካከል በአፍሪካ የስልጠና ተቋም ለማቋቋም የሦስትዮሽ ስምምነት እንደሚኖር ጠቁመዋል፡፡
በስምምነቱ መሰረትም ለአፍሪካ ኅብረት እና ኢትዮጵያ ድጋፍ እንደሚደረግ ጠቅሰው÷ ይህ የባለብዙ ወገን ስምምነት እንዳለ ሆኖ በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከልም በጋራ ሊሠሯቸው በሚፈልጓቸው ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ስምምነት መደረግ እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል።
የሲቪል ሰርቫንት ደመወዝ ማሻሻያ በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች የተሰራጨው መረጃ ሃሰተኛና ምንም ዓይነት የመነሻ መሰረት የሌለው መሆኑን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትእንደገለጹት ÷የመንግስት ሰራተኞችን የደመወዝ ስኬል በተመለከተ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተናፈሱ የሚገኙ መረጃዎች ሃሰተኛ ናቸው፡፡
ማንኛውም ማሻሻያ ወይም የደመወዝ ስኬል ለውጥ ካለ ሕጋዊ ሰውነት ባላቸው እና በሚመለከታቸው አካላት ይፋ እንደሚደረግ አስገንዝበዋል፡፡
ውሳኔዎቹ ሲኖሩም በዝርዝር ጥናቶች እና የበጀት አጸዳደቅ ሥርዓትን ተከትለው የሚካሄዱ መሆኑን ማጤን ጠቃሚ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ታማኝ እና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት ሁልጊዜም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ማጣራት እና ማገናዘብ ከስህተት እንደሚታደግም አንስተዋል፡፡
በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚሰራጩ መረጃዎች አንዳንድ ጊዜ እውነታዎችን ሊያዛቡ ይችላሉ ያሉት ኮሚሽነሩ ÷ ይህም ግራ መጋባትን ከማስከተሉ ባለፈ ያልተፈለገ እንድምታ ሊያስከትል ይችላል ብለዋል።
በአሁኑ ጊዜ እየተናፈሱ የሚገኙት አሉባልታዎች እውነተኛ የመረጃ መሠረት እንደሌላቸው ገልጸው ÷ መሰል የሚሊየኖችን ሕይወት የሚነካ ሃሰተኛ መረጃ ማሰራጨት ተገቢነት እንደሌለውም ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ መሸጡን አስታውቋል፡፡
ባንኩ ዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም የተካሄደውን የልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ አድርጓል።
በዚህም ዛሬ በልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድን የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ መሸጡን አስታውቋል፡፡
በጨረታው 27 የንግድ ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን÷ የዛሬው አማካይ ዋጋም የነገ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጠቋሚ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ እንደሆነ መገለጹን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ÷ ተግባራዊ የተደረገው የባንክ ምንዛሪ ዋጋ ከትይዩ የገበያ ዋጋ ጋር ያለው ልዩነት መቀራረቡን የሚያሳይ ተጨባጭ ውጤት መገኘቱ አስደሳች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
Part 1
“Maktub” means “It is written.” The Arabs feel that “It is written” is not really a good translation, because, although everything is already written, God is compassionate, and wrote it all down just to help us. The wanderer is in New York . He has overslept an appointment, and when he leaves his hotel, he finds that his car has been towed by the police. He arrives late for his appointment, the luncheon lasts longer than necessary, and he is thinking about the fine he will have to pay. It will cost a fortune. Suddenly, he remembers the dollar bill he found in the street the day before. He sees some kind of weird relationship between the dollar bill and what happened to him that morning. “Who knows, perhaps I found that money before the person who was supposed to find it had the chance? Maybe I removed that dollar bill from the path of someone who really needed it. Who knows but what I interfered with what was written?” He feels the need to rid himself of the dollar bill, and at that moment sees a beggar sitting on the sidewalk. He quickly hands him the bill, and feels that he has restored a kind of equilibrium to things. “Just a minute,” says the beggar. “I'm not looking for a handout. I'm a poet, and I want to read you a poem in return.” “Well, make it a short one, because I'm in a hurry,” says the wanderer. The beggar says, “If you are still living, it's because you have not yet arrived at the place you should be.” Think of the lizard. It spends most of its life on the ground, envying the birds and indignant at its fate and its shape. “I am the most disliked of all the creatures,” it thinks. “Ugly, repulsive, and condemned to crawl along the ground.” One day, though, Mother Nature asks the lizard to make a cocoon. The lizard is startled -it has never made a cocoon before. He thinks that he is building his tomb, and prepares to die. Although unhappy with the life he has led up until then, he complains to God: “Just when I finally became accustomed to things, Lord, you take away what little I have.” In desperation, he locks himself into the cocoon and awaits the end. Some days later, he finds that he has been transformed into a beautiful butterfly. He is able to fly to the sky, and he is greatly admired. He is surprised at the meaning of life and at God's designs. A stranger sought out the Father Superior at the monastery of Sceta. “I want to make my life better,” he said. “But I cannot keep myself from having sinful thoughts.” The father noticed that the wind was blowing briskly outside, and said to the stranger: “It's quite hot in here. I wonder if you could seize a bit of that wind outside and bring it here to cool the room.” “That's impossible,” the stranger said. “It is also impossible to keep yourself from thinking of things that offend God,” answered the monk. “But, if you know how to say no to temptation, they will cause you no harm.” The master says: “If a decision needs to be made, it is better to make it and deal with the consequences. You cannot know beforehand what those consequences will be. The arts of divination were developed in order to counsel people, never to predict the future. They provide good advice, but poor prophecy. “In one of the prayers that Jesus taught us, it says, 'God's will be done. ' When His will causes a problem, it also presents a solution. If the arts of divination were able to predict the future, every soothsayer would be wealthy, married and content.” The disciple approached his master: “For years I have been seeking illumination,” he said. “I feel that I am close to achieving it.
Paulo Coelho
Dedicated to Nha Chica
የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን ለመቋቋም የሚደረጉ ዓለም አቀፍ ጥረቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ሚናዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል ተመላከተ፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የአረንጓዴ ዕድገት ኢንስቲትዩት፣ ከግብርና ሚኒስቴር እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፥ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብሩ የሀገሪቱን የደን ሽፋን በ2011 ዓ.ም ከነበረበት 17 ነጥብ 2 በመቶ ዘንድሮ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ከፍ አሳድጎታል ብለዋል፡፡
አረንጓዴ ዐሻራ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ስለሆነ አጠናክሮ ለማስቀጠል ይሠራል ማታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
መርሐ-ግብሩ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአካባቢው የውኃ አካላት መጎልበት ዘርፈ ብዙ ሚና እንዳለው ገልጸው÷ በአረንጓዴ ዐሻራ ዙሪያ ያላትን ልምድ ለጎረቤት ሀገራት በማካፈል ሚናዋን እየተወጣች ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚደረጉ ጥረቶች ላይ ሚናዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
የዓለም አቀፉ አረንጓዴ ዕድገት ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ቢሮ ዳይሬክተር ኦኬቹኩ ዳንኤል ኦግቦናያ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ ላይ እያከናወነች ያለው ተግባር ምሳሌ እንደሚሆን ጠቅሰዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን የሚቋቋም የግብርና ስርዓትን ለመገንባት በኢትዮጵያ የተጀመሩ ስራዎች አበረታች ውጤት እየተመዘገበባቸው መሆኑንም ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ ጋር በአረንጓዴ ልማት የጀመረውን የትብብር ስራ እንደሚያስቀጥልም ጠቁመዋል።
የከርሰ ምድርና ገፀ ምድር ውሃን በተገቢው ሁኔታ ለመጠበቅና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል ችግኞችን በየጊዜው መትከል ይገባል ሲሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች በጋምቤላ ክልል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርና ለተማሪዎች የትምህር ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ግድቦች በደለል እንዳይሞሉና የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር ውሃን በተገቢው መንገድ ለመጠበቅ የደን ሀብቶችን ማሳደግና ችግኞችን መተከል ይገባል።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ሚኒስትር ዴኤታ አብርሃ አዱኛ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ችግኝ መትከልና መንከባከብን ለትውልድ በማሻገር ከብክለት የፀዳች ሀገርን ማስረከብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ተጠሪ ተቋማቱ በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ላፕቶፕ ያበረከቱላቸው ሲሆን÷ የኢኮኖሚ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች ደግሞ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
በተጨማሪም የወንዞች ሙላትና የጎርፍ አደጋ ሲከሰት መጓጓዝ የሚያስችል የሞተር ጀልባ ለክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አስረክበዋል፡፡
በፈረንሳይ አስተናጋጅነት የተካሄደው 33ኛው የፓሪሱ ኦሊምፒክ 31 አዳዲስ ክብረ ወሰኖች ሲመዘገቡበት በርካታ አይረሴ ድራማዊ ክስተቶችንም አስተናግዶ አልፏል፡፡
የደቡብ ኮሪያ አትሌቶች በመድረኩ የሰሜን ኮሪያ ተብለው መጠራታቸው እንዲሁም በደቡብ ሱዳን ብሄራዊ መዝሙር ምትክ የሱዳን ብሄራዊ መዝሙር መለቀቁ ኦሎምፒኩን አነጋጋሪ አድርገውት ቆይተዋል፡፡
በበርካታ ውድድሮች ከሁለት ሳምንት በላይ በፓሪስ ሲካሄድ በቆየው የኦሊምፒኩ ጨዋታዎች አሜሪካ በ126 ሜዳሊያዎች ለ7ኛ ጊዜ ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ ቻይና በ91 እንዲሁም ጃፓን በ45 ሜዳሊያዎች ተከታዩን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል፡፡
በውድድሩ በአጠቃላይ 31 አዳዲስ ክብረ ወሰኖች የተመዘገቡ ሲሆን ይህም 22 ክብረወሰኖች ከተመዘገቡበት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ጋር ሲነፃፀር የዘጠኝ ብልጫ አለው፡፡
አትሌቲክስ፣ ተራራ መውጣት፣ የውሃ ቀዘፋ፣ የብስክሌት ውድድር፣ ሞደርን ፔንታሎን (ኢላማ)፣ ውሃ ዋና እና ክብደት ማንሳት በኦሊምፒኩ ክብረ ወሰን የተመዘገበባቸው የስፖርት ዘርፎች ናቸው፡፡
አሜሪካዊቷ ሲድኒ ማክላፊን 4 በ400 የዱላ ቅብብል፣ ስዊድናዊው አርማንድ ዱፕላንት በምርኩዝ ዝላይ፣ ፈረንሳዊው ዋናተኛ ሊዮን ማርቻንድ ክብረ ወሰን ያስመዘገቡ ወጣት አትሌቶች ናቸው፡፡
በተጨማሪም አርሻድ ናዲም ከፓኪስታን በጦር ውርወራ፣ ሮክ ስቶና ከጃማይካ በዲስክ ውርወራ፣ በሴቶች 400 ሜትር ማሪየልዲ ፖሊኖ ከዶሚኒካን ሪፐብሊክ፣ በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ሩጫ ኮል ሆከር ከአሜሪካ፣ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ዊንፈሬድ ያቪ ከባህሬን የኦሊምፒክ ክብረ ወሰንን በማሻሻል ስማቸውን በመዝገብ ላይ አስፍረዋል።
በማራቶን በሁለቱም ጾታ የኦሊምፒኩ ክብረ ወሰን የተሻሻለ ሲሆን በወንዶች ለኢትዮጵያ ብቸኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ያመጣው አትሌት ታምራት ቶላ 2:06:26 በሆነ ሰዓት በመግባት ክብረ ወሰኑን አሻሽሏል።
በሴቶች ደግሞ ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሰን 2:22:55 በመግባት የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን ያሻሻለች ሲሆን፤ ኡጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቴፕቴጌይ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር የኦሊምፒኩን ክብረ ወሰን ማሻሻል ችለዋል።