Entertailment Page

Entertailment






👁 :
ላሊበላ
Catagory: History
Auter:
Posted Date:07/29/2024
Posted By:utopia online

ላሊበላ በኢትዮጵያ፣ በአማራ ክልል በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሀገር የምትገኝ ከተማ ነች። በ12.04° ሰ 39.04° ምዕ ላይ የምትገኘው የላሊበላ ከተማ ከባሕር ጠለል በላይ 2,500 ሜትር ከፍታ ያላት ስትኾን የሕዝቡም ብዛት ወደ 11,152 ነው። 1 ላሊበላ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ከተማዎች መካከል ከአክሱም ቀጥላ በኹለተኛነት ደረጃ የምትገኝ ከተማ ስትኾን፣ ለአብዛኞቹ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንደ ዋና የእምነት ማእከል በመኾን ታገለግላለች። የላሊበላ ነዋሪዎች በአብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ናቸው። የላሊበላን ከተማ በዋነኛነት ታዋቂ ያረጉዋት ከክ.ል. በኋላ በ13ኛው መቶ ክፍለዘመን እንደ ተሰሩ የሚነገርላቸው 11 አብያተ-ክርስቲያናት ናቸው። በኢትዮጵያ ትውፊት መሰረት እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት በንጉሥ ላሊበላ ዘመን በቅዱሳን መላዕክት እረዳትነት እንደተሰሩ የሚታመን ሲኾን ግርሃም ሃንኮክ የተባለው እንግሊዛዊ ጸሓፊ ግን እኤአ በ1993 ዓ.ም ባሳተመውና The Sign and the Seal በተባለው መጽሃፉ አብያተ-ክርስቲያናቱን በማነፁ ሥራ ላይ ቴምፕላርስ የሚባሉት የመስቀል ጦረኞች ተካፍለዋል ሲል አትቷል ነገር ግን ማረጋገጫ አልነበረውም። እነዚሀ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ አርባ ትንንሽ ቤተ ክርስቲያኖች አሉ። ንጉሡ ላሊበላ የሚለውን ስም ያገኘው፣ ሲወለድ በንቦች ስለተከበበ ነው ይባላል። ላል ማለት ማር ማለት ሲኾን፤ ላሊበላ ማለትም -ላል ይበላል (ማር ይበላል) ማለት አንደሆነ ይነግራል። ውቅር ቤተ ክርስቲያናቱን ንጉሡ ጠርቦ የስራቸው ከመላእክት እገዛ ጋር እንደሆነ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ይነግራል። በ16ኛው ከፍለ ዘመን አውሮፓዊ ተጓዥ ላሊበላን ተመልክቶ «ያየሁትን ብናግር ማንም እንደኔ ካላየ በፍጹም አያምነኝም» ሲል ተናግሮ ነበር። በላሊበላ 11 ውቅር ዐብያተ ክርስቲያናት ያሉ ሲኾን ከነዚህም ውስጥ ቤተ ጊዮርጊስ (ባለ መስቀል ቅርፁ) ሲታይ ውሃልኩን የጠበቀ ይመስላል። ቤተ መድሃኔ ዓለም የተባለው ደግሞ ከሁሉም ትልቁ ነው። ላሊበላ (ዳግማዊ ኢየሩሳሌም) የገና በዓል ታህሳስ 29 በልዩ ኹኔታ ና ድምቀት ይከበራል፣ "ቤዛ ኩሉ" ተብሎ የሚጠራው በነግህ የሚደረገው ዝማሬ በዚሁ በዓል የሚታይ ልዩ ና ታላቅ ትዕይንት ነው።የሚደረገውም ከቅዳሴ በኋላ በቤተ ማርያም ሲኾን ከታች ባለ ነጭ ካባ ካህናት ከላይ ደግሞ ባለጥቁር ካብ ካህናት በቅዱስ ያሬድ ዜማ ቤዛ ኩሉ እያሉ ይዘምራሉ። 11ዱ የቅዱስ ላሊበላ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት 1.ቤተ መድኀኔ ዓለም፣ 2.ቤተ ማርያም፣ 3. ቤተ ደናግል፣ 4.ቤተ መስቀል፣ 5. ቤተ ደብረሲና፣ 6.ቤተ ጎለጎታ፣ 7.ቤተ አማኑኤል፣ 8.ቤተ አባ ሊባኖስ፣ 9.ቤተ መርቆሬዎስ፣ 10. ቤተ ገብርኤል ወሩፋኤል፣ 11. ቤተ ጊዮርጊስ


Type:Social
👁 :
Second Annual Symposium on Accelerating Science, Technology, and Circular Innovation in Southeast Asia: Smart Cities Innovation, Biotechnology, and Circularity
Catagory:Education
Auter:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

The U.S. Department of State hosted the second annual Symposium on Accelerating Science, Technology, and Circular Innovation in Southeast Asia: Smart Cities Innovation, Biotechnology, and Circularity in Vientiane, Lao People’s Democratic Republic (Lao PDR) on July 17-19. The U.S.-ASEAN Smart Cities Partnership (USASCP), Arizona State University (ASU)-implemented U.S-ASEAN Science, Technology, Innovation and Cooperation Program (STIC), and Rochester Institute of Technology (RIT) jointly developed this event, which underscored the importance of education and training, circular economy and innovation, and climate resilience to the region. The event convened public, academic, and private sector actors across multiple disciplines. Throughout the Symposium, discussions highlighted programs across multiple sectors, including Water Smart Engagements (WiSE), which pairs water utilities from U.S. and Southeast Asian cities to improve water security in ASEAN cities through sustainable water management solutions. The Symposium showcased WiSE partnerships in the Mekong sub-region, demonstrating the outcomes of the city partnerships and success in the program’s final year. These partnerships exemplify U.S. cooperation on water and natural resources management under the Mekong-U.S. Partnership (MUSP). USASCP also announced its intent to launch the Smart Cities Business Innovation Fund 2.0, capitalized at $3 million, to catalyze net zero urban innovation and sustainable business practices. ASU hosted the U.S.-ASEAN STIC business venture pitch competition and research project presentations, which culminated in the disbursement of $100,000 in awards supporting proposals that advance technology innovations across ASEAN member states. Several research proposals spotlighted biotechnology, reflecting its crucial role in advancing scientific knowledge and addressing contemporary challenges in the ASEAN region. The Circular Entrepreneurship program, a flagship initiative of RIT, expanded its training partnerships across the entire ASEAN region and presented its material flow analysis research as well as its ongoing work to better understand the role of the informal sector in the ASEAN e-waste life cycle. This integrated event with public and private sector partners demonstrated the U.S. commitment to advancing science, innovation, and resiliency across ASEAN


Type:Technology
👁 :
Science, Technology, and Innovation
Catagory:Education
Auter:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

Science, technology, and innovation are cornerstones of the American economy. They are also dominant forces in modern society and international economic development. Strengthening these areas can foster open, transparent, and meritocratic systems of governance throughout the world. The Department of State executes public diplomacy programs that promote the value of science to the general public. It also implements capacity-building programs in emerging markets that train young men and women to become science and technology entrepreneurs, strengthening innovation ecosystems globally. The Department’s efforts contribute to scientific enterprises that hasten economic growth and advance U.S. foreign policy priorities. Read more about what specific bureaus are doing to support this policy issue Office of Science and Technology Cooperation (STC): STC, part of the Bureau of Oceans and International Environmental and Scientific Affairs (OES), cultivates science, technology, and innovation (STI) ecosystems to support U.S. foreign and economic policy priorities. It leverages a wide variety of tools and foreign partnerships to strengthen STI around the world Office of the Science and Technology Adviser to the Secretary of State (STAS): STAS provides a focal point for the integration of science, technology, and innovation into U.S. foreign policy. It anticipates the foreign policy impacts of STI research and development and the effects of discoveries emerging from the high-technology and private sectors. It is a central bridge between the Department and the U.S. and global STI communities.Office of Space Affairs (SA): SA carries out diplomatic and public diplomacy efforts to strengthen American leadership in space exploration, applications, and commercialization by increasing understanding of, and support for, U.S. national space policies and programs and to encourage the foreign use of U.S. space capabilities, systems, and services


Type:Technology
👁 :
Automatic Test Equipment and Why They are Widely Used?
Catagory:Education
Auter:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

The need to offer high-quality standard while improving functionalities has pushed manufacturers toward automatic test equipment (ATE) that are reliable and guarantees repeatability. ATEs aid manufacturers to perform several accurate tests and reducing the incidence of failures and errors, offering test results faster than the conventional manual testing methodology. For the years to come, the global automatic test equipment market is expected to boom owing to advancements in technologies, innovation in highly integrated electronic components, and the emergence of complex electric devices. What is automatic test equipment? ATE is computerized machinery that utilizes test instruments to complete and evaluate the results of functionality, quality, performance, and stress tests performed on electronic devices. Furthermore, it automates the traditional manual electronic testing processes and demands less to no human intervention. Automatic test equipment is often known as automated test equipment or automated testing equipment. On the other hand, the devices that are assessed by ATE are referred to as a device under test (DUT), equipment under test (EUT), or unit under test (UUT). Today, several electronic devices are tested by ATE to ensure the performance, functionality, and safety of those who would ultimately use them in workplaces. ATE include printed circuit boards (PCBs), integrated circuits (ICs), hard disk drives, and other several electronic systems and line-replaceable units that support aircraft, satellite, and spacecraft. How does ATE work? ATE monitors, controls, and captures data using an array of test instruments and signal sources such as digital multimeters, LCR meters, digital storage oscilloscopes, radiofrequency, and arbitrary waveform generators. A high-performance data acquisition (DAQ) computer runs special test software or DAQ software that controls the test station’s instruments and signal sources. The raw data captured by test instruments are analyzed and stored using signal sources and test software and these readings essentially determine whether the device needs correction or not. Is ATE beneficial? The purpose of ATE is to ensure the performance and functionality of electronic devices once they are in the customer’s hands. Moreover, the automatic test prevents faulty devices from entering the market. And one step further, if a fault occurs during testing procedures, ATE helps diagnose why the devices are found at fault and allows manufacturers to correct their procedures. In a long run, ATE systems help save a colossal amount of money and cut down the testing time by digitizing traditional manual testing equipment that often relies on humans. ATE system’s automation factor ensures test and cycle time by eliminating variable troubleshooting on behalf of engineers. It eliminates human intervention and thus, human errors. These systems are efficient and cost-effective and allow engineers to focus on occasional testing instead of testing every electronic device manually. Most importantly, ATE systems are much faster and offer more accurate test results as compared to manual testing that relies on the speed and skill of the engineer. In the last couple of years, the use of ATE systems has skyrocketed across various industries and companies. In fact, everything from missile launches to avionic systems is validated by automatic test equipment, and in the future, the user will surely increase even further.


Type:Technology
👁 :
የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ የ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ብድር አጸደቀ
Catagory:News
Auter:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አስፍጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ ለአራት ዓመት የ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የተራዘመ ብድር አገልግሎት አቅርቦትን አጽድቋል፡፡ አይ ኤም ኤፍ ጉዳዩን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አስፈጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ የሚሆንና መጠኑም 2.556 ቢሊየን SDR (የኮታው 850% ወይም ወደ 3.4 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ) የሆነ፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መፋለስን መፍታትን እና በግል ዘርፉ ለሚመራ እድገት መሠረት መጣልን አላማው ያደረገውን የመንግሥትን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አፈጻጸም የሚደግፍ የአራት ዓመት የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት(ECF) አጽድቋል። የአስፈጻሚ ቦርዱ ውሳኔም ኢትዮጵያ ከባላንስ ኦፍ ፓይመንት ጋር የተያያዙ ፍላጎቶቿን እንድታሟላ የሚረዳትን እንዲሁም በጀቷን የሚደግፈውን የ766.75 ሚሊየን SDR ወይም 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ክፍያ ወዲያውኑ እንዲለቀቅ የሚያስችል ይሆናል። በአራት ዓመቱ የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት የሚደገፈው የመንግሥት የኢኮኖሚ ፕሮግራም የግል ዘርፉን እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ ሁለገብ የፖሊሲ ፓኬጅን እንዲሁም የላቀ እና በይበልጥ አካታች የሆነ እድገትን ማምጣትይቻል ዘንድ ኢኮኖሚውን ክፍት ማድረግን ኢላማው ያደረገ ነው። ማሻሻያው ተጋላጭ በሆኑ ቤተሰቦች/አባዎራዎች ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ ለማለዘብ ይቻል ዘንድ የማህበራዊ ሴፍቲ ኔቶችን ማጠናከርም የመንግሥት የማሻሻያ ፕሮግራም አንድ ወሳኝ ክፍለአካል ነው። ቁልፍ የሚባሉት ፖሊሲዎችም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ 1) ውጫዊ ኢሚዛናዊንትን ለመፍታት እና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለማስታገስ በገበያ ወደሚወሰን የምንዛሪ ዋጋ መሄድ፤ 2) የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍን በማዘመን የዋጋ ግሽበትን መዋጋት፤ 3) የሀገር ውስጥ የገንዘብ ምንጮችን በማሰባብሰብ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ሕዝባዊ ወጪዎች ማዋል፤ 4) ከውጪአበዳሪዎች ጋር የሚደረጉ ወቅታዊ የእዳ ሪስትረክቸሪንግ ስምምነቶችን በመፈጸም ጭምር የእዳ አከፋፈል ዘላቂነትን መመለስ እንዲሁም 5) ወሳኝ የሆኑ የማክሮ ፋይናንሺያል ተጋላጭነቶችን ለመቀነስ የመንግሥት ኢንተርፕራይዞችን የገንዘብ አቋም ማጠናከር። ፕሮግራሙ ከልማት አጋሮች የሚገኝ ተጨማሪ የገንዘብ አቅርቦትን በማፋጠን እንዲሁም በመካሄድ ላይ ያለው የእዳ ሪስትረክቸሪንግ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የሚያደርግ ማዕቀፍ በመስጠት ረገድ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።


Type:News
👁 :
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ
Catagory:News
Auter:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመጪው ረቡዕ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል፡፡ በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 58 ( 4) እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራርና የአባላት ሥነ- ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 15 ( 1 ና 2) መሰረት ምክር ቤቱ በዕረፍት ላይ እያለ የምክር ቤቱን ውሳኔ የሚሹ አስቸኳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ በዚህ መሰረትም ለረቡዕ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡ ስለሆነም የ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በዕለቱ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ ሪፖርት በማድረግ በአስቸኳይ ስብሰባው እንዲገኙ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡


Type:News
👁 :
ቻይና ሙቀት የሚያመርት 4ኛ ትውልድ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ የማስፋፊያ ሥራ ጀመረች
Catagory:News
Auter:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

ቻይና በዓለም የመጀመሪያ የተባለውን ከፍተኛ ሙቀት አምራች አራተኛ ትውልድ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የማስፋፊያ ሥራ ጀምራለች። የማስፋፊያው ሥራ በምስራቅ ቻይና ሻንዶንግ ግዛት በትናንትናው እለት መጀመሩም ተመላክቷል፡፡ ቻይና ሙሉ በሙሉ ነፃ የሆነና የአዕምሮአዊ ንብረት መብት ባለቤት የሆነችበት ፕሮጀክት በሮንግቼንግ ግዛት በዌይሃይ ከተማ ውስጥ ይገኛል። ፕሮጀክቱ በቻይና ሁዋንግ ግሩፕ፣ በስንጉዋ ዩኒቨርሲቲ እና በቻይና ብሔራዊ ኒውክሌር ኮርፖሬሽን በጋራ የለማ መሆኑ ተመላክቷል። በዓለም የመጀመሪያው የሆነውና አራተኛው ትውልድ በመባል የሚታወቀው ይህ የኒውክሌር ጣቢያ ባለፈው ታህሳስ ወር ወደ ንግድ ስራ መግባቱ ተገልጿል። የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ የማስፋፊያ ምዕራፍ ሌላ በሀገር ውስጥ የበለጸገ በውሃ ሃይል የሚሰራ ሶስተኛ ትውልድ ሁዋሎንግ ዋን የተሰኘውን ማመንጫ በጋዝ ማቀዝቀዝ ስርዓት ከሚሰራው ጋር በማገኛኘት ማሰራት መሆኑን የኩባንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ዣንግ አይጁን ተናግረዋል። ይህ ማስፋፊያ የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነት መብት ያላቸው የሁዋሎንግ ዋን ሁለት ክፍሎችን ያካተተ ሲሆን÷ ማመንጫዎቹ እያንዳንዳቸው 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ኪሎ ዋት አቅም እንዳላቸው ዣንግ ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በዓመት 20 ቢሊየን ኪሎ ዋት ሰዓት በማመንጨት የሙቀት አቅርቦቱን በ20 ሚሊየን ካሬ ሜትር እንደሚያሳድግና 600 ሺህ ነዋሪዎችንም ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አክለዋል፡፡ ወደፊት የተያዘው የማስፋፊያ ዕቅድም እያንዳንዳቸው ከ1 ሚሊየን ኪሎ ዋት በላይ አቅም ያላቸው በውሀ ግፊት የሚሰሩ አራት ተጨማሪ ማመንጫዎችን እንደሚጨምር መናገራቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።


Type:Technology
👁 :
እስራኤል በጎላን ተራራ ሂዝቦላ ያደረሰባትን ጥቃት ተከትሎ ሊባኖስን በቦንብ ደበደበች
Catagory:News
Auter:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

እስራኤል በጎላን ተራራ ሂዝቦላ አድርሶብኛል ያለችውን ጥቃት ተከትሎ ሊባኖስን በቦንብ መደብደቧ ተነግሯል፡፡ የእስራኤል ጦር በማእከላዊ ዴር ኤል ባላ ውስጥ ለመስክ ሆስፒታል እና ለመጠለያነት በሚያገለግል ትምህርት ቤት ላይ ጥቃት በመሰንዘር 15 ህጻናትን ጨምሮ 30 ሰዎችን ለህልፈት ዳርጓል ነው የተባለው። ሂዝቦላህ በእስራኤል በተያዘው ጎላን ተራራ በሚገኘው ማጅዳል ሻምስ ከተማ ሮኬት በመተኮስ 12 የድሩዝ ማህበረሰብ ወጣቶችን መግደሉ ተመላክቷል፡፡ ጥቃቱን ተከትሎም የእስራኤል ጦር በደቡብ እና ምስራቅ ሊባኖስ የሚገኙ መንደሮችን እና ከተሞችን በቦምብ ደብድቧል። እስራኤል ለተፈፀመባት ጥቃት ሂዝቦላን ተጠያቂ ታድርግ እንጂ የሊባኖስ ቡድን ለሮኬት ጥቃቱ ኃላፊነት አለመውሰዱን አልጀዚራ ዘግቧል።


Type:Social

Page 4 of 75