Entertailment Page

Entertailment






👁 :
በአሶሳና አካባቢዋ የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ አገልግሎት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/19/2024
Posted By:utopia online

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከትናንት ጀምሮ በአሶሳ ከተማ፣ ባምባሲ፣ ቶንጎ፣ መንጌ፣ ሆሞሻ፣ ኩምሩክ እና አካባቢዎቻቸው የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ወደ አገልግሎት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ከመንዲ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ አሶሳ ከተማ በተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ እያጋጠመው ባለው ተደጋጋሚ ብልሽት ምክንያት ኃይል መቋረጡ ተመላክቷል፡፡ በመሆኑም እየተከናወነ ያለው የጥገና ሥራ እስከሚጠናቀቅ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞች በትግዕስት እንዲጠብቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጥሪ አቅርቧል፡፡


Type:Technology
👁 :
ሚኒስቴሩ በህፃን ሄቨን ላይ በተፈፀመው ወንጀል በተሰጠው ውሳኔ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሰራ አስታወቀ
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/19/2024
Posted By:utopia online

በህፃን ሄቨን ላይ በተፈፀመው ዘግናኝ የሆነ ኢ ሰብአዊ ወንጀል የተሰጠው ዉሳኔ አስመልክቶ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚኬድበት አግባብ ባለመሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሰራ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የህፃናትን መብት በማስጠበቅ ረገድ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ ተግባራትን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በህፃናት መብት ጥበቃ ላይ በተለየ መልኩ የፖሊሲ አቅጣጫዎች እንዲቀመጡና የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የሚፈፀሙ ጥቃቶች የሚመዘገቡበትና ተገቢ የሆነ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት እንዲያገኙ የህፃናት የመረጃ አያያዝ ሰርዓት እንዲዘረጋ እና የቅንጅት ስራዎች እንዲጠናከሩ እየተደረገ መሆኑም ተመላክቷል፡፡ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለችውን ህፃን ሄቨን በተመለከተም በደረሰው ዘግናኝ የሆነ ኢ-ሰብአዊ ወንጀል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሰማውን ሀዘን ገልፆ ይህንን አይነት የህፃናት ጥቃት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በፅኑ እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡ በተፈፀመው ወንጀል ዙሪያም የተሰጠውን ዉሳኔ አስመልክቶ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚኬድበት አግባብ ባለመሆኑ ከፍትህ አካላት እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራ እና እንደሚከታተል አረጋግጧል፡፡


Type:Social
👁 :1
የጉለሌው ሰካራም1 በተመስገን ገብሬ2 ክፍል 2
Catagory:tireka
Auter:
Posted Date:08/19/2024
Posted By:utopia online

ዝናቡ እስኪያባራ ይቆያሉ፡፡ ተበጀን ‹‹ ቤትህን ይባርክ ›› ሊሉት ነው፡፡ እንግዲህ መንገደኛው ሁሉ ‹‹ ይህ የማን ቤት ነው ? ብሎ ሲጠይቅ የተበጀ ሊባል ነው ›› አለ፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ‹‹ ተበጀ የትኛው ነው ሲባል ዶሮ ነጋዴው ሊባል ነው ›› አለ፡፡ ‹‹ ዶሮ ነጋዴው የትኛው ነው ›› ሲባል ያ የጉለሌው ሰካራም ሊባል ነው፡፡ አወይ፤ እኔ ተበጀ፤ ተበላሽቻለሁ አለና ደነገጠ፡፡ ከዚህ በኋላ ስለቤቱ ክብር እንኳ መጠጥ መተው ይገባኛል አለ ፡፡ መጠጥ ለመተው ያሰበበት የመጀመሪያ ጊዜው ይህ ነው፡፡ ሰካራምነት ጉዳት መሆኑ ተሰምቶት እንደሆን ይናገር ስለ ቤት ክብር ማለቱ ግን ወደ ዳር ይቆይ፡፡ ስለ ቤት ክብር ምን ያውቃል? ዶሮ ነጋዴው ተበጀ ሰካራሙ ተበጀ አይደለምን ? ሰካራሙ ተበጀ የሰራውን የገዛ ቤቱን ከፍቶ ገበና ኩራዙን አስቀምጦ ክብሪቱን ለመጫር ሲያወጣ በሐሳብ ተሰቅዞ እንደዚህ አሰበ፡፡ መምረጥ አለብኝ፡፡ ከዚህ ቤት ያለው መጠጥ ሁሉ አንድ ሳይቀር እየወጣ ይፍሰስ፤ ከዚህ በኋላ ክብሪቱም ኩራዙም በቤት ይደር፤ በአዲሱም ቤት ብርሃን ይዙርበት፡፡ አለዚያም በአዲሱ ቤት መጠጥ ይዙርበት፤ ኩራዙም ክብሪቱ ከቤት ይውጣና ይፍሰስ፡፡ ሊደረግ የሚገባ ከሁለቱ አንዱ ነው እንጂ፤ በሰካራሙ ተበጀ ቤት መጠጥና እሳት በአንድነት ይህች ውሸት አለና ሳቀ፡፡ ከሁለቱ አንዱ ለማድረግ ሳይቆርጥ መብራቱን አቃጠለና ተቀመጠ፡፡ እንደገና ደግሞ እንደዚህ አሰበ፡፡ አያድርገውና ዛሬ ሰክሬ ይህ ቤት ቢቃጠልብኝ አመዱን አይቶ በሰካራሙ ተበጀ ላይ ለመሳቅ ድፍን ጉለሌ ነገ ከዚህ ነው የሚቆም ! ጉለሌ ምን ባለኝ? ወሬ ከማቡካት በቀር ጉለሌ ምን ሥራ አለው; ለአዲስ አበባም የስድስት ወር መሳቂያ በሆንኩ ነበር፡፡ መንገድ አላፊዎችም ነገ በዚህ ሲያልፉ አመዱን አይተው ይህ የተቃጠለው ቤት የማን ነበር ሲሉ የተበጀ ሊባል ነው፡፡ በሰካራሙ ተበጀ ቤት መጠጥና እሳት ባንድነት ይህች ውሸት ! ወደ ውጭ እንደ እርም ወርውሮት የነበረውን የመጠጥ ጠርሙስ ሁሉ በጨለማው ዳብሶ አንድ በአንድ ለቃቀማቸው፡፡ አንዱን ግን ቀና አደረገና ከአፍንጫው አስጠግቶ አሸተተው፡፡ በጠርሙሱ ቅርፅ የመጠጡን አይነት አወቀው፡፡ ዊስኪ ነበርና ስለዚህ ነው ሰው እንዳይሰማ ቀስ ብሎ የሳቀ፡፡ የጠርሙሱን ግማሽ ከጠጣ በኋላ ግን በአፉ ቡሽ ቢወትፍበት ለሳቁ መጠን የለውም፡፡ ‹‹ ጉለሌ ተኝቷልና ከዚሁ ከባሕር ዛፍ ሥር ቁጭ ብየ ብጠጣ የሚታዘበኝ የለም›› አለና አሰበ፡፡ እውነቱን ነው፡፡ ጉለሌስ ተኝቶ ነበር ነገር ግን አሁን እርሱ ጠጥቶ የሰከረ እንደሆነ ጉለሌን ሊቀሰቅሰው ነው እርሱ ከጠጣ በጉለሌ ማን ይተኛል? ጠርሙሱን ከከፈተው በኋላ ብርጭቆ ያስፈልገው እንደነበር ትዝ አለው፡፡ ሶስት የሚሆን ደኅና ጉንጭ ጠርሙሱን ከአፉ አስጠግቶ ጨለጠ፡፡ ከዚያ በኋላ የሚጠጣበት ብርጭቆ ሊያመጣ አሰበ ከዚያ በኋላ ደግሞ በሶስት ጉንጭ ምን ያህል ጠርሙሱን ቀና አድርጎ በጨረቃዋ ተመለከተ፡፡ ‹‹ግማሹን ያህል ሰርጉጀዋለሁ›› አለና በሳቅ ፈነዳ፡፡ ‹‹ ለዚህችስ ብርጭቆ ማምጣት አያሻም›› እያለ ጠርሙሱን አምቦጫቦጨው፡፡ በቀኝ ክንዱ መሬቱን ተረክዞ የቀረውን ጅው አድርጎ ወደ ውስጥ ወረወረው፡፡ ባዶውን ጠርሙስ ደግሞ በጁ እየጠነቆለ ‹‹አንተን ደግሞ ለአንድ ዶሮ ለውጩ ሞያ እይዛለሁ የዊስኪ ቅርፍቱም ዋጋ አለው አይጣልም›› አለ፡፡ ‹‹እንዲሁ ሲጠጣ ሌሊቱን አጋመሰው፡፡ ቀጥሎ ከእግሩ በታች የወደቀውን ጠርሙስ እየቆጠረ ይህን ሁሉ እንደጠጣሁት አላምንምና በጉለሌ አፈርሳታ ይደረግልኝ እነናቄ እነተሰማ አጎቴም ይጠጣሉ›› አለ፡፡ የጠርሙሱ መጠጥ ሁሉ እስኪያልቅ ድረስ ከዚያ ከዛፉ ሥር ተቀምጦ ያን ጠንካራ ትምባሆውን ከአፉ አላየውም፡፡ በሳቅ ጊዜ ብቻ መልሶ ዝም እስኪል ድረስ መጠጡ ወይም ትምባሆው ከአፉ ያቋርጣል፡፡ የመጠጥና የትምባሆ ጊዜው ተበጀ ይህ ነው፡፡ማለዳ በቀዝቃዛ ውሃ ታጠበ፡፡ ቋንጣም እንቁላልም ጠበሳና በዳቦ በላ፡፡ የጦም ቀን ነበር ‹‹ ለአባ ተክለ አረጋይ አልናገርምና ነፍሴ ሆይ ግድ የለም አለ››፡፡ የነፍስ አባቱን ማለቱ ነው፡፡ ምናልባት በዓመት እንኳ አንድ ጊዜ ጠየቋቸው ወይም ጠይቀውት አያውቁም፤ እርሱንም አያደርሰውም፤ እርሳቸውም ከበዓታቸው አይወጡም፤ አንዳንድ ጊዜ የዛሬውን እሑድ ዕረፍት አደርገዋለሁ ያለ እንደሆነ እግሩን ደኅና አድርጎ የሚታጠብበት ቀን ማለት ነው፡፡ ደክሞት ነበርና ደኅና እንቅልፍ ተኝቶ ነበር፡፡ ዝናሙን ነጎድጓዱን ጎርፉን ውሃ ምላቱን አልሰማም፡፡ አንዳች ነገር ሰማ፡፡ ዘፈን እና እልልታ የሰማ መሰለው፡፡ ትናንት ከጠጣው መጠጥ ኃይል መሰለውና ይህስ ዕብደት ነው እንጂ ስካር አይደለም አለና ተመልሶ ተኛ፡፡ እንደገና አዳመጠ፡፡ የእርዳታ ጥሬ ጩኸት ሰማ፡፡ ከ አልጋው ዘልሎ ከወረደ በኋላ ቤቱን ለመዝጋት ጊዜ አላገኝም፡፡ በትልቁ ወንዝ ዙሪያ ቁመው ይጮሁ የነበሩ ሰዎች የውሃው ምላት የሾገሌን ገረድ እንደጠለፋት ነገሩት፡፡ ጉርፍ የወሰደው ሾገሌን ራሱን ቢሆን ወይም የሾገሌን ገረድ ለተበጀ ማዕረግ ምኑም አይደለም፡፡ ‹‹ ገረዲቱን እናንተ በመጨረሻ ያያችኋት ወዴት ነው? ›› ብሎ ጠየቀና እየጠለቀ በዋና ይፈልግ ጀመር፡፡ ስለ ሾገሌ ገረድ በትኩስ ውሃ ምላት ለመግባት አንሠዋም ያለው ጉለሌ በዳር ተሰልፎ ቁሞ ተበጀን ይመለከት ነበር፡፡ ብዙ ጠልቆ ከቆየ በኋላ ብቅአለና ‹‹ አገኝኋት መሰለኝ ›› ብሎ በዳር ላሉት ጮሆ ተናገረ፡፡ ለሰው ሁሉ ደስታ ሰጠው፡፡ ከሁሉም ይልቅ እርሱን ደስ አለው፡፡ የጠለቀውና የዋኝው ረጅም ጊዜ ስለሆነ ደክሞት ነበር፡፡ ነገር ግን ሊያወጣት ይገባዋል፡፡ ጠለቀና አገኛት፡፡ በአሸካከሙ ላይ ጥበብ ያስፈልጋል፡፡ አለዚያስ ውሃው ምላት እንደገና ይነጥቀዋል፡፡ እንደተሸከማት ውስጥ ለውስጥ ዋኝና ከዳር ብቅ አለ፡፡ ከሸክሙ ክብደት ኃይል የተነሣ ወዲያው ወደቀ፡፡ እርዳታ ተነባበሩለትና ጎትተው እርሱንም እርሷንም አወጧቸው፡፡ ተበጀ ተንዘራግቶ በብረቱ ውጋት እያቃተተ የጉለሌ ሰው በሳቅ ሲፈነዳ ሰማ- ከራሱ ነኩል ቀና አለና ‹‹ ሴትዮዋ ድናለች? ›› ብሎ በርኅራሄ ድምፅ ጠየቃቸው፡፡ አንዱ ቀረበና ‹‹ አሳማ ነው ያወጣሃው ›› አለው፡፡ የሚያቃትተው ተበጀ ከወደራሱ ቀና አለና ‹‹አሳማ?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ‹‹ ለመሆኑ ከእናንተ ውሃ ወሰደባችሁ ሰው ነበር ወይስ አሳማ ኑርዋል? ›› ብሎ ተበጀ ጠየቀና ያቃትት ጀመር፡፡ ጎረቤትህን እንደነፍስህ ውደድ ቢባልም ሰዎችን እነ እቲላን ነበር እንጂ የእቲላን አሳማዎች አልነበረም፡፡ እቲላ ጎረቤቱ አሳማ አርቢ ነው፡፡ ውሃው ምላት ነጥቆ ወስዶ የነበረ የእቲላን አሳማ ሳለ ያላዩትን ቢያወሩ ግድ የሌላቸው ሰዎች የሾገሌን ገረድ ውሃ ወሰዳት ብለው አውርተው የተበጀ ነፍስ ለአንድ አሳማ ነፍስ ሊያስለውጡት ነበር፡፡ መልካሙ የሰማዕትነት ሥራው ሁሉ ደግሞ እንዲሁ ርካሽ ሆኖ የሚቆጠር የሆነበት ዘወትር የሚሰክር ሆኖ ስለታወቀ ነው፡፡ በሞራልም (ግብረ ገብነት) መሠረት አደረግሁት የሚለውን ሁሉ ሳያውቀው እንደሚያደርገው ይቆጥሩበታል፡፡ ‹‹ በጎ ሥራህን ሁሉ በትኩስ መቃብር ውስጥ አፈር አልብሰው አንተ ሰው ሁን ሚስት አግባ ልጆች ይኑሩህ›› ይሉትና ይዘልፍት ነበር፡፡ ድኃ ቢሆን ወይም ባለጠጋ ሰካራም ቢሆን ወይም ትኅርምተኛ ሁሉም የጉለሌ ልጆች ነን አባታችንም ጉለሌ ነው ብሎ ራሱን ሚያኮራ እርሱ ተበጀ ብቻ ነው፡፡   ከሚያሰክር ሁሉ ትኅርምተኛ ለመሆን ብዙ ጊዜ አስቦ ነበር፡፡ ሰክሮ ያደረበት ሌሊት አልፎ ብርሃን በሆን ጊዜ ከእንግዲህ ወዲህ ‹‹መጠጥ አልቀምስም›› እያለ እየቀኑ በብርሃን ተበጀ ምለዋል፡፡ በነጋዉ የበለጠ ጠጥቶ የባሰ ሰክርዋል፡፡ ለመስከር ይጠጣል፡፡ ደስ ያለው እንዲመስለው ይጠጣል፡፡ ብስጭቱን የሚረሳ መስሎት ይጠጣል ይህ ነው ተበጀ፡፡ ‹‹ ይህን መስከርህን ካልተውህ ላንተ አበ ነፍስ አልሆንህም›› ብለው የመጀመሪያ ንስሐ አባቱ ብዙ ከመከሩት በኋላ መንፈሳዊ ልጅነቱን ከርግመት ጋራ አስወግደውታል፡፡ ገረዶቹም ለርሱ ተቀጥሮ መሥራትን ከውርደት ቆጥረውት እየነቀፉት ሂደዋል፡፡ ‹‹ መጠጥ ካልተውህ አናገባህም›› ብለው እየጊዜው ለጋብቻ ጠየቋቸው የነበሩ በቁመናው አሰናብተውታል፡፡ በሰምበቴ በማኅበርም ማኀበርተኛ ለቦሞን የጠየቃቸው ነፍሱን ሳይቀር ንቀውታል፡፡ ይህ ሁሉ በእርሱ ዘንድ ከኢምንት አይቆጠርም፡፡ ያሉትን ቢሉ እርሱ ምን ቸገረው ገንዘብ እኮ አለው፣ ገንዘቡም ጥሬ ብር ነው፡፡ ባለጠጋ ነው፡፡ መስከረም የባለጠጎች ነው፡፡ ትኅምርተኛ መሆንም የድሆች ነው፡፡ እንደ ልዩ አመፅ አድርገው ለምን በእርሱ ይቆጥሩበታል? እንዲህ በተከራከረ ነበር፡፡ ነገር ግን ልዩነት አለው፡፡ እርሱ ብዙ ጊዜ ሰክሮ አውቶሞቢል በላዩ ላይ ሒዶበታል፡፡ ሰክሮ በበነጋታው ከእንቅልፉ ሲነቃ ብዙ ጊዜ ከእስር ቤት ውስጥ አድሮ ራሱን አግኝቶታል፡፡ በጉለሌ መንገድ ዳር ባሉት በብዙ የውሀ ጉድጓዶች ሰክሮ ገብቶባቸው እየተጮኸ ጉለሌ አውጥቶታል፡፡ ሰክሮ የጎርፍ ውሀ ከወሰደው በኋላ ብዙ ጊዜ እሳት አደጋ ደርሶለታል፡፡ ሰክሮ ከቤቱ መድረስ እያቃተው ከወደቀበት ባቡር ምንገድ ሳይነሳ ብዙ ጊዜ ጎርፍ በላዩ ላይ ሲሄድበት አድርዋል፡፡ ይህ ሁሉ ውርደት እና ርክሰት ነው እንጂ ክብር ከቶ አይደለም፡፡ እንግዲያውስ ክቡር ደሃ ነው ገንዘብ ስለሌለው ራሱን መግዛት ይችላል፡፡ ባለጠጋ ደግሞ መናኛ ተራ ነው፡፡ ገንዘብ ስላለው ራሱን መግዛት አይችልም፡፡ ይህን ሁሉ አሰበ፡፡ ስለኖረ ባይማር እንኳ ብዙ ከማወቅ ደርሰዋል፡፡ ‹‹ ባለጠጋ ሆነ ወይም ደሀ፣ ሰው ከራሱ የበለተ መሆን ይገባዋል››፡፡ አለ፡፡ ቤቱን ከሠራ ከአምስት ወራቶች በኋላ ጀምሮ ተበጀ መጠጥ ከቶ አልተጠጣም ስለቤቱ ክብር መጠጥ እርም ነው ማለት ጀምሯል፡፡ ያለፈውንም ዘመን መራርነት እያሰበ ተንገፍግፈዋል፡፡ አንድ ብሎ ለመጀመር ከወደቀበት ትቢያ አንስቶ ዕድሉን ሲራግፍ እነደ ራዕይ ያያል፡፡ ያበላሸው እድሉ አሳዘነው ‹‹ በዚህ እድሜየ ሁሉ ሚስትም አላገባሁ ልጅም የለኝም›› አለና አዘነ፡፡ ውሾቹ እየተባሉ ሲጫወቱ ተመለከተና ‹‹አመሌ ውሻ ነበርና ከውሾች ጋር ኖርኩ›› ብሎ ራሱን ረገመ፡፡ በውሾች ፈንታ አሁን በዚህ እድሜው ልጆቹ ዙሪያውን እየተጫወቱ ሲፈነጩ ባየ ነበር እንዲሁ አሰበ፡፡ ቀልድና ወዘበሬታ ስለሚያውቅ እንደዚህ እያለ ይቀልድ ነበረ፡፡ ጉጃም የአበባውንና የግራር ማሩን ይጭናል፡፡ የተጉለትና የአምቦ ወረዳ ጌሾውን ያቀርባል፡፡ የሆላንድ የቢራ ፋብሪካ ቢራውን ያወጣል የኢጣሊያ ፋብሪካ ወይን ጠጅ (ነቢት) ያፈላል፡፡ መደቅሳና ዘቶስ በግሪክ አገር ይጣራል በስኮትላንድ ዊስኪ ይጠመቃል፡፡ ይህ ሁሉ የሚደረገው በአራዳ የሚቀመጡትን እንዳይተማቸው ነው፡፡ በዚህም ምክንያት መዋሻዋ እንደምትጮህ ጉጉት ሰካራሞች በከተማይቱ ይጮሃሉ፡፡ ‹‹በደብረ ሊባኖስ ግን ድምጡን ዘለግ አድርጎ የሚናገር ወፍ እንኳ የለም፡፡ ውሃ እንኳ የሚጠጣ በመቅነኑ ነው፡፡ በአራዳ አሁን ወይም በገዳም ምንም ገንዘብና ቢስቲን ለሌለው ውሀ ደግሞ እጅግ አድርጎ ይጣፍጣል፡፡›› ይህን የመሰለ ቀልድ ይቀለድ ነበር፡፡ ሰካራሙ ተበጀ ግን ገንዘብ እያለው ወሀ ጣፍጦታል፡፡ ልዩ በሆነው በዚያ ማታ ወደ አልጋው ወጥቶ በተኛ ጊዜ መጠጥን እርም ካደረገው አንድ አመት ከዘጠኝ ወር ከዘጠኝ ቀን እንደ ሆነው ጊዜውን ቆጥሮ አወቀው፡፡ ጊዜውንስ ማወቅ ለምን አስፈለገው? ‹‹ እንደ ጉድፍ ( ጥንብ) መጣያ ትንፋሼ ተበላሼ፤ አፌም እነደ እሬት መረረኝ ሹልክ ብየ ዛሬ ብቻ፤ ጥቂት ብቻ፤ አንድ ጊዜ ብቻ፤ እኔ ብቻ፣ ብጠጣ ምን ይጎዳል›› ብሎ ተመኝቶ ስለመበረ ነው፡፡ ነገር ግን ወደ አልጋው ወጥቶ ተጋደመ ከተጋደመም በኋላ ተነሥቶ መጠጥ ቤት ለመሄድ ከባድ ከነበረው እንቅልፉ ለበላቀቅ ታገለ፡፡ በመጨረሻ ወደ መጠጥ ቤት በሄደ ጊዜ በውኑ ወይንም በሕልሙ እንደነበረ ራሱን ተበጀ አላውቀውም፡፡ የጠጣም እነደሆነ ከሁለት መቶ ዓመት በፊት ይደረግ በነበረው የአረመኔ ቅጣት እጁን እግሩ ከመቆረጥ ይደርሳል ብሎ አላሰበም፡፡ አናጢ የጠረበው እንጨት ከቅልጥሙ ይቀጠላል ብሎ ክፉ ሕልም አላለመም፡፡ አንድ ሰካራም አንካሳ በአንድ ዓመት ስንት የእንጨት እግር ይጨርሳል ብሎ ስለዋጋው አልተጨነቀም፡፡ ደኅና ምቾት ያለው አንካሳ ለመሆንም ገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ አንካሳው ሰው ሰካራም እንደሆን በእንጨት እግሩ በሰላም ጊዜ ይሄድበታል፡፡ በሁከት ጊዜ ደግሞ ይማታበታል፡፡ ሲማታበት ይሰበራል ሲሰበርም ሌላ የእነጨት እግር መግዛት ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህ የእንቸጥ እግር የሚሰሩ አናጢዮች ለደንበኞቻቸው ትርፍ መጠባበቂያ እግር በሜንጦ ሰቅለው ያስቀምጡላቸዋል ይባላል፡፡ ተበጀን እንደዚህ ያለ ሕይወት አያጋጥመውም፡፡ በበቀለች ዓምባ መጠጥ ቤት ደረጃውን ተራምዶ ተበጀ በገባ ጊዜ የጥንት ወዳጆቹ ስካሮች በእቅፍ ልይ ተነባበሩ፡፡ እንደተወደደ መሪ በጫንቃቸው ላይ ተሸክመው እየተቀባበሉት በዕልልታ ጮሁ፡፡ ከመጠጥ ቤት ጠፍቶ የነበረው ተመልሰዋልና በስካሮች ሁሉ ዘንድ ደስታ ሆነ፡፡ እንኳን በደኅና ገባህ! የመጠጥ ጠርሙሶቹን እንደ ዘንባባ ይዘው ተቀበሉት ቁማርተኛው ያረጀ ግሪክ እየሳለ ተናገረ ሁሉም በደስታ ይጮሁ ስለነበረ አንድም የሰማው የለም፡፡ ረስቶት የነበረው መጠጥ ጣዕሙን ገና ሳያውቀው ገና ከጫብቃቸው ሳይወርድ በጩኸቱም በመጠጡም ተበጀ ሰከረ፡፡ ከጫንቃቸው ወደ ቁልቁል ጣሉት ፡፡ የሕፃንነት ዘመን አልፉልና ራስህን ችነል መሄድ ይገባሃል አሉት፡፡ ሰማህ? አቅም አንሶህ መሄድ አቅቶሃልና እንደኩብኩባ እየዘለለህ መሄድ ትችል እንደሆነ ምርኩዜ ይኸውልህ ብሎ አንካሳው በየነ አቀበለው፡፡ ምረኩዙን ለመያዝና ለመጨበጥ እጁን ሲዘርር በግምባሩ ከበሬት ላ ተደፋ፡፡ እንደ ወደቀም ሳለ፤ እስኪነቃ ድረስ በመካከሉ ስንት ሰዓት አልፎ እንደነበረ ለማስተዋል አልቻለም፡፡ የመጠጥ ቤቱ እመቤት ጊዜ አልፏልና ከውጭ ጣሉትና ቤቱን ዝጉት ብላ አዘዘች፡፡ ወደቤቱ የተመለሰ መስሎት ሄደ፡፡ ማወቅ አልቻለምና ወዴት እንደሄደ ግን አላወቀም፡፡ አንድ መንገድ ሲያቋርጥ ተሰናከለና ወደቀ፡፡ ከወደቀበትም ምድር ላይ በዳሰሰ ጊዜ ለእጁ የገጠመው የባቡር ሀዲድ ነው፡፡ ቤቱ ያለ በጉለሌ ነው፡፡ የሰከረበት ደግሞ የበቀለች መተጥ ቤት ነው፡፡ መጠጥ ቤቱም ከዩሃንስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ነው፡፡ ምን ያህል ቢክር ነው የጉለሌ መንገድ ጠፍቶት እስከ ባቡር ሀዲድ ድረስ ተሳስቶ የሄደ; ራሱን ይዞ ለመጮህም ራሱ ወዴት እንዳለ ማወቅ አቃተው፡፡ እንደ ቤቱ መንገድ ጠፋበት፡፡ ጥቂት መስማት ከቻለ በኋላ ጩኸት በስተ ኋላው የነፋ ነበረ የእሳት አደጋ ወይስ ባቡር ኑርዋል; እያፎደፎደ ሲሄድ ከወደ ኋላው በኩል ምን እንደገፋው አላወቀም፤ ከኋላው በኩል ትልቅ ሀይል መታው፤ ከፊቱ በኩል ቀበሮ ጉድጓድ ተቀበለው፡፡ እግሩ እንደ ብርጭቆ ነከተ፡፡ ከወደቀበትም ሌሊቱን ሁሉ ደም ከእግሩ ዘነመ፡፡ ትንኝም እንደ ንብ በላዩ ሰፎ ደሙን መጠጠው፡፡ ቀና ብሎ በአጠገቡ የወደቀውን የአህያ ሬሳ አሞራዎች ሲግጡት አየ፡፡ የቀረው ልቡ በድንጋፄ ተመታ የእርሱ እድል ከአህያው ሬሳ ዕድል ቀጥሎ ሆነ፡፡ በስካሩ ምክንያት እስከ ዘላለም ድረስ ከአህያ ሬሳ እንደ ማይሻል ተረዳው፡፡ ነገር ግን የአሁኑ መረዳት ለምን ይበጀዋል? ማወቅ የሚያስፈልግበት ጊዜ አልፏል፡፡ በሕይወቱ ሳለ እንደ ወደቀ ያህያ ሬሳ መነሳትአልቻለምና በተራው አሞራዎቹን ዓይኑን ሊመነቁሩት ነው፡፡ ሥጋውን በልተው ከጨረሱት በኋላ አጥንቱን ሊግጡት ነው፡፡ሌሊት ደግሞ ቀበሮዋች ሊረፈረፉበት ነው፡፡ ይህን እንዲያመልጥ ለመሸሽ ከወደቀበት ሊነሣ እቃተተ ሞከረ፡፡ ባልተቻለው ጊዜ ግን ተጋደመ፡፡ በደሙ ላይ እነደተጋደመ አራት ቀኖች አለፉ፡፡ እግሩ እንደቀረበታ ተነፋ፡፡ እንደ ቅጠልያ ያለ እዥ ወረደው፡፡ ከወደቀበት ያነሳው የመንግስት አምቡላንስ ባገኝው ጊዜ ፈፅሞ በስብሶ ነበር፡፡ ዶክቶር ክሪመር ባዩት ጊዜ ከሰማይ በታች ሊደረግለት የሚችል ሕክምና ምንድር ነው; ደሙ አልቅዋል፡፡ በሽተኞችን ለመርዳት በጎ ፈቃድ ካላቸው ሰዎች የተለገሰውን ደም ለሚሰክር ጥጋበኛ አልሰጥም፡፡ እርሱን መንካት መርዙን ያስፈራል ከዚህ በፊት ይህ እንዳይደርስበት እንዳይሰክር ብዙ አስጠንቅቀነው ነበር አሉ፡፡ ከንፈሩ ተንቀሳቀሰ፡፡ ላብ በፊቱ እንደ ውሀ ፈሰሰ፡፡ ለመናገር ጣረ፡፡ በመጨረሻ ግን መናገም ስይሆንለት ቀረ፡፡ ሐኪሞችም የገማውን ልብሱን ገፈፉት፡፡ እንደ ቅባትም ያለ መድኃኒት ቀቡት፡፡ ከግማሽ ሊትር የበለጠ ደም ሰጡት፡፡ በመጠጥ ከተጉዳው ከልቡ ድካም የተነሣ ኤተር ለመቀበል አለመቻሉን ከተረዱ ዘንድ የሚያፈዝ መድኃኒት ጀርባውን ወግተው ሰጡት፡፡ አንዱ ሐኪም ከጉልበቱ ይቆረጥ አለ፡፡ ሌላው ግን ሁለተኛ እንዳይሰክር ከቂጡ አስጠግቼ እቆርጠዋለሁ አለና ከቂጡ አስጠግቶ ቆረጠው፡፡ የተቆረጠውን እግሩን ከፊቱ መዝናችሁ አስታቅፉት ብሎ አስታማሚዎችን አዘዘ፡፡ እግሩን ከፊቱ መዘኑትና አሥር ኪሎ የሆነው እግርህ ይኸውልህ ታቀፈው ብለው አስታቀፉት፡፡ በዚህ ጊዜ በአጥንት የተጣሉት ውሾች በላዩ ላይ ተረፈረፉበትና በድንጋፄ ከእንቅልፉ ነቃ፡፡ ይህ ሁሉ የደረሰበት በሕልሙ እንደነበር ማወቅ አቃተው፡፡ ከአልጋው ላይ ወረደና ገረዱን ወይዘሮ ጥሩነሽን ከመኝታቸው ቀስቅሶ እየጮኸና እየተንዘረዘረ ስንት እግር ነው ያለኝ ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ወይዘሮ ጥሩነሽም ‹‹ድሮ ስንት እግር ነበረዎ ጌታ?›› ብለው ጠየቁት፡፡ እየጮኸ ሶስት ጊዜ ‹‹ ሁለት ሁለት ሁለት ነበረኝ›› አላቸው፡፡ ሶስት ጊዜ ሁለት ስድስት ማለት ነው፡፡ ልጆቼን ያሳደገች ላም ካራት እግር የበለጠ አልነበራትም ሰለዚህ የእርስዎም እግሮች አራት ናቸው አሉት፡፡ ‹‹የምሬን ነው የምጠይቅዎት;›› አለና ጮሆ ተንዘረዘረ፡፡ ‹‹በእርግጥ ሁለት እግሮች አሉዎት ጌታ›› አሉት፡፡ ተበጀ እግሩን አጎንብሶ ለመሳም ሞከረና ራቀው፡፡ ወደ ሰማይ እያየ መጠጥ ማለት ለእኔ ሞት ማለት ነው አለ፡፡ ጊዜውም ሌሊት ነበር፡፡ እንደዚህ የማሉበት ሌሊት ያልፋል ብለው ወይዘሮ ጥሩነሽ መለሱለት፡፡


Type:Social
👁 :2
ወራጅ አለ
Catagory:tireka
Auter:
Posted Date:08/19/2024
Posted By:utopia online

ከአራት ኪሎ በስታዲየም ወደ ሜክሲኮ በሚጓዝ ታክሲ ውስጥ ነኝ። በተሳፋሪ መቀመጫ ሁለተኛ ወንበር ላይ በግራ በኩልተቀምጫለሁ። ብዙ ጊዜ የትራፊክ መጨናነቅ በሚስተዋልበትና ባቡር ጣቢያ ፊትለፊት በሚገኘው መስቀለኛ መንገድ ላይእንደደረስን ከጎኔ የነበረች አንዲት ወጣት ባቡር ጣቢያ መድረስ አለመድረሳችንን ጠየቀችኝ። አኔም ሳናልፈው ጥሩ ሰዓትጠየቅሽኝ በማለት በታክሲው በግራ በኩል ባለው መስኮት እያመለከትኩ ያውልሽ ደርሰናል አልኳት። እኔ አመልካች ጣቴንከመስኮቱ ሳላነሳ እኛ ባለንበት ታክሲ ውስጥ ያለውን ረዳት ሳይሆን በቀኝ በኩል ባለው መንገድ ታጥፎ ወደ ቸርችል ጎዳናበሚጓዘው ታክሲ ውስጥ ያለውን የታክሲ ረዳት የምትጠይቅ በሚመስል ድምጽ “ወራጅ አለ” ስትል ከድምጿ ቅጥነትናኃይል የተነሳ ሁላችንም ደነገጥን። በተለይ እኔ…. እንዴት ብዬ ልንገራችሁ! በመጀመሪያ ስታናግረኝ የነበረው ለስለስ እና ዝግባለ ድምጽ ስለነበርና እንደዚያ ያለ ድምጽ በዚያ ቦታ ስላልጠበኩኝ ነው መሰለኝ ክው ነው ያልኩት።አገር አማን ነው ብሎ በብርና በሳንቲም የተሞላውን ግራ እጁን ከፊተኛው ወንበር መደገፊያ ላይ ቀኝ እጁን ደግሞ በከፊልበተከፈተው የታክሲው የበር መስታወት ላይ አስደግፎ ይጓዝ የነበረው ረዳት ከድንጋጤ ይሁን ከንዴት እንጃ አይኑ በርበሬመሰለ። ዞር ብሎ ተመለከተና ዝም አላት።ራሰ ፍንጭቱ ሾፌርም “አዚህ ጋ መውረድ አይቻልም” አሏት በጎርናና ድምጽ።ልጅቱ የሾፌሩን ንግግር ትታ ረዳቱን “ክፈትልኝ” ስትል እንደገና ጮኸችበት።ረዳቱም “ታስከስሽኛለሽ አልከፍትም” አላት። ብትሰማውም ባትሰማውም “ተሻግረሽ ኮሜርስ ነው መውረድ የምትችዪው”ብሎ ሳይጨርስ “ባቡር ጣቢያ እንጂ ኮሜርስ እሔዳለሁ አልኩህ እንዴ? ዞር በልልኝ!” ብላ በሩን ልትከፍት መታገል ያዘች።ሾፌሩ ታክሲውን ቀኝ መስመር በማስያዝና ፍጥነቱንም ቀነስ በማድረግ “ደግሞ ዛሬ ምኗን ነው የጣለብኝ? ኮሜርስ እንጂአዚጋ መውረድ አትችዪም ስትባዪ አትሰሚም እንዴ?” አሏት ንዴት በተቀላቀለበት ቅላፄ።“ኮሜርስ መውረድ ያለበት ኮሜርስ የሚሄድ ነው እኔ ባቡር ጣቢያ ነው የሚሄደው ስለዚህ ባቡር ጣቢያ ነው የምወርደው።ለምን አይገባችሁም?” ይባስ ተናደደች።እኔን ጨምሮ ከነበርነው ተሳፋሪዎች አንድም ደፍሮ የተናገራት የለም። ሁላችንም ፊልም የምናይ ነው የምንመስለው። እሷስትናገር እሷን፣ ሾፌሩ ሲናገሩ ሾፌሩን፣ ረዳቱ ሲናገር ረዳቱን እንመለከታለን።“የኔ እህት እዚጋ ባወርድሽ እከሰሳለሁ! ታስከስሺኛለሽ” አሉ የልጅቷ አያያዝ ያላማራቸው ሾፌር።“እኔ በወረድኩት ማን ምን አግብቶት ነው የሚከሳችሁ? የፈለኩት ቦታ የመውረድ መብት የለኝም እንዴ?” በማለትበሁኔታዋ ግራ ለተጋቡት ሾፌር ጥያቄዎችን አከታተለችባቸው።ይህንን ስትናገር ምንም እንኳን በአነጋገሯ እና ሁኔታዋ የተማረች ብትመስልም አዲስ አበባ ስትመጣ ይህ የመጀመርያዋሳይሆን እንደማይቀር፣ የተነገራትም ምልክት ባቡር ጣብያ ስትደርሺ ውረጂ ከዚያ እንዳታልፊ! የሚል ሊሆን እንደሚችል፣ሾፌሩና ረዳቱ ኮሜርስ ኮሜርስ የሚሏት ቦታም ከባቡር ጣቢያው በጣም የራቀ መስሎ የተሰማት እንዲሁም ስለ መንገድትራንስፖርት ህግ ያላት ዕውቀት ያነሰ እንደሆነ በመገመት ሽምግልና ገባሁ። ሾፌሩና ረዳቱ እሷን ለመጉዳት የተናገሩት አንዳች ነገር እንደሌለ፣ የአገላለጽ ችግር ቢኖርም ሃሳባቸው ትክክል እንደሆነ፣ኮሜርስ የሚባለው ቦታም (በታክሲው የፊት መስታወት እያሳየኋት) ቅርብ መሆኑን፣ እሷ ልውረድ የምትልበት ቦታ ለታክሲተሳፋሪን ለመጫንም ይሁን ለማውረድ በህግ የተከለከለ መሆኑን እንዲሁም አስፈላጊ ከሆነ እኔ ከሷ ጋር ወርጄ ባቡር ጣቢያእንደምመልሳት ቃል ገብቼ የረዳቱን ሸሚዝ ጨምድዶ ይዞ የነበረውን እጇን አስለቅቄ በግድ አስቀመጥኳት።አንዳንድ ጊዜ ሳስበው በስርዓተ ትምህርታችን ውስጥ መካተት እየተገባቸው ያልተካተቱ ነገር ግን በህይወት ዘመናችን የዕለትተዕለት እንቅስቃሴያችንን በብልሃትና በጥንቃቄ ለማከናወን ትልቅ ድርሻ ያላቸው ትሞህርቶች እንዳሉ ይሰማኛል።ለምሳሌም ስለ የመጓጓዣ ዓይነቶች (የአየር፣ የምድር እና የባህር) መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦቻቸውንና በአጠቃቀማቸውም ረገድሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ህግጋትና መመሪያዎችን ባማከለ መልኩ መሰረታዊ ዕውቀት ሊሰጥ የሚችል። ብዙ ጊዜ ስለትራፊክ አደጋ መከሰትና ስላስከተለው የአካል ጉድለት፣ የህይወት ጥፋትና የንብረት ውድመት በተለያዩ የመረጃ ወይም የወሬማሰራጫዎች እንሰማለን። እንዲህ ዓይነቱን መረጃ ትናንት እንሰማው ነበር ዛሬም እየሰማነው ነው። ነገስ መስማት አለብን?በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በዓመት ከ2000 በላይ የሚሆኑ ወገኖች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ያጣሉ። ከ8000 በላይየሚሆኑት ደግሞ ለከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ይዳረጋሉ። ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው ንብረት ይወድማል።የመኪና አደጋ መንስዔ ተብለው ዘወትር የሚገለጹት ምክንያቶች፡ የአሽከርካሪው የብቃት ማነስ፣ የመንገዱ ደረጃውንያልጠበቀ መሆን፣ የተሽከርካሪዎች ብልሽት እና የእግረኞች የግል ጥፋት ናቸው። የእነዚህ ምክንያቶች ቁልፉ ደግሞ የዕውቀትችግር ነው። ለአሽከርካሪው በተግባር ልምምድ የተደገፈ መሰረታዊ የማሽከርከር ዕውቀት፣ ለመንገድ ሰሪዎች እና አሰሪዎቸአግባብና ጥራት ያለው የመንገድ አሰራር ጥበብና ዕውቀት፣ ለተሽከርካሪ ባለቤቶችም ስለ ተሽከርካሪው ዋና ዋና አካላትጥቅምና ጉዳታቸው የሚያስገነዝብ ዕውቀት እንዲሁም ለእግረኞችም መሰረታዊ የሆነ የመንገድ አጠቃቀም ዕውቀትያስፈልጋቸዋል። ይህ ዓይነቱ ዕውቀት በአንድ ጀንበር የሚገኝ አይደለም። አንድ አደጋ ከተከሰተ በኋላ በባለስልጣናትበሚሰጥ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዴት ተደርጎ የህዝብን አስተሳሰብ ማጎልበት ይቻላል?ስለ መንገድ አጠቃቀም ለአሽከርካሪም ለመንገደኛም መሰረታዊ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ መጻሕፍት በግለሰቦች፣በአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲሁም በመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን በየጊዜው ይታተማሉ። ተጠቃሚውማነው ሲባል ግን መልሱ መንጃ ፍቃድ ለማውጣት የፈለገ/የፈለገች ነው። ነገር ግን እግረኞችም ሊያውቁትና ሊመሩበትይገባል። እስቲ ለአብነት ያክል በሀገራችን የመንገድ ስርዓት መሰረት በሁሉም መጻሕፍት ውስጥ የሚገኝ አንድ መመሪያእንመልከት። ለተሽከርካሪ ክፍት በሆኑ መንገዶች እግረኞች የግራ መስመራቸውን ይዘው መጓዝ እንዳለባቸው ያስቀምጣል።ታድያ ይህንን መመሪያ እግረኞች መጽሐፍቱን አንብበውና አውቀው ካልተገበሩት አሽከርካሪዎች ብቻ ስላወቁት ምን ያክልውጤታማ ሊሆን ይችላል?ህጉንና ስርዓቱን ሾፌሩ ያውቀዋል ተሳፋሪው ግን በአጋጣሚ በሰማው አሊያም በደመነፍስ ይጓዛል። ከዚያም በመግቢያችንላይ እንደተመለከትናት እህታችን እኛ ደስ ባለን ወይም በፈለግነው ቦታ ላይ አውርዱን እያልን እንጨቃጨቃለን ሌላ ጊዜደግሞ ታክሲ በማይቆምበት ቦታ ላይ ቆመን ታክሲ እንዳይቆም የሚከለክለውን ታፔላ ተደግፈን ታክሲ በመጠበቅ ጊዜእናጠፋለን። ለነገሩ አንዳንድ የታክሲ ሾፌሮችም ቢሆኑ በልምድ እንጂ በመጻሕፍቱ ላይ ያሉትን መመሪያዎች እና የመንገድዳር ምልክቶችን ትርጉም ገብቷቸው አይደለም የሚያሽከረክሩት። ምክንያቱም መጽሐፉን ያነበቡት ለፈተና ብቻ ስለሆነ። ይህ ባይሆን ኖሮ በጥቃቅን ስህተቶች የብዙ ወገኖቻችን አካል ሲጎድል፣ ህይወት ሲጠፋ እና ንብረት ሲወድም በየጊዜውባልተመለከትን ነበር።አንዳንድ አሽከርካሪዎች በአንፃሩ ዕውቀትን ከስነ ምግባር ጋር አስተባብረው የያዙና በሙያቸው ምስጉኖች አሉ። ይህ ልዩነትታድያ ለምን ተፈጠረ? ለምንድነው ሁሉን አሽከርካሪዎች አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ማርሽ ሲቀይሩ ፍሪሲዮን መርገጥ ብቻየሚሆነው? አሽከርካሪውንና ተሳፋሪውን ከአደጋ ለመከላከል ይቻል ዘንድ የደህንነት ቀበቶ አድርግ እየተባለ የሚገደድ እናበዚህም ምክንያት የሚቀጣ አሽከርካሪ ከየት መጣ? የትራፊክ ፖሊስን ካላየ በቀር የትራፊክ ህግን የማያክብር አሽከርካሪንማነው የላከብን? በታክሲው ውስጥ “ፍቅር ካለ ታክሲም ባስ ይሆናል” የሚል ጽሑፍ ለጥፎ የታክሲንና የአንበሳ ባስንየተሳፋሪ ቁጥር ልዩነት ለማጥበብ የሚጥር አሽከርካሪ ከየት ተፈጠረ? ቢያንስ ቢያንስ የመንገድ አጠቃቀም ህጉን ከእግረኛውይልቅ እኔ በተሻለ አውቀዋለሁ በማለት በእግረኛ ማቋረጫ ላይ ለእግረኞች ቅድሚያ በመስጠት ፋንታ ማቋረጫውን እንደንቅሳት የሚቆጥሩት፣ ትምህርት ቤቶች ባሉባቸውና ህዝብ በሚበዛባቸው መንገዶች ላይ ውድድር የሚያምራቸውና ደቂቃየማትሞላ ትዕግስት በማጣት ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለሀገራቸው የሚሆን ታላቅ ዓላማ የነበራቸውወገኖቻችንን በወጡበት ያስቀሩብንን አሽከርካሪዎች ፈትቶ የለቀቀብን ማነው?የአሽከርካሪዎችን ያክል ራሳቸው ተጎድተው ለሌሎች ጉዳትና ለንብረት ጥፋትም መንስዔ የሚሆኑ እግረኞችም አሉ። መቼምየእሳትን መፋጀት ያወቅነው ሁላችንም አንድ አንድ ጊዜ ተቃጥለን አይደለም። እሳት ያቃጥላል ተባልን እኛም አመንንራሳችንንም ከእሳት እንጠብቃለን። ራሳችንንም ከትራፊክ አደጋ ለመከላከል የግድ አስቀድመን አንድ አንድ ጊዜ መገጨትአይጠበቅብንም። መኪና ሰው ሊገጭ እንደሚችል፣ ገጭቶም አካል ሊያጎድል ከዚያም ሲያልፍ ሊገድል እንደሚችል ለማወቅየግድ መንጃ ፈቃድ ሊኖረን አይገባም። ይህንን ለማወቅ እና ለማገናዘብ ሰው መሆናችን ብቻ ከበቂ በላይ ነው። ምክንያቱምአንዳንድ እንሰሳት እንኳን መንገድ ላይ ሆነው መኪና ሲመጣባቸው እንዴት አንደሚሸሹ እናያለን። በኣርአያ ስላሴየተፈጠረው ሰው ታድያ ከእንሰሳቱ በተሻለ እንዴት አያገናዝብ ለዛውም ለገዛ ህይወቱ።አንዳንድ ጊዜ ግን ከእንሰሳቱ አንሰን እንታያለን። ለአንድ አቅጣጫ ብቻ እንዲያገለግሉ ታስበው የተሰሩ ነገር ግን በሁለቱምአቅጣጫዎች ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች የሚያገለግሉ አንዳንድ መንገዶች አሉ። በእነዚህ መንገዶች በተለይ ከሁለቱምአቅጣጫ መኪኖች ሲመጡ ፍጥነታቸውን ቀንሰው በጥንቃቄ ነው የሚተላለፉት። በእንደእነዚህ ዓይነት መንገዶች ላይ ያለመንገደኛ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ሊወስድ እንደሚገባው መቼም ሌላ አካል እንዲነግረው አይጠበቅም። አስፋልቱን ለመኪኖቹትቶ ሊጓዝ እየተገባው መሐላ ያለበት ይመስል አስፋልቱን ላለመልቀቅ ሲታገል ጉዳት ቢደርስበት መኪናው ገጨኝ ነውወይስ ገጨሁት ወይስ ደግሞ ተገጫጨን ሊል የሚገባው? መኪና ሰውን ሊገጭ እንዲሁም ሊገድል እንደሚችል ያላመነወይም የተጠራጠረ የሚመስል ሰው አጋጥሟችሁ አያውቅም?የአንዳንዶቹማ እኮ አያድርስ ነው። ዕቃ ተሸክመው፣ ህፃናትን ይዘው፣ በተንቀሳቃሽ ስልክ እየተነጋገሩ፣ ተቃቅፈው፣ እጅለእጅ ተያይዘው፣ ሦስት አራት ሆነው ሞቅ ያለ ጨዋታ ይዘው በጠባብ መንገድ ላይ የሚጓዙቱ ወይ ዳር አይወጡ ወይደግሞ ታርጋ አያወጡ ምን ሊባሉ ይሆን? እንደ ፀረ 6 ፀረ መኪና ተከትበው ይሆን እንዴ? በዜብራ ላይ መሻገርላለመገጨት እንደዋስትና የሚቆጥሩና ያለምንም ጥንቃቄ በደመነብስ ለመሻገር የሚሞክሩም እኮ አሉን።“ከስህተቱ የማይማር ፈንጂ አምካኝ ብቻ ነው” የሚል ፅሑፍ ታክሲ ውስጥ ማንበቤ ትዝ ይለኛል። ይህንን ፅሑፍ ብዙምአልስማማበትም። ምክንያቱም ግራ እና ቀኝ ሳይመለከት፣ የእግረኛ ማቋረጫን ሳይጠቀም እና አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሳያደርግ መንገድ አቋርጣለሁ ሲል ከፍተኛ አደጋ የደረሰበት ሰው እንዴት ብሎ ነው ከስህተቱ የሚማረው? በስህተቴ ተፀፅቻለሁ ብሎጉዳቱን undo ማለት ይችላል እንዴ?እንደ እኔ አመለካከት ግን አብዛኛው አሽከርካሪ እና እግረኛ መሰረታዊ የሆነ የመንገድ ትራንስፖርት አጠቃቀም ግንዛቤይጎድለዋል። ይህንን ዓይነት የግንዛቤ እጥረት እስከ ወዲያኛው ለማስወገድ ደግሞ በትምህርት ቤት ውስጥ እንደ ሌሎችየትምህርት ዓይነቶች በመደበኛነት ትምህርቱን መስጠትን የመሰለ ምን አማራጭ ይኖራል? ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ለየክፍልደረጃው የተማሪዎቹን የማገናዘብ አቅም ባማከለ መልኩ ስለ የመጓጓዣ ዓይነቶች፣ ስለ መኪና ምንነት፣ ዓይነት፣ አሰራሩ፣አጠቃቀሙ፣ አገዛዙ፣ አሻሻጡ፣ የሞተር ዓይነቶች ከነመመዘኛቸው፣ የጎማ ዓይነት እስከነመስፈርቱ፣ ከእያንዳንዱ የመጓጓዣዓይነት ጀርባ ያለው የምህንድስና ጽንሰ ሀሳብ፣ የመንገድ አጠቃቀም መመሪያዎች ወዘተ በቂ መረጃ ሊያስጨብጥ የሚችልየትምህርት ዓይነት ቢኖረን ምን አለበት?እንዲህ ዓይነቱ ትምህርት ከታች ጀምሮ ቢሰጥ የተማሪዎችን ወደ ተለያዩ የምህንድስና ሙያዎች እንዲሳቡና ጥሩ የሆነዝንባሌ እንዲኖራቸው በማድረጉ ረገድም ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል። 10ኛ ክፍልን ካጠናቀቁ በኋላ በተለያዩ የቴክኒክና ሙያማሰልጠኛ ተቋማት ለሚገቡት ተማሪዎችም ይህንን መሰረታዊ ዕውቀት ይዞ መግባት ምን ያህል ውጤታማ ሊያደርጋችወናየተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን ለመስራት አንደሚረዳቸው መቼም ግልጽ ነው።እኅቶች እና ወንድሞች ታድያ ይህንን ትምህርት በስርዓተ ትምህርታችን ውስጥ ተካቶ ልንማረው አይገባም ትላላችሁ?ቸር ያሰማን።


Type:Social
👁 :1
Maktub Paulo Coelho Dedicated to Nha Chica PART4
Catagory:Fiction
Auter:
Posted Date:08/19/2024
Posted By:utopia online

There, the small river becomes a mighty current, and is split into dozens of waterfalls. The wanderer is walking through the area, hearing the music of the waters. Suddenly, a grotto -behind one of the cataracts -captures his attention. He studies the rocks, worn by time, and regards the lovely forms created patiently by nature. And he finds a verse by R. Tagore inscribed on a plaque: “It was not a hammer that made these rocks so perfect, but water -with its sweetness, its dance and its song.” Where force can only destroy, gentleness can sculpt. The master says: “Many people are fearful of happiness. For such persons, to be content in life means they must change a number of their habits -and lose their sense of identity. Often we become indignant at the good things that befall us. We do not accept them, because to do so causes us to feel that we are in God's debt. We think: 'Better not to drink from the chalice of happiness, because, when it is empty, we will suffer greatly. ' Out of a fear of shrinking, we fail to grow. Out of a fear of weeping, we fail to laugh.” One afternoon at the monastery at Sceta, one of the monks offended another. The superior of the monastery, Brother Sisois, asked that the offended monk forgive his aggressor. “I cannot do that,” responded the monk. “It was he that did this, and it he who must pay.” At that very moment, Brother Sisois raised his arms to heaven and began to pray: “My Jesus, we no longer have need of thee. We are now capable of making the aggressor pay for his offenses. We are now able to take vengeance into our own hands, and to deal with Good and Evil. Therefore, You can leave us on our own, and their will be no problem.” Ashamed, the monk immediately pardoned his brother. A disciple said, “All masters say that spiritual treasure is discovered through solitary search. So, then, why are we all together here?” “You are together because a forest is always stronger than a solitary tree,” the master answered. “The forest conserves humidity, resists the hurricane and helps the soil to be fertile. But what makes a tree strong is its roots. And the roots of a plant cannot help another plant to grow. To be joined together in the same purpose is to allow each person to grow in his own fashion, and that is the path of those who wish to commune with God.” When the wanderer was ten years old, his mother insisted that he take a course in physical education. One of the activities required him to jump from a bridge into a river. Early in the course, he was paralyzed by fear. Each day, he stood last in line, and suffered every time one of those in front made his jump -because it would shortly be his turn. One day, the instructor -noticing his fear -made him take the first jump. Although he was still frightened, it was over so quickly that the fright was replaced by courage. The master says: “Often, we can afford to take our time. But there are occasions when we must roll up our sleeves and resolve a situation. In such cases, there is nothing worse than delay.” Buddha was seated among his disciples one morning when a man approached the gathering. “Does God exist,” he asked. “Yes, God exists,” Buddha answered. After lunch, another man appeared. “Does God exist?” he asked. “No, God does not exist,” Buddha answered. Late in the day, a third man asked Buddha the same question, and Buddha's response was: “You must decide for yourself.” “Master, this is absurd,” said one of the disciples. “How can you give three different answers to the same question?” “Because they were different persons,” answered the Enlightened One. “And each person approaches God in his own way: some with certainty, some with denial and some with doubt.” We are all concerned with taking action, doing things, resolving problems, providing for others. We are always trying to plan something, conclude something else, discover a third. There is nothing wrong with that -after all, that is how we build and modify the world. But the act of Adoration is also a part of life. To stop from time to time, to escape one's self, and to stand silent before the Universe. To kneel down, body and soul. Without asking for something, without thinking, without even giving thanks for anything. Just to experience the warmth of the love that surrounds us. At such moments, unexpected tears may appear -tears neither of happiness nor sadness. Do not be surprised at that. It is a gift. The tears are cleansing your soul. The master says: “If you must cry, cry like a child. You were once a child, and one of the first things you learned in life was to cry, because crying is a part of life. Never forget that you are free, and that to show your emotions is not shameful. Scream, sob loudly, make as much noise as you like. Because that is how children cry, and they know the fastest way to put their hearts at ease. “Have you ever noticed how children stop crying? They stop because something distracts them. Something calls them to the next adventure. Children stop crying very quickly. And that's how it will be for you. But only if you can cry as children do.” The wanderer is having lunch with a woman friend, an attorney inFort Lauderdale . A highly animated drunk at the next table insists on talking to her throughout the meal. At one point, the friend asks the drunk to quiet down. But he says: “Why? I'm talking about love in a way that a sober person never does. I'm happy, I'm trying to communicate with strangers. What's wrong with that?” “This isn't the appropriate time,” she said. “You mean there are only certain times that are appropriate for showing one's happiness?” With that, the drunk is invited to share her table. The master says: “We must care for our body. It is the temple of the Holy Spirit, and deserves our respect and affection. We must make the best use of our time. We must fight for our dreams, and concentrate our efforts to that end. But we must not forget that life is made up of small pleasures. They were placed here to encourage us, assist us in our search, and provide moments of surcease from our daily battles. It is not a sin to be happy. There is nothing wrong in -from time to time -breaking certain rules regarding diet, sleep and happiness. Do not criticize yourself if -once in a while -you waste your time on trifles. These are the small pleasures that stimulate us.” The pianist Artur Rubinstein was late arriving for lunch at a first class restaurant inNew York . His friends began to be concerned, but Rubinstein finally appeared, with a spectacular blonde, one-third his age, at his side. Known to be something of a cheapskate, he surprised his friends by ordering the most expensive entree, and the rarest, most sophisticated wine. When lunch was over, he paid the bill with a smile. “I can see that you are all surprised,” Rubinstein said. “But today, I went to my lawyer's to prepare my will. I left a goodly amount to my daughter and to my relatives, and made generous donations to charities. But I suddenly realized that I wasn't included in the will; everything went to others. So, I decided to treat myself with greater generosity.” While the master was traveling to spread the word of God, the house in which he lived with his disciples burned down. “He entrusted the house to us, and we didn't take proper care,” said one of the disciples. They immediately began to rebuild on what remained after the fire, but the master returned earlier than expected, and saw what they were doing. “So, things are looking up: a new house,” he said happily. One of the disciples, embarrassed, told him what had actually happened; that where they had all lived together had been consumed by fire. “I don't understand,” said the master. “What I am seeing is men who have faith in life, beginning a new chapter. Those who have lost everything they owned are in a better position than many others, because, from that moment on, things can only improve.” The master says: “If you are traveling the road of your dreams, be committed to it. Do not leave an open door to be used as an excuse such as, 'Well, this isn't exactly what I wanted. ' Therein are contained the seeds of defeat. “Walk your path. Even if your steps have to be uncertain,


Type:Social
👁 :
ዩክሬን በኩርስክ የኒውክሌር ማዕከል ላይ ጥቃት ከፈጸመች ከባድ አጸፋዊ ምላሽ ይጠብቃታል – ሩሲያ
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/19/2024
Posted By:utopia online

ዩክሬን በኩርስክ የኒውክሌር ሃይል ማመንጫ ማዕከል ላይ ጥቃት ከሰነዘረች የሩሲያ ጦር አፋጣኝ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስጠንቅቋል። ዩክሬን ከቀናት በፊት ወደሩሲያ ግዛት ዘልቃ በመግባት ጥቃት እያደረሰች መሆኗን እና በኩርስክ ግዛትም ድል እየቀናት መሆኑን ገልጻለች፡፡ ይህን ተከትሎም ዩክሬን እና ሩሲያ በግዙፉ ዛፖሪዝዝሂያ የኒውክሌር ሃይል ማመንጫ ማዕከል ላይ ተነስቶ በነበረው የእሳት አደጋ ምክንያት እርስ በርስ ተወነጃጅለው እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህም የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ፥ በሩሲያ ከሁለት ዓመት በላይ ሲተዳደር የነበረው የኒውክሌር ሃይል ማመንጫ ማዕከል እሳት እንዲነሳ ምክንያቷ ራሷ ሞስኮ ናት ሲሉ ወንጅለዋል፡፡ በአንጻሩ ሩሲያ የኒውክሌር ማዕከሉ በእሳት እንዲያያዝ ያደረገችው ዩክሬን ናት ስትል መወንጀሏየሚታወስ ነው፡፡ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ÷ በሁለቱ ሀገራት መካከል እየከረረ በመጣው ጦርነት የኩርስክን የኒውክሌር ጣቢያ ለማጥቃት ዩክሬን አቅዳለች ብሏል፡፡ በዚህም ዩክሬን የኒውክሌር ማዕከሉን ለማጥቃት ካሰበች ከባድ አጸፋዊ ምላሽ ይጠብቃታል ሲል ማስጠንቀቁን አርቲ ዘግቧል፡፡ ዩክሬን እያደረገች ያለው ትንኮሳም ሩሲያን ተጠያቂ ለማድረግ በማሰብ መሆኑን ሚኒስቴሩ አጽንኦት ሰጥቷል፡፡ የኒውክሌር ጣቢያው ላይ ጥቃት ከተፈጸመ የጨረር ልቀትና የኒውክሌር አደጋ በመላው አውሮፓ ሊከሰት እንደሚችል ተመላክቷ


Type:Social
👁 :
ዩክሬን ወደ ሩሲያ ድንበር ያደረገችው ግስጋሴ ዋሺንግተን ያልጠበቀችው እንደነበር ተመላከተ
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/19/2024
Posted By:utopia online

ዩክሬን በሩሲያ ኩርስክ ግዛት ላይ ያደረሰችው ጥቃት በአካባቢው ያሳደረውን ተፅዕኖ እና የፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪን ድፍረት የተሞላበት እርምጃ በአሜሪካ ያልተጠበቀ መሆኑ ተነገረ። የዩክሬን የሩሲያን ድንበር አልፋ በብዙ ኪሎሜትሮች መዝለቋን ዋሽንግተን በግርምት እየተመለከተችው መሆኑ ተመላክቷል። የአሜሪካ ባለስልጣናት ይህ ድንገተኛ ጥቃት ፖለቲካዊና ወታደራዊ እንቅስቃሴን እንዴት እንደተለወጠና ዩክሬን በአሜሪካ የቀረቡላትን የጦር መሣሪያዎች አጠቃቀም ላይ ዋሺንግተን የተጫወተችውን ሚና በተመለከተ እየገመገሙ ነው። ድንገተኛ ወረራው ሩሲያንም ሆነ ምዕራባውያን መሪዎችን ያስደመመ ሲሆን÷ ዩክሬንን ለመጠበቅ ለተሰለፈው ምዕራባውያን ሰራሽ መከላከያም ከከፍተኛ ስኬቶቹ አንዱ እንደሆነለት ተገልጿል፡፡ ፕሬዚዳንት ባይደን የአሜሪካ እና ሞስኮን ፍጥጫ በማያባብስ መልኩ ዩክሬን ሩሲያን ከወረረቻቸው አካባቢዎች እንድታስወጣ አቅም ለመፍጠር በተደጋጋሚ ሞክረዋል። ፕሬዚዳንት ፑቲን በተደጋጋሚ ግጭቱን በሩሲያ እና በምዕራባውያን መካከል የተፈጠረ ጦርነት አድርገው ለመግለጽ ይሞከሩ እንደነበር ተገልጿል፡፡ ፕሬዚዳንት ባይደን በበኩላቸው ይህንን አመለካከት ለማጥፋት በአሜሪካ ፖሊሲ ላይ ግልጽ ገደብ ለማበጀት ጥረት ማድረጋቸው ተነግሯል። ወታደራዊ ተንታኞች እንደሚሉት ዩክሬን በኩርስክ ግዛት ያደረሰችው ጥቃት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በሩሲያ ላይ በውጭ ሀገር ወታደሮች የደረሰ ትልቁ ጥቃት በመሆኑ በነጩ ቤተመንግስት ጥያቄ ማጫሩን ቢቢሲ ዘግቧል።


Type:Social
👁 :
ሁሉን አቀፍ የባንክ አሰራርን ተደራሽ ማድረግ ኢንቨስትመንትን እንደሚያበረታታ ተመላከተ
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/20/2024
Posted By:utopia online

5ኛው ዓለም አቀፍ ወለድ አልባ የባንክ አሰራርና ታካፉል ዋስትና ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሀመድ በዚህ ወቅት÷ከወለድ ነፃ የሆነ የባንክ አገልግሎት የሙስሊሙን ማህበረሰብ ፍላጎት ከማርካት በተጨማሪ የአምራች ኢንዱስትሪውን ኢንቨስትመንት እንደሚያበረታታ ገልጸዋል፡፡ ከወለድ ነፃ የሆነ የባንከ ስርዓት መዘርጋት መንግስት ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተገበረ ካላቸው ተግባራት አንዱ መገለጫ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡ ስለሆነም መንግስት የሙስሊሙን ማህበረሰብ ፍላጎት መሰረት በማድረግ ከዓለም አቀፍ ኢስላማዊ የባንክና ኢኮኖሚ ማዕከል አልሁዳ ጋር በትብብር መስራቱን ይቀጥላል ማለታቸውን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡


Type:Social

Page 10 of 75