Entertailment Page

Entertailment






👁 :
በጋምቤላ ክልል የባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ እየተካሄደ ነው
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/02/2024
Posted By:utopia online

በጋምቤላ ክልል የባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ እየተካሄደ ነው። የባለድርሻ አካላቱ የፖለቲካ ፓርቲ፣ ሶስቱ የመንግስት አካላት፣ ማህበራትና ተቋማት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተመረጡ 60 ተወካዮች ናቸው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም እንደተናገሩት÷ ከባለድርሻ አካላት የምክክር ምዕራፍ ለክልሉም ሆነ ለሀገር የሚጠቅሙ እንዲሁም መግባባት ላይ የሚያደርሱ ሀሳቦችና አጀንዳዎች ይጠበቃሉ። ተወካዮቹ በአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ ሂደቱ ላይ ጥሩ አስተዋጽኦ ለማድረግና መግባባት ላይ ለመድረስ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል። ሰላምን በማረጋገጥ ልማትን በማምጣት ለትውልድ የሚሻገር ስራ ለመስራት በዚህ የምክክር ምዕራፍ የሚዋጣው ሀሳብ ወሳኝነት እንዳለውም አስገንዝበዋል። ምክክሩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን÷ ባለድርሻዎች አጀንዳዎቻቸውን ለይተውና አደራጅተው ለኮሚሽኑ ያስረክባሉ ተብሎ ይጠበቃል።


Type:Social
👁 :
በሕንድ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 93 ደረሰ
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/02/2024
Posted By:utopia online

በሕንድ ደቡባዊ ግዛት ኬራላ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 93 ሲደርስ ፤ ብዙዎች ከመሬት ስር ተቀብረው ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል፡፡ እየተከናወነ ያለውን የነፍስ አድን ሥራም ከባድ ዝናብና የድልድይ መደርመስ እያስተጓጎለው መሆኑን ተከትሎ አደጋው በተከሰተበት ሥፍራ ያሉ ዜጎችን ለማውጣት አዳጋች እንዳደረገው ተሰምቷል፡፡ በዚህም አደጋ የሟቾች ቁጥር ያሻቅባል የሚል ስጋት እንዳለ የተገለጸ ሲሆን፥ ይህም በአካባቢው በፈረንጆቹ 2018 ከደረሰው ከባድ የጎርፍ አደጋ በኋላ አስከፊው ነው ተብሏል፡፡ የነፍስ አድን ሥራ ለመስራትም ከ200 በላይ የሠራዊት አባላት መሰማራታቸውም ነው የተጠቆመው፡፡ የሀገሪቱ አንድ ባለስልጣን በሰጡት መግለጫም፥ የደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ መላውን አካባቢ ጠራርጎ ወስዶታል ብለዋል፡፡ በአካባቢው ባሉ ሆስፒታሎችም ቢያንስ 123 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፥ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከአካባቢው እንዲለቁ በማድረግ ወደ 45 የእርዳታ ካምፖች መግባቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡ ከክስተቱ በኋላ በተደረገ አሰሳም የ16 ሰዎች አስከሬን በወንዝ ውስጥ መገኘቱ የአደጋውን አስከፊነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ግዛቲቱ በተለይ በክረምት ወራት ለመሬት መንሸራተት አደጋ የተጋለጠች መሆኗም ይገለጻል፡፡


Type:News
👁 :
ኢትዮጵያ በተለያዩ ርቀቶች የምትሳተፍበት የማጣሪያ ውድድሮች ዛሬ ይደረጋሉ
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/02/2024
Posted By:utopia online

በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች የሚሳተፉባቸው የማጣሪያ ውድድሮች ዛሬ ይደረጋሉ። በዚሁ መሠረት ቀን 6 ሠዓት ከ5 ላይ በ1 ሺህ 500 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ አትሌት ሳሙኤል ተፈራ፣ ኤርሚያስ ግርማ እና አብዲሳ ፈይሳ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡ እንዲሁም ምሽት 1 ሠዓት ከ10 ላይ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ መዲና ኢሳ እና እጅጋየሁ ታዬ ይሳተፋሉ። በሌላ መርሐ-ግብር ደግሞ ምሽት 2 ሠዓት ከ45 ላይ በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ፅጌ ዱጉማ፣ ሀብታም ዓለሙ እና ወርቅነሽ መለሰ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ።


Type:Social
👁 :
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ ከግብፅ አምባሳደር ጋር ተወያዩ
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/07/2024
Posted By:utopia online

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ ከግብፅ አምባሳደር መሀመድ ኦማር ጋድ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸው ÷በሁለትዮሽ፣ቀጠናዊ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ ሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸውና በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ እንዲሁም አልሸባብ በሶማሊያና በቀጣናው ባሳድረዉ ስጋት ላይም ምክክር ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ውይይቱ በድህረ-አትሚስ ተልዕኮ እና በኢትዮጵያ ፍላጎቶች ላይ ያተኮረ እንደነበር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡


Type:Social
👁 :
ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት የ3 ሺህ ሜትር የወንዶች መሰናክል ፍጻሜ ዛሬ ይካሄዳል
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/07/2024
Posted By:utopia online

በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ የዛሬ መርሐ-ግብሮች ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የፍጻሜ እና የማጣሪያ ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡ በዚሁ መሠረት ምሽት 4 ሠዓት ከ43 ላይ በሚካሄደው 3 ሺህ ሜትር የወንዶች የፍጻሜ ውድድር÷ አትሌት ለሜቻ ግርማ፣ ሳሙኤል ፍሬው እና ጌትነት ዋለ ይሳተፋሉ፡፡ እንዲሁም ቀን 6 ሠዓት ከ10 ላይ በሚካሄደው 5 ሺህ ሜትር የወንዶች ማጣሪያ አትሌት ሐጎስ ገብረ ሕይወት፣ ቢንያም መሐሪ እና አዲሱ ይሁኔ ተሳታፊ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል እንዲሁም ትናንት በተካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ከምድቧ ያላለፈችው አትሌት ብርቄ ሓየሎም ዛሬ ቀን 7 ከ45 ላይ በድጋሚ በማጣሪያው የምትወዳደር ይሆናል፡፡ በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምክ ኢትዮጵያ እስከ አሁን ሁለት የብር ሜዳሊዎችን በመያዝ 52ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ አሜሪካ፣ ቻይና፣ አውስትራሊያ እና ፈረንሳይ በቅደም ተከተል ከ 1 እስከ 4 ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡


Type:News
👁 :
ሩሲያና ኢራን በሁለትዮሽና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/07/2024
Posted By:utopia online

በትናንትናው ዕለት ኢራን ቴህራን የገቡት የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፀሃፊ ሰርጌይ ሾይጉ በተለያዩ የሁለትዮሽ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ከቴህራን ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ሾይጉ የእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጓድ ከፍተኛ አዛዥ እና የኢራን ከፍተኛ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፀሃፊ ከሆኑት ሪር አድሚራል አሊ አክባር አሕመድ ጋር ተገናኝተው መክረዋል ነው የተባለው። በተጨማሪም ሾይጉ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን እና የኢራን ወታደራዊ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም መሀመድ ባገሪ ጋርም ተገናኝተው መክረዋል ተብሏል። በዚህም “ሩሲያ በአስቸጋሪ ጊዜያት ከኢራን ህዝብ ጎን ከቆሙት ሀገራት መካከል አንዷ ናት” ሲሉ ፔዜሽኪያን ማመስገናቸውን ጠቅሶ የዘገበው ሬውተርስ ነው፡፡ አክለውም፥ በኢራን እና በሩሲያ መካከል ያለው የጋራ አቋም ብዝሃ-ሃይልን በማስተዋወቅ ወደ የላቀ ዓለም አቀፍ ደህንነት እና ሰላም ያመራል ብለዋል፡፡ አፍሪካ ኒውስ በበኩሉ ባወጣው ዘገባ፤ የሰርጌይ ሾይጉ ጉብኝት ኢራንና እስራኤል ውጥረት ውስጥ በገቡበት ወቅት መሆኑን አንስቶ፤ አሜሪካና አጋሮቿ በቀጣናው እየተካረረ የመጣውን ቀጣናዊ ቀውስ መፍትሄ ለማበጀት እየመከሩ እንደሆነ ጠቅሷል።


Type:Social
👁 :
ሂዝቦላህ በእስራኤል ላይ በሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መፈፀሙን ገለጸ
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/07/2024
Posted By:utopia online

የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላህ ወደ ሰሜናዊ እስራኤል ተከታታይ የሰው አልባ አውሮፕላን እና የሮኬት ጥቃቶችን መፈፀሙን ገለጸ፡፡ እስራኤል ባለፈው ሳምንት የቡድኑን ከፍተኛ አዛዥ መግደሏን ተከትሎ እየተጠበቀ ያለው የበቀል እርምጃ ገና ይቀጥላል ሲልም አስጠንቅቋል። ሄዝቦላህ በሰሜን እስራኤል በአክሬ አቅራቢያ የሚገኙ ሁለት የጦር ሰፈሮችን በሰው አልባ አውሮፕላኖች ማጥቃት መጀመሩን እና በሌላ ቦታ በእስራኤል ወታደራዊ ተሸከርካሪ ላይ ጥቃት መሰንዘሩንም ተናግሯል። የእስራኤል ጦር በበኩሉ ከሊባኖስ የተወነጨፉ በርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መለየታቸውን እና አንደኛው መክሸፉን አስታውቋል። የህክምና ባለስልጣናትም ጉዳት የደረሰባቸው ሰባት ሰዎች ከአካባቢው ለቀው በደቡባዊ ድንበር ከተማ ናሃሪያ ወደ ሚገኝ ሆስፒታል መወሰዳቸውን፤ አንዱም አስጊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የእስራኤል ጦር እንደገለጸው በርካታ ንጹሃንን ያቆሰለው አደጋ የደረሰው ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለመምታት የተወነጨፈ ተተኳሽ ኢላማውን ስቶ መሬት በመውደቁ ነው፡፡ ይሁንና ክስተቱ አሁንም በምርመራ ላይ እንደሚገኝ አመላክቷል፡፡ የእስራኤል ጦር በሰጠው መግለጫ በአክሬ አካባቢ የማንቂያ ደወል ድምፅ እንደተሰማና ነገር ግን ያ የውሸት ማንቂያ ሆኖ መገኘቱን ገልጿል፡፡ የአየር ኃይሉ በደቡብ ሊባኖስ ሁለት የሂዝቦላ ተቋማትን መምታቱንም ተናግሯል። የሂዝቦላህ አዛዥ ፉአድ ሹክር እና ባለፈው ሳምንት በቴህራን ለተገደለው የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ መሪ ኢስማኤል ሃኒዬህ አጸፋ እንደሚመልሱ ሂዝቦላህና ኢራን ዛቻ መሰንዘራቸውን ተከትሎ መካከለኛው ምስራቅ ወደ ሙሉ ጦርነት ሊገባ ይችላል የሚል ስጋት እየጨመረ መጥቷል። ለኮማንደር ፉአድ ሹክር ግድያ የሚሰጠው ምላሽ ገና አልተጀመረም ሲሉ አንድ የሂዝቦላህ ምንጭ መናገራቸውን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡


Type:Social
👁 :
ኢትዮጵያ በየትኛቹ ኦሊምፒኮች ተሳተፈች?
Catagory:Reading
Auter:
Posted Date:08/07/2024
Posted By:utopia online

ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ በኦሊምፒክ እየተሳተፈች የምትገኘው ኢትዮጵያ በታሪኳ በኦሊምፒክ መሳተፍ የጀመረችው ኦሊምፒክ ከተጀመረ ከ60 ዓመታት በኋላ አውስትራሊያ ባስተናገደችው 16ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ነው፡፡ በግሪክ አስተናጋጅነት በፈረንጆቹ 1986 የጀመረው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ውድድር አውስትራሊያ፣ ኦስትሪያ፣ ቡልጋሪያ፣ ቺሊ፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ በወቅቱ አጠራር ታላቋ ብሪታንያ (አየርላንድን ጨምሮ)፣ ግሪክ፣ ሀንጋሪ፣ ጣልያን፣ ስዊድን፣ ስዊዘርላንድና አሜሪካ ተሳትፈውበታል። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ተሳትፎዋ በማራቶን፣ ዱላ ቅብብል እና ብስክሌት ስፖርቶች ተካፍላ ሜዳሊያ ባለማግኘቷ ደረጃ ውስጥ ሳትገባ ቀርታለች፡፡ ሁለተኛ ተሳትፎዋ በሆነው በፈረንጆቹ 1960 ጣልያን ባስተናገደችው 17ኛው ኦሊምፒክም በአትሌቲክስና ብስክሌት የስፖርት ዓይነቶች ተሳትፋ፤ አትሌት አበበ ቢቂላ ባስገኘው የወርቅ ሜዳሊያ 21ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቃለች። ጃፓን በፈረንጆቹ 1964 ባሰናዳችው 18ኛው ኦሊምፒክ በአትሌቲክስ፣ ቦክስና ብስክሌት ስፖርቶች የተሳተፈችው ኢትዮጵያ÷ በአትሌት አበበ ቢቂላ የወርቅ ሜዳሊያ 24ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች። 19ኛው ኦሊምፒክ በፈረንጆቹ 1968 በሜክሲኮ ሲካሄድ በአትሌቲክስ፣ ቦክስና ብስክሌት የስፖርት ዓይነቶች ተሳትፋ÷ አትሌት ማሞ ወልዴ በማራቶን ወርቅ፣ በ10 ሺህ ሜትር ደግሞ ብር ሜዳሊያ በማምጣቱ 25ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡ ጀርመን በፈረንጆቹ 1972 ባስተናገደችው 20ኛው የኦሊምፒክ ውድድር በአትሌቲክስ፣ ቦክስ እና ብስክሌት ተሳትፋ÷ አትሌት ማሞ ወልዴ በማራቶን እንዲሁም ምሩጽ ይፍጠር በ10 ሺህ ሜትር ባመጡት የነሐስ ሜዳሊያ ኢትዮጵያ 41ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች። በፈረንጆቹ 1980 ሩሲያ ባስተናገደችው 22ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ደግሞ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ፣ ቦክስና ብስክሌት ስፖርቶች ተሳትፋ÷ ማርሽ ቀያሪው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር በ5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አስገኝቶላታል፡፡ በፈረንጆቹ 1992 ስፔን ባዘጋጀችው 25ኛው የኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ እና ብስክሌት ተካፍላ÷ በአትሌት ደራርቱ ቱሉ 10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ፣ አዲስ አበበ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች እና ፊጣ ባይሳ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች የነሐስ ሜዳሊያዎች በማግኘት 33ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች። እንዲሁም 26ኛው የኦሊምፒክ ውድድር በአሜሪካ ሲካሄድ በአትሌቲክስና ቦክስ ስፖርቶች የተሳተፈችው ኢትዮጵያ በአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ፣ ፋጡማ ሮባ በማራቶን ወርቅ፣ ጌጤ ዋሚ በ10 ሺህ ሜትር ነሐስ ሜዳሊያዎችን አግኝታ 34ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። አውስትራሊያ ያዘጋጀችው 27ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በፈረንጆቹ 2000 ሲካሄድ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስና ቦክስ ተሳትፋ ደማቅ ታሪክ ማስመዝገቧ ይታወቃል፡፡ በዚህ ኦሊምፒክ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ፣ ደራርቱ ቱሉ በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ፣ ሚሊዮን ወልዴ በ5 ሺህ ሜትር ወርቅ፣ ገዛኸኝ አበራ በማራቶን ወርቅ፣ ጌጤ ዋሚ በ10 ሺህ ሜትር ብርና በ5 ሺህ ሜትር ነሐስ፣ አሰፋ መዝገቡ በ10 ሺህ ሜትር እና ተስፋዬ ቶላ በወንዶች ማራቶን በተመሳሳይ የነሐስ ሜዳሊያዎችን አግኝተው ኢትዮጵያ በውድድሩ 8 ሜዳሊያዎችን በማግኘት 20ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች። ግሪክ በፈረንጆቹ 2004 ባስተናገደችው 28ኛው ኦሊምፒክም ኢትዮጵያ በአትሌቲክስና ቦክስ ተሳትፋ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ እና በ5 ሺህ ሜትር ብር፣ መሰረት ደፋር በ5ሺህ ወርቅ፣ በ10 ሺህ ሜትር እጅጋየሁ ዲባባ የብር፣ ስለሺ ስኅን በ10 ሺህ ብር፣ አትሌት ደራርቱ ቱሉና ጥሩነሽ ዲባባ ነሐስ ሜዳሊያ አግኝተው በ7 ሜዳሊያዎች 28ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቅ ችላለች፡፡ 29ኛውን የኦሊምፒክ ውድድር በ2008 ቻይና ባስተናገደችበት ወቅትም በአትሌቲክስ ስፖርት ብቻ የተሳተፈችው ኢትዮጵያ በአትሌት ቀነኒሳ በቀለና ጥሩነሽ ዲባባ በ5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር ወርቅ፣ ስለሺ ስኅን በ10 ሺህ ሜትር ብር እና መሰረት ደፋር ብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከ204 ሀገራት 18ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡ በ2012 ብሪታንያ 30ኛውን ኦሊምፒክ ስታዘጋጅ 12ኛ ተሳትፎዋን ያደረገችው ኢትዮጵያ በአትሌቲክስና ውኃ ዋና ስፖርቶች ተካፍላ በአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ እና በ5 ሺህ ሜትር ነሐስ፣ መሰረት ደፋር 5 ሺህ ሜትር ወርቅ፣ ቲኪ ገላና በማራቶን ወርቅ፣ ደጀን ገብረ መስቀል በ5 ሺህ ሜትር ብር፣ ሶፊያ አሰፋ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ብር፣ ታሪኩ በቀለ በ10 ሺህ ሜትር እና አበባ አረጋዊ በ1 ሺህ 500 ሜትር ነሐስ ሜዳሊያዎችን አግኝተው ኢትዮጵያ በ8 ሜዳሊያዎች 24ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡ በፈረንጆቹ 2016 በብራዚል በተካሄደው 31ኛው የኦሊምፒክ ውድድር በአትሌቲክስ፣ ብስክሌትና ውሃ ዋና ስፖርቶች በመሳተፍ በአትሌት አልማዝ አያና በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ እና በ5 ሺህ ሜትር ነሐስ፣ ፈይሳ ሌሊሳ በማራቶን ብር፣ ገንዘቤ ዲባባ በ1 ሺህ 500 ሜትር ብር፣ ታምራት ቶላ በ10 ሺህ ሜትር፣ አትሌት ሐጎስ ገብረ ሕይወት በ5 ሺህ ሜትር፣ ጥሩነሽ ዲባባ በ10 ሺህ ሜትር እና ማሬ ዲባባ በማራቶን በተመሳሳይ የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘት ኢትዮጵያ 8 ሜዳሊያዎችን በማግኘት 44ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ጃፓን 32ኛውን የኦሊምፒክ ውድድር ስታስተናግድ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ፣ ብስክሌት፣ ውሃ ዋና እንዲሁም በቴኳንዶ ተሳትፋ በውድድሩ አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ወርቅ፣ ለሜቻ ግርማ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ብር፣ ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር እና ለተሰንበት ግደይ በ10 ሺህ ሜትር በተመሳሳይ የነሐስ ሜዳሊያ አምጥተው በ4 ሜዳሊያዎች 56ኛ ደረጃን በመያዝ በኦሊምፒክ ተሳትፎዋ ታሪክ ዝቅተኛውን ውጤት አስመዝግባለች። ካናዳ በፈረንጆቹ 1976 ባስተናገደችው 21ኛው ኦሊምፒክ፣ አሜሪካ በ1984 ባዘጋጀችው 23ኛው ኦሊምፒክ እና ደቡብ ኮሪያ በ1988 ባስተናገደችው 24ኛው የኦሊምፒክ ውድድሮች ኢትዮጵያ አልተሳተፈችም፡፡ ዘንድሮ በፈረንሳይ አስተናጋጅነት 33ኛው የኦሊምፒክ ውድድር እየተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያ 15ኛ በሆነው ተሳትፎዋ በአትሌቲክስና ውሃ ዋና ስፖርቶች 38 ስፖርተኞችን እያሳተፈች ሲሆን እስካሁን በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች በአትሌት በሪሁ አረጋዊ አማካኝነት የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።


Type:Technology

Page 6 of 75