Entertailment Page

Entertailment






👁 :
በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው የለም – ጤና ሚኒስቴር
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/14/2024
Posted By:utopia online

በኢትዮጵያ እስከ አሁን ድረስ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው አለመኖሩን ጤና ሚኒስቴር አረጋገጠ፡፡ ዛሬ የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ተቋም (አፍሪካ ሲ ዲ ሲ) ባወጣው መግለጫ÷ በ13 የአፍሪካ ሀገራት 2 ሺህ 863 ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ መያዛቸውን እና 517 ያህሉ ሕይወታቸው ማለፉን አሳውቋል፡፡ ይህን ተከትሎም በሽታው የሕብረተሰብ ጤና አኅጉራዊ ደኅንነት ስጋት ነው ማለቱን የጤና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡ የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የሁሉንም የአፍሪካ ሀገራት የጋራ ርምጃ የሚጠይቅ መሆኑም ተጠቁሟል። በኢትዮጵያም ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ በሞያሌ እና ሌሎች የመግቢያ ቦታዎች የቁጥጥርና ማጣራት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ነው ጤና ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡ ሚኒስቴሩና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በቅርበት ክትትል እያደረጉ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን÷ እስከ አሁንም በኢትዮጵያ በበሽታው የተያዘ ሰው አለመኖሩ ተረጋግጧል፡፡ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዙ ሰዎች ከሚያሳዩአቸው ዋና ዋና ምልክቶች መካከል÷ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የዕጢ እብጠት፣ የጡንቻ እና የጀርባ ህመም፣ ሽፍታ፣ የቆዳ ቁስለት እንዲሁም የአቅም ማጣት ይጠቀሳሉ፡፡ ምልክቶች መከሰታቸው የተረጋገጠ እና በቅርቡ በሽታው ወደ ተከሰተባቸው ሀገሮች የጉዞ ታሪክ ያለው ሰው በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራና እንክብካቤ ማግኘት እንዳለበት ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡ በሽታው በቀጥታ ከሰው ወደ ሰው በንክኪ የሚተላለፍ እንደመሆኑ መጠን በመግቢያና መውጫ ኬላዎች አካባቢ የሕብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ የተጠናከረ የቁጥጥርና መከላከል ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያስታወቀው፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች የሚያሳይ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም ሪፖርት ማድረግ ወይም በ952 እና 8335 ነጻ የስልክ መስመር ጥቆማ ማድረግ የሚቻል መሆኑም ተመላክቷል፡፡


Type:Science
👁 :
ዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ 40 በመቶ የሚሆነው በታላቁ ህዳሴ ተፋሰስ አካባቢ የሚተከል ነው- ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/15/2024
Posted By:utopia online

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 40 በመቶ የሚሆነውችግኝ በታላቁ ህዳሴ ተፋሰስ አካባቢ የሚተከል መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በድሬዳዋ አሊ ቢራ ፓርክ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አከናውነዋል፡፡ አቶ ተመስገን በዚሁ ወቅት ÷ ድሬዳዋ ሞቃታማ መሆኗን ጠቅሰው ሙቀቷ ምቹ፣ አየሯም ተስማሚና ለአካባቢው ምቹ ሆና እንድትቀጥል ችግኞችን አብዝተን መትከል ይገባል ብለዋል። ትልቅ ቦታ የትልቅ ሰው ስም በሚነሳበት የአሊ ቢራ ፓርክ የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርም ትልቅ ትርጉም እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም÷የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ለየት የሚያደርገው ከተያዘው የ7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ 40 በመቶ የሚሆነው በታላቁ ህዳሴ ተፋሰስ አካባቢ የሚተከል በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ ይህም የአባይ ወንዝና የታላቁ ህዳሴ ግድብን ከፍ ባለ አቅም ለማስጠበቅ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው በመግለጽ እስካሁንም ከ5 ቢሊየን ችግኝ በላይ መተከሉን ገልጸዋል፡፡ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር በበኩላቸው÷የአረንጓዴ አሻራ ትግበራ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥም ሆነ አካባቢው ደጋግሞ የሚያጠቃውን የጎርፍ አደጋ ለመከላከልና የአየር ንብረት ለውጥን ለማስተካከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እስካሁን በከተማ አስተዳደሩ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኝ መተከሉን አስታውሰው በቀጣይ ቀናት 1 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀምበር ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን አመላክተዋል። በድሬዳዋ ከተማ አሊ ቢራ ፓርክ በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።


Type:Social
👁 :
Maktub Paulo Coelho Dedicated to Nha Chica PART3
Catagory:Fiction
Auter:
Posted Date:08/15/2024
Posted By:utopia online

A master capable of taking the fire to wherever he desires, or of extinguishing it whenever he wants to do so. And, since he has taught no one how to light the fire, he is likely to leave everyone in the darkness.” “When you strike out along your path, you will find a door with a phrase written upon it,” says the master. “Come back to me, and tell me what the phrase says.” The disciple gives himself to the search, body and soul, and one day comes upon the door, and then returns to his master. “What was written there was 'THIS IS IMPOSSIBLE,' he says.” “Was that written on a wall or on a door?” the master asks. “On a door,” the disciple answers. “Well, then, put your hand on the doorknob and open it.” The disciple obeyed. Since the phrase was painted with the door, it gave way just as the door itself did. With the door completely open, he could no longer see the phrase -and he went on. The master says: “Close your eyes. Or even with your eyes open, imagine the following scene: a flock of birds on the wing. Now, tell me how many birds you saw: Five? Eleven? Sixteen? Whatever the response -and it is difficult for someone to say how many birds were seen -one thing becomes quite clear in this small experiment. You can imagine a flock of birds, but the number of birds in the flock is beyond your control. Yet the scene was clear, well-defined, exact. There must be an answer to the question. Who was it that determined how many birds should appear in the imagined scene? Not you!” A man decided to visit a hermit who, he had been told, lived not far from the monastery at Sceta. After wandering aimlessly about the desert, he finally found the monk. “I need to know what is the first step that should be taken along the spiritual path,” he said. The hermit took the man to a small well, and told him to look at his reflection in the water. The man tried to do so, but as he made his attempt, the hermit threw pebbles into the water, causing the surface to be disturbed. “I won't be able to see my face in the water if you keep throwing those pebbles,” said the man. “Just as it is impossible for a man to see his face in tro??6t? ?TI have been thinking about how to make this news less difficult to hear -how to paint it in brighter colors, add to it promises of Paradise, visions of the Absolute, provide esoteric explanations -but they do not apply. Take a deep breath, and prepare yourself. I have to be blunt, and I assure you, I am absolutely certain of what I'm telling you. It is an infallible prediction, without any doubt whatsoever. It's the following: you are going to die. It may be tomorrow or fifty years from now, but -sooner or later --you are going to die. Even if you would rather not. Even if you have other plans. Think carefully about what you are going to do today. And tomorrow. And with the rest of your life.” An explorer, a white man, anxious to reach his destination in the heart of Africa , promised an extra payment to his bearers if they would make greater speed. For several days, the bearers moved along at a faster pace. One afternoon, though, they all suddenly put down their burden and sat on the ground. No matter how much money they were offered, they refused to move on. When the explorer finally asked why they were behaving as they were, he was given the following answer: “We have been moving along at such a fast pace that we no longer know what we are doing. Now we have to wait until our soul catches up with us.” Our Lady, with the infant Jesus in her arms, came down to earth to visit a monastery. In their joy, the padres stood in line to pay their respects: one of them recited poetry, another showed Her illuminated images for the Bible, another recited the names of all of the saints. At the end of the line was a humble padre who had never had the chance to learn from the wise men of his time. His parents were simple people who worked in a traveling circus. When his turn came, the monks wanted to end the payment of respects, fearful that he would damage their image. But he, too, wanted to show his love for the Virgin. Embarrassed, and sensing the disapproval of the brothers, he took some oranges from his pocket and began to toss them in the air -juggling as his parents with the circus had taught him. It was only then that the infant Jesus smiled and clapped his hands with joy. And it was only to the humble monk that the Virgin held out her arms, allowing him to hold her Son for a while. Do not always try to be consistent. Saint Paul, after all, said, “The wisdom of the world is madness in the eyes of God.” To be consistent is always to wear a tie that matches one's socks. It is to have the same opinions tomorrow as one has today. And the movement of the planet? Where is it? So long as you do no harm to another, change your opinion once in a while. Contradict yourself without being embarrassed. This is your right. It doesn't matter what others think -because that's what they will think, in any case. So, relax. Let the universe move about. Discover the joy of surprising yourself. “God selected the crazy things on the earth so as to embarrass the wise men,” saidSaint Paul . The master says: “Today would be a good day for doing something out of the ordinary. We could, for example, dance through the streets on our way to work. Look directly into the eyes of a stranger, and speak of love at first sight. Give the boss an idea that may seem ridiculous, an idea we've never mentioned before. The Warriors of the Light allow themselves such days. Today, we could cry over some ancient injustices that still stick in our craw. We could phone someone we vowed never to speak to again (but from whom we would love to receive a message on the answering machine). Today could be considered a day outside the script that we write every morning. Today, any fault will be permitted and forgiven. Today is a day to enjoy life.” The scientist, Roger Penrose, was walking with some friends and talking animatedly. He fell silent only in order to cross the street. “I remember that -as I was crossing the street -an incredible idea came to me,” Penrose said. “But, as soon as we reached the other side, we picked up where we left off, and I couldn't remember what I thought of just a few seconds earlier.” Late in the afternoon, Penrose began to feel euphoric -without knowing why. “I had the feeling that something had been revealed to me,” he said. He decided to go back over every minute of the day, and -when he remembered the moment when he was crossing the street -the idea came back to him. This time, he wrote it down. It was the theory of black holes, a revolutionary theory in modern physics. And it came back to him because Penrose was able to recall the silence that we always fall into as we cross a street. Saint Anton was living in the desert when a young man approached him. “Father, I sold everything I owned, and gave the proceeds to the poor. I kept only a few things that could help me to survive out here. I would like you to show me the path to salvation.” Saint Anton asked that the lad sell the few things that he had kept, and -with the money -buy some meat in the city. When he returned, he was to strap the meat to his body. The young man did as he was instructed. As he was returning, he was attacked by dogs and falcons who wanted the meat. “I'm back,” said the young man, showing the father his wounded body and his tattered clothing. “Those who embark in a new direction and want to keep a bit of the old life, wind up lacerated by their own past,” said the saint. The master says: “Make use of every blessing that God gave you today. A blessing cannot be saved. There is no bank where we can deposit blessings received, to use them when we see fit. If you do not use them, they will be irretrievably lost. God knows that we are creative artists when it comes to our lives. On one day, he gives us clay for sculpting, on another, brushes and canvas, or a pen. But we can never use clay on our canvas, nor pens in sculpture. Each day has its own miracle. Accept the blessings, work, and create your minor works of art today. Tomorrow you will receive others.” The monastery on the bank of the Rio Piedra is surrounded by beautiful vegetation -it is a true oasis within the sterile fields of that part of Spain


Type:Event
👁 :
የእስራኤል ጦር በኢራን የሚፈጸምን ጥቃት ለመመከት በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን አስታወቀ
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/15/2024
Posted By:utopia online

የእስራኤል ጦር ኢራን እፈጽመዋለሁ ላለችው ጥቃት አስፈላጊውን ምላሽ ለመስጠት በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በቅርቡ የሃማስ ከፍተኛ የፖለቲካ ሃላፊ ኢስማኤል ሃኒዬህ እና የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላ ከፍተኛ አዛዥ በኢራን መገደላቸው ይታወሳል፡፡ ኢራን ለግድያው እስራኤልን ተጠያቂ ያደረገች ሲሆን÷በአንጻሩ እስራኤል በጉዳዩ ላይ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥባለች፡፡ ድርጊቱን ተከትሎም ኢራን በእስራኤል ላይ ከባድ አጸፋዊ እርምጃ እወስዳለሁ ስትል በተደጋጋሚ አስጠንቅቃለች፡፡ ከነገው ዕለት ጀምሮ ሊፈጸም ይችላል በተባለው መጠነ ሰፊ ጥቃት የሂዝቦላ ታጣቂ ቡድን ሊሳተፍ እንደሚችል ተመላክቷል፡፡ እስራኤል በበኩሏ÷ከኢራን ሊፈጽም የሚችልን ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት ከአሜሪካ ጋር አስተማማኝ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን አስታውቃለች፡፡ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞም የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ሃላፊ ሚካኤል ኩሪላ እስራኤል መግባታቸው ነው የተገለጸው፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት መንገሱን ተከትሎ አሜሪካ እስራኤልን ለመከላከል ቁርጠኛ መሆኗን ያረጋገጠች ሲሆን÷ለዚህም የሚሳኤል መከላከያ በቀጣናው ለማሰማራት ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች፡፡ የእስራኤል ጦርም ለጥቃቱ አስፈላጊውን ምላሽ ለመስጠት በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ እንዲቆም ትዕዛዝ መሰጠቱን አር ቲ ዘግቧል፡፡


Type:Social
👁 :
በካናዳ የተከሰተ ከባድ ሰደድ እሳት የጃስፐር ከተማን ግማሽ አወደመ
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/12/2024
Posted By:utopia online

ከፍተኛ የሰደድ እሳት የካናዳ የቱሪስት መዳረሻ የሆነችውን ጃስፐር ከተማ ግማሽ ያህሏን አውድሟቷል ተብሏል። ጃስፐር በካናዳ ምዕራባዊ ክፍል በአልበርታ ግዛት በተራራማው የጃስፐር ብሔራዊ ፓርክ መሃል የምትገኝ ከተማ ናት። ጃስፐር ከተማና ፓርኩ በዓመት ከሁለት ሚሊየን በላይ ጎብኚዎችን እንደሚያስተናግዱ ነው የተነገረው፡፡ እንደ አካባቢው ባለስልጣናት ገለፃ፤ ባሳለፍነው ሰኞ በግምት 10 ሺህ ነዋሪዎችና ከ15 ሺህ የሚልቁ ጎብኚዎች አደጋውን በመስጋት ከአካባቢው እንዲለቁ ተደርጓል፡፡ ከተማዋ ከሰደድ እሳቱ በሚመነጭ ጭስ እና አመድ የተሞላች ሲሆን÷ በየሆስፒታሉ ያሉ ታካሚዎችን የማስወጣቱ ሥራ እንደቀጠለ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ የአልበርታ መሪ ዳንየል ስሚት “ይህ ለማንኛውም ማህበረሰብ እጅግ የከፋ አደጋ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ሰደድ እሳቱ እስከ አሁን ከቁጥጥር ውጪ መሆኑን ገልጸው÷ በአካባቢው ከ 30 እስከ 50 በመቶ የሚሆነው መሠረተ ልማት እየወደመ መሆኑን በመግለጽ ከፍተኛ የመልሶ ግንባታ እንደሚጠይቅም አክለዋል፡፡ ክስተቱን እየደጋገሙ አስከፊ ቅዠት የመሰለ አደጋ በማለት የጠሩት የአካባቢው ከንቲባ ሪቻርድ አየርላንድ፤ ሰዎች የሁሉም ማህበረሰብ የልብ ትርታ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። ሰዎችን አትርፈናል ይህ ደግሞ ወሳኝ ነው፤ ከተማዋን መልሶ ለመገንባት መንገድ ማግኘት ይቻላል ያሉት ከንቲባው፤ ዳግም መገናኘትና መተቃቀፍ እንችላለን ምክንያቱም ሁላችንም ወጥተናል ማለታቸውን ዘ ኒው ዴይሊ ዘግቧል፡፡


Type:Social
👁 :
ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ለመነጋገር ፍቃደኛ መሆኗን ገለጸች
Catagory:News
Auter:
Posted Date:08/16/2024
Posted By:utopia online

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ዩን ሱክ ዮል ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያለውን ውጥረት ለማርገብና የኢኮኖሚ ትብብርን ለመቀጠል የሚያስችሉ መንገዶችን የሚያከናውን አዲስ የሥራ ቡድን ለማቋቋም ሀሳብ አቅርበዋል። አዲሱ የሥራ ቡድንም የቀጣናውን ውጥረት ማርገብን ጨምሮ የኢኮኖሚ ትብብር፣ የሰዎች ለሰዎች እና የባሕል ልውውጥ እንዲሁም ከአየር ንብረት ለውጥ እና የአደጋ ምላሽ ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ጉዳዮች ሊዳስስ እንደሚችል ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም ፒዮንግያንግ ኒውክሌርን ለማስወገድ አንድ እርምጃ የምትወስድ ከሆነ ሀገራቸው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለመጀመር ዝግጁ መሆኗንም አመላክተዋል። በሁለቱ ኮሪያዎች ግንኙነት መካከል ውይይት እና ትብብር ቁም ነገር ያለው መሻሻል ሊያመጡ እንደሚችሉም ዩን መናገራቸውን ዲ ደብሊው ዘግቧል።


Type:Social
👁 :
ኢትዮጵያና አውሮፓ
Catagory: History
Auter:
Posted Date:08/16/2024
Posted By:utopia online

ከ1798 እስከ 1848 ዓ.ም. ድረስ ያለው ክፍለ ዘመን የመሳፍንት ዘመን ተብሎ ይጠራል ። በዚህ ጊዜ ንጉሡ የሚኖረው አማራ በሚባለው አውራጃ በጐንደር ̧ ነበር ። ኢትዮጵያን በሞላ ለማስተዳደር ኃይል አልነበረውምና ሸዋ ፤ ጐጃም ፤ ትግሬና ሌሎችም ስፍራዎች የሚተዳደሩ በግል ራሶቻቸው እና በባለ ቤቶቻቸው ነበር ። የቀይ ባሕር ጠረፎች ፤ ሐረር ፤ ሰሜን ሱዳንና ሱማሌም በእስላ ሞች ነበር የሚተዳደሩት ። ጋሎች ደግሞ ደቡባዊውን ክፍል ይገዙ ነበር ። ብዙ ውን ጊዜ ገዥዎች በመካከላቸው ጦርነት ያደርጉ ነበር ። በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ታላላቆች የአውሮጳ ሐገሮች በኢትዮ ጵያ ላይ ታላቅ ፍላጐት አደረባቸው ። 1800-1850ዓ.ም. አዲስ ጐብኚዎች የሮማ ካቶሊኮችና የፕሮቴስታንት ሚሲዮናውያን ነጋዴዎችና የዲፕሎማቲክ ሰዎች የአውሮፓና የዓለምን ሥልጣኔ ወደ ኢትዮጵያ እየያዙ ገቡ ። ኢትዮጵያን በበለጠ ከየሐገራቸው ያስተዋውቁ ጀመር ። በአፍሪካውያን ቋንቋዎች በተተረጐሙት ቅዱ ሶት መጻሕፍት የአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ 1833 ዓ.ም. ጨርሶ በመተር ጐም ሁለተኛው ነበር ። በ1763ዓ.ም. ሶልት የተባለ ሰው ከእንግሊዙ ንጉሥ ጆርጅ ፫ኛ ለኢትዮጵያ ንጉሥ የተላኩ ደብዳቤዎችን ይዞ ገባ ። ሆኖም ንጉሡ ዘንድ ጐንደር ሳይደርስ ደብዳቤውን ለትግሬው ገዥ ሰጠ ። ሶልት ስለኢትዮጵያ አንድ በውስጡ የሐገሪ ቱና የሕዝቡ ስዕል የሚታይበት ግሩም የሆነ መጽሐፍ ጽፎአል ። መጽሐፉም በአ ውሮፓና በተባበረው አሜሪካ ሕዝብ ዘንድ በመነበብ ኢትዮጵያን የማወቅ ፍላ ጐት አሳድሮባቸዋል ። በ1833 ዓ.ም. ታላቋ ብሪታንያና ፈረንሣይ በምፅዋ ቆን ሲሎቻቸውን አቋቋሙ ። በ1834ዓ.ም. በአንድ ኢትዮጵያዊ መሪና በአውሮጳ ሐገር መካከል የመጀመሪያው ውል ተፈረመ ። የፈረሙትም ለኢትዮጵያ ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ፣ ለታላቋ ብሪታንያ ካፒቴን ኸሪስ ነበሩ ። የፈረንሣይ መንግሥ ትም ከኚሁ ንጉሥ ጋር በ1836 ዓ.ም. አንድ ውል ተፈራርሟል ። በዚሁ ዘመን ፕላውደንና ቤል የተባሉ ሁለት እንግሊዛውያን ለንግድ ወደ ኢትዮጵያ ገቡ ። በኋላም ፕላውደን የእንግሊዝ መንግሥት መልክተኛ በመ ሆን በ1842 ዓ.ም. ከጐንደሩ ራስ ዐሊ ጋር አንድ ውል ተፈራርሟል ። በ1843ዓ.ም. ዋና ዋናዎቹን አራት ጠቅላይ ግዛት የሚገዙ አራት ታላ ላቅ ባላባቶች ነበሩ ። ራስ ዓሊ ከንጉሡ ይልቅ ጐንደርን በጠነከረ መንፈስ ይመሩ ነበር ። ደጃዝማች ጐሹ ጐጃምን ፤ ደጃዝማች ውቤ ትግሬንና ፤ ንጉሥ ኃይለመለ ኮት ሸዋን ይገዙ ነበር ። ከነዚህም ማንኛቸውም ሌላውን አልፎ ለመውጋት ኃይል ስለአልነበረው በየራሳቸው ግዛት ተወስነው ነበር ። ከነርሱም አንዱ ይነግሣል የማለት አሳብ ቢኖርም ለዚህ ኃላፊነት ብቁ ሆኖ የተገኘው ሌላ ሰው ነበር ።


Type:Event
👁 :
የጉለሌው ሰካራም1 በተመስገን ገብሬ2 ክፍል 1
Catagory:tireka
Auter:
Posted Date:08/16/2024
Posted By:utopia online

በጉለሌ የነበረው የታወቀ ዶሮ ነጋዴ ማነው ብለው ከገፈርሳ እስከ ደጃዝማች ይገዙ ሰፈር ለጠየቁ ሰዎች፤ ተበጀ ሰካራሙ ተበጀ ዶሮ ነጋዴው፤ ተበጀ ነው ብለው ይነግሯቸዋል፡፡ የሕይወቱ ታሪክ ፍፁም ገድል ነው፡፡ ጢም ያለው ሽማግሌ ሰው ነው፡፡ ራሱን ጠጉር ውሃ ወይም መቀስ ነክቶት አያውቅም፡፡ ማለዳ አይናገርም፡፡ በጠርሙስ የከመረውን ከጠጣ በኋላ ሲራገም ወይም ሲሳደብ ሲፈክር ወይም ሲያቅራራ ድምጡ ከፈረንጅ ውሻ ድምጥ ይወፍራል፡፡ ቢያውቀውም ባያውቀውም ላገኝው ሁሉ ማታ ሰላምታ ይሰጣል፡፡ ቢያውቀውም ባያውቀውም ካገኝው ሁል ጋር ማታ ይስቃል፡፡ ቢውቀውም ባያውቀውም የሰላምታው አይነት እንደ ወታደር ወይም እንደ ሲቪል ቢሆን ለእርሱ እንደተመቸው ነው፡፡ ከሰላምታው ጋር ድምጥ ትሰማለችሁ፡፡ ከአፉ ከሚወጣው ከሚወጣው ግን አንድ ቃል መለየት አትችሉም፡፡ ቡን በተፈላ ጊዜ በጉለሌ በየምድጃው ሥር የሰካራም ተረት በየተጫወተ ሰው ሁሉ የተናገረ በተበጀ ላይ ነው፡፡ መልኩን አይተውት ያላወቁት ባልቴቶች እንኳ ከፍንጃል ቡን ፉት እያሉየሌላውን ሰካራም ተረት በተበጀ ላይ ያላክኩት ነበር፡፡ይህ እውነት ነበር፡፡ በጠባዩ ከተባለለት የባሰ ሰካራም ይሁን ወይም የጉለሌ ባህር ዛፍ ውስጥ ወጥቶ እንደ አዲስ እንግዳ ሰው ሆኖ ለአዲስ አበባ ታይቷል፡፡ ከዱሮ የእንጨት ጉሙሩክ አጠገብ ወደ ምሥራቅ ሲል ሲል ካለው ወንዝ ማዶ ድልድዩን ወደ ምሥራው ተሻግሮ መጀመሪያ የሚገኝው አነስተኛ ሳር ክዳን ቤት የተበጀ ቤት ማለት ያ ነው፡፡ በዚያ በቤቱ በዚያ በጉለሌ በሠፈሩ ኖረ፡፡ እንጨቱን ተሸክሞ አፈሩን ቆፍሮ ቤቱን የሰራው እርሱ ነው፡፡ ዋጋ ከፍሎ አስከድኖታል፡፡ ተበጀን ኩራት ተሰማው፡፡ ቆይቶ ደግሞ አይኖቹ እንባ አዘሉ፡፡ በጉንጩም የእንባ ዘለላ ወረደው፡፡ በግራ እጁ መዳፍ ከጉንጩ የተንከባለለውን እንባ ጨፈለቀው፡፡ ዓይኖቹ እንባ ያፈሰሱ ለራሱ ጎጆ ስላለው ነው፡፡ ሊነገር በማይችል ደስታ ልቡ ተለውስዋል፡፡ ዝናም ያባረራቸው ም ከቤቱ ጥግ ሊያጠለሉ ይችላሉ፡፡ ቤት የእግዚአብሄር ነውና ውዥብ እንዳያገኛቸው ከቤት ውስጥ


Type:Social

Page 9 of 75