Entertailment Page

Entertainment






👁 :
አምባሳደር ዮሐንስ አብርሃም የካማላ ሀሪስ የፕሬዚዳንታዊ ሽግግር ቡድን ሀላፊ ሆነው ተመረጡ
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/28/2024
Posted By:utopia online

የትውልድ ሀረጋቸው ከኢትዮጵያ የሚመዘዘው አሜሪካዊው አምባሳደር ዮሐንስ አብርሃም የካማላ ሀሪስ የፕሬዚዳንታዊ ሽግግር ቡድን ሀላፊ ሆነው መመረጣቸው ተነገረ። ዴሞክራቶችን ወክለው በመጪው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚፎካከሩትን ካማላ ሀሪስ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የመምራት ሃለፊነት የተሰጣቸው አምባሳደር ዮሐንስ የፕሬዚዳንታዊ ሽግግር ቡድን በመምራት ልምድ ያላቸው መሆኑም ገልጸዋል። ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዮሐንስ መቀመጫውን ጃካርታ ባደረገው የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ ሲሆን÷ በቀጣይ ቀናት ስራቸውን አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ ተብሏል። አምባሳደር ዮሐንስ በአዲሱ የስራ ሀላፊነት ምክትል ፕሬዚዳንቷ ካማላ ሀሪስ በሚደረገው የምርጫ ሂደት ተፎካካሪያቸው ዶናልድ ትራምፕን ማሸነፍ ከቻሉ የአዲሷን ፕሬዝዳንት የሽግግር ቡድን በማዋቀር ከመሳተፍም በላይ ፖሊሲ ማርቀቅ ላይም ሚና ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ እንዳሉት፤ አምባሳደር ዮሐንስ አብርሃም የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት የአሜሪካ አምባሳደር ሆኖ በቆዩባቸው ሁለት አመታት የአሜሪካን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። አምባሳደር ዮሐንስ ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 2020 የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሽግግር ቡድን ዋና ሀላፊ እንደነበሩ ኤንቢሲ ኒውስ በዘገባው አስታውሷል። ዮሐንስ በባራክ ሁሴን ኦባማ አስተዳደር ዘመንም ለስምንት ዓመታት በኋይት ሃውስ ውስጥ ሙያዊ አገልግሎት ሰጥተዋል። የ42 ዓመቱ አምባሳደር ዮሐንስ አብርሐም በፖለቲካ ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በቢዝነስ አስተዳደር የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በከፍትኛ ማዕረግ ተመርቀዋል።


Type:Technology
👁 :
የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ስቬን ጎራን ኤሪክሰን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/28/2024
Posted By:utopia online

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ የነበሩት ስቬን ጎራን ኤሪክሰን በ 76 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ባጋጠማቸው የካንሰር ሕመም ምክንያት በሕይወት የመቆያ ጊዜያቸው አንድ ዓመት ብቻ እንደነበር በሐኪሞቻቸው ተነግሯቸው እንደነበር ተመላክቷል፡፡ አሰልጣኝ ስቬን ጎራን ኤሪክሰን በክለብ ደረጃ ማንቼስተር ሲቲ፣ ሌስተር ሲቲ፣ ሮማ እና ላዚዮን ጨምሮ 12 ክለቦችን ማሰልጠናቸው ይታወሳል፡፡ በአሰልጣኝነት ጊዜያቸውም 18 ዋንጫዎችን ማንሳት እንደቻሉ ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡


Type:Social
👁 :
በ2024 አጋማሽ የሩሲያ ኢኮኖሚ በ4 ነጥብ 6 በመቶ ማደጉ ተገለጸ
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/28/2024
Posted By:utopia online

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በፈረንጆቹ 2024 የመጀመሪያ አጋማሽ የሩሲያ ምጣኔ ሀብት (ጂዲፒ) በ4 ነጥብ 6 በመቶ ማደጉን አስታወቁ፡፡ ፕሬዚዳንቱ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ አስመልክቶ ባደረጉት የቪዲዮ ኮንፈረንስ ላይ “እንዳለፈው ዓመት ሁሉ የሩሲያ ምጣኔ ሀብት ከፍ ባለ ፍጥነት ማደጉን ቀጥሏል” ማለታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ የሥራ አጥ ቁጥሩም በሰኔ ወር ይፋ እንደተደረገው ከእስከ አሁኑ በተለየ ሁኔታ በ 2 ነጥብ 4 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅሰዋል፡፡


Type:Technology
👁 :
አሜሪካ ከፌስቡክ ላይ የኮቪድ-19 የተወሰኑ ይዘቶች እንዲነሱ ግፊት አድርጋ ነበር ተባለ
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/28/2024
Posted By:utopia online

የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አሥተዳደር በ2021 የኮቪድ-19 የተወሰኑ ይዘቶች ከፌስቡክ እንዲወገዱ ለወራት በተደጋጋሚ ግፊት ማድረጉን የሜታ ኩባንያ መስራች ማርክ ዙከር በርግ አመላከቱ፡፡ ዙከር በርግ ለሀገሪቱ ምክር ቤት የፍትሕ ኮሚቴ በጻፉት ደብዳቤ÷ በባይደን አሥተዳደር ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት አስቂኝና ቀልድ አዘል መልዕክቶችን ጨምሮ አንዳንድ የኮቪድ-19 ይዘቶችን ሳንሱር ለማድረግ ግፊት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የባይደን አሥተዳደር የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች ጎጂ የሆኑና የተሳሳቱ መረጃዎችን እንዲያስወግዱ መጠየቁን ደግፎ እንደነበርም ዘ ኢንዲፐንደንት ዘግቧል፡፡ በተደጋጋሚ የተደረገውን ግፊት ተቋማቸው ለዓለም አለማሳወቁ የቆጫቸው ዙከርበርግ÷ እንዲህ ያለ ተጽዕኖ ድጋሜ ከተፈጠረ እንደማይታገሱ አስጠንቅቀዋል፡፡


Type:Technology
👁 :
ዴርቶጋዳ
Catagory:Fiction
Author:
Posted Date:08/27/2024
Posted By:utopia online

እናድርገው......" አለ በሌላ አጭር ብራና ላይ የሰፈረ የቃላት ዝርዝር እያወጣ፡፡ “እነዚህን ቃላት እዚህ ግጥም ውስጥ በታትነህ ትደባልቃቸዋለህ፡፡ አዘበራርቀህ ዝራቸው፡፡ ለግጥምህ ፡ ጉልበት ከመሆናቸውም በላይ እኔም ከእንግዴህ ይህን ከረጢት ይዤ አልንከራተትም፡፡...በሳ......ዝራቸው በታትኖ ፀጋዬ የተሰጡትን ቃላት በፃፈው ግጥም ውስጥ ዘራቸው፡፡ ቃላቱ 48 ናቸው፡፡ ሰውየው ባድናቆት እንደገና ጨበጠውና 48ቱ ቃላት የተዘሩበትን ግጥም እየተመለከተ : በሌላ : ወረቀት ላይ አንድ ጉጥ ያለው መስቀል መሳል ጀመረ፡፡ በመስቀሉ ላይም አያሌ ቁጥሮችንና አንዳንድ ከባባድ ቃላትን ከቀረፀበት በኋላ ሰቆቃወ ጴጥሮስ የሚለውን ምስጢራዊ ግጥም በብራና ወረቀት ላይ ከከረጢቱ ባወጣው መቃብዕርና ቀለም ቀዳው፡፡ በብራናው ላይ ገልብጦ ከጨረሰ በኋላ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንደገና አነበበው፡፡ በሚያስገመግም ድምፅ፡፡ ሰቆቃወ ጴጥሮስ እየ+ ምነው እመ ብርሃን? ኢትዮጵያን ጨከንሽባት? ምነው ቀኝሽን ረሳሻት? እስከመቼ ድረስ እንዲህ+ መቀነትሽን ታጠብቂባት? ልቦናሽን ታዞሪባት? ፈተናዋን* ሰቀቀንዋን ጣሯን ይበቃል ሳትያት? አላንቺ እኮ ማንም የላት.... አውሮጳ እንደሁ ትናጋዋን፣ በፋሽስታዊ ነቀርሳ ታርሳ˖ተምሳ+ በስብሳ ሂትለራዊ እባጭ ጫንቃዋን እንደ ኮረብታ ተጭኗት ቀና ብላ እውነት እንዳታይ አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟት ነፍሷን ድጦ ያስበረከካት ሥልጡን ብኩን መፃጉዕ ናት፤ እና+ ፈርቼ እንዳልባክን+ ሲርቀኝ የኃይልሽ ውጋጋን አንቺ ካጠገቤ አትራቂ+ በርታ በይኝ እመ ብርሃን ቃል ኪዳኔን እንዳልረሳት- እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን፡፡ አዎን ብቻዬን ነኝ ፈራሁ እሸሸግበት ጥግ አጣሁ እምፀናበት ልብ አጣሁ እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ ተፈትቶ እንዳይከዳት ሠጋሁ አዋጅ+ የምሥራች ብዬ የትብት ምግቤን ገድፌ ከናቴ ማህፀን አልፌ በኢትዮጵያ ማህፀን አርፌ+ ከአፈርዋ አጥንቴን ቀፍፌ ደሜን ከደሟ አጠንፍፌ ከወዟ ወዜን ቀፍፌ በሕፃን አግሬ ድኼባት+በሕልም አክናፌ ከንፌ እረኝነቴን በሰብሏ+ በምድሯ ላብ አሳልፌ ከጫጨትና ከጥቾ ከግልገል ጋር ተቃቅፌ፤ በጋው የእረኛ አደባባይ+ ክረምት እንደወንዙ ፍሳሽ በገጠር የደመና ዳስ በገደል ሸለቆ አዳራሽ ከቀቅና ከሚዳቋ+ ከዥግራ ጠረን ስተሻሽ በወንዝ አፋፍ ሐረግ ዝላይቱ መወርወር መንጠልጠል ጢሎሽ ከፍልፈል ጋር ሩጫ ስገጥም+ ከቀበሮ ድብብቆሽ ከናዳ ጫፍ ሳር አጨዱለግት ላሜ ትንሽ ግጦሽ ለጥጃዬ የሌት ግርዶሽ ለጥማድ በፊዎች ፊት ለማታቸው ትንሽ ድርቆሽ ለግልገሌ ካውሬ ከለል እማሳው ሥር ጎጆ መትከል ለፀሐይ የሾላ ጠለል← ለዝናብ የገሳ ጠለል ውሎ የንብ ቀፎ ማሰስ ያበባ እምቡጥ ሲፈነዳ ግጦሽ ሣር ሲለመልም ሲሰማሩ ሰደድ ሜዳ አዝመራው ጣል ከንበር ሲል ከበድ ለሆራ ሲነዳ ፈረስ ግልቢያ ስሸመጥጥ← አወፎች ዜማ ስቀዳ ልቤ በንፋስ ተንሳፈፉ በዋሽንት ዋይታ ሲከዳ ያቺን ነው ኢትዮጵያ የምላት እመ ብርሃን እረሳሻት? ያችን የልጅነት ምሥራች? የሕፃንነት ብሥራት የሣቅ የፍንደቃ ዘመን← የምኞት የተስፋ ብፅአት ያቺን የልጅነት እናት? አዛኚቱ እንዴት ብለሽ ጥርሶችሽን ትነክሽባት? ስሜን በስምሽ ሰይሜ ባገልግሎትሽ ስዋትት ከዜማ ቤት እቅኔ ቤት አድባ ቤት አመራሕፍት ካንቺ ተቆራኝታ ዕድሌ+ ካንቺ ተቆራኝታ ነፍሴ ከቀፈፋ ደጀ ሰላም ከቤተ ልሔም ቅዳሴ አኩ ቀፎ+ ዳባ ለብ ቅኔ ዘርፎ ግሥ ሃይ መቅደስ አጥኖ ማኅሌት ቆም በሳ ተክህኖ አጊጦ← በበር አካል ተሸልሞ እመ ብርሃን ያንቺ ጽላት ነፍሴ ላይ በሳት ታትሞ የመናኒው ያባ ተድላ ረድ ሆኜ አብሮኝ ታድሞ ሕይወቴ እምነትሽን ጸን ሥጋ ፈቃዴ ተድሶ ለሕንፃሽ መዲና ቆም፡ ለክብርሽ ድባብ ምሰሶ ስሜን በስምሽ ሰይሜ ሆነሽኝ የእምነቴ ፋኖስ ለዋዜማሽ ግሸን ማርያም- ለክብርሽ ደብረ ሊባኖስ ስሮጥ+ በወንበሩ አኖርሺኝ በአንበሳው በቅዱስ ማርቆስ ታዲያን ዛሬ ኢትዮጵያ ስትወድቅ ከምትሰጪኝ ለፍርሃት ጦስ ምነው በረኝነት ዕድሜ ዓይኔን በጓጎጣት የሎስ የጋኔል ጥንብ አንሳ ከንፎ+ ወርዶ በጨለማ በርኖስ፡ ባክሽ እመብርሃን ይብቃሽ+ ባክሽ ምስለ ፍቁር ወልዳ ጽናት ስጪኝ እንድካፈል+ የእናቴን የኢትዮጵያን ፍዳ ከነከሳት መርዝ እንድቀምስ ከነደደችበት እቶን የሷን ሞት እኔ እንድሞታት ገላዋ ገላዬ እንዲሆን፡፡..... እምን+ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ እምፀናበት ልብ አጣሁ፡፡ ሕፃን ሆኜ የእርግብ ጫጩት+ አንዳንዴ ራብ ሲያዳክማት ችጋር ከጎጆዋ ገፍቶ እዛፍ ግርጌ ሲጥላት እናቷ በርራ ደርሳላት በአክናፏ ሙቀት ታቅፋት እፍ እያለች ግንባሯ ላይ+ ሕይወት ስትተነፍስባት ወዲያው ነፍስ ትዘራለች ሽር-ብር-ትር እያለች። ባክሽ አንቺም አትራቂብኝ እመ ብርሃን እናቱ ትንፋሽሽን እፍ በይብኝ ዕናትሽን እፍ በይብኝ+ ወይም ይቺን የሞት ጽዋ+ ጥላዋ ነፍሴን ካፈናት እንዳልጠጣት አሳልፊያት መራራ ክንፏን ገንጥለሽ ቀጠሮ ቃልዋን ግደፊያት ... አለዚያም ዕናትሽን ስጪኝ ልጠጣው ኪዳነ-ውሉን የኔ ፍቃድ እምነትሽ ነው+ ያንቺ ፍቃድ ብቻ ይሁን፡፡ እንደ ጳውሎስ እንድፀና በፍርሀት እንዳልታሰር በውስጤ ከሚታገለኝ በሥጋ አውሬ እንዳልታወር ለዕለቱ ሞት እንዳልሰንፍ የኪዳኔ ቃል እንዳይነጥፍ ቃልሽ በሕሊናዬ ዲብ +ኃይልሽ በህዋሴ ይረፍ፡፡ ፍርሀት ቢያረብብኝም +አንቺ ካለሽ አልሰጋም ኩርትም ብዬ አችልበት እሸሸግበት አይጠፋም የግማደ መስቀሌን ጉጥ + እታገስበት አላጣም አለዚያማ ብቻዬን ነኝ ኢትዮጵያም አላንቺ የላት አንቺ አዕኝኝ አንድጸናላት፡፡ አስር ብኝ የአምነት ቀንጃ ለሥጋቴ አጣማጅ አቻ ለጭንቀቱ-መቀነቻ፡፡...... አዎን÷ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ እሸሸግበት ጥግ አጣሁ እምፀናበት ልብ አጣሁ...... ያሉ ቀበና (ፀጋዬ ገብረ መድህን) “ግሩም ነው! እሳት የላሰ ግጥም እሳት የላስክ ልጅ!' የፀጋዬን ግንባር ግጥም አድርጎ ሳመው፡፡ “ማስጠንቀቂያ!" አለው ከዚያ፡፡ "ከዚህ ግጥም ላይ አንድም ቃል አንድም ነጥብ እዳይለወጥ! ይህ ምስጢር ነው፡፡ ከዚህ ግጥም ውስጥ አንድ ቃል ብታወጣ ከሀገርህ ጋር ያለህ ወዳጅነት ይጎድፋል፡፡ ለመሆኑ ታሳትመዋለህ?“እንደ አምላክ ፈቃድ “እንግዲያውስ እንደነገርኩህ አንድም ቃል እንዳይለወጥ! አንድ ቀን ይህ ግጥም........ ትኵር ብሎ አይቶት በብራና ላይ የፃፈውን የሰቆቃወ ጴጥሮስን ቅጂ ከረጢቱ ውስጥ ቋጥሮ ሲወጣ ነግቶ ወፎች እየዘመሩ ነበር፡ፀጋዬ አፉን ከፍቶ ቀረ፡፡ ተከትሎ “ስምህ ማነው? ዳግመኛ ላገኝህ እፈልጋለሁ...." ሲል እየሮጠ ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ጠየቀው፡፡ ሰውየው እርምጃውን ጉቶ ወደኋላ ዞረ፡፡ የፈለከውን ብለህ ልትጠራኝ ትችላለህ፡፡ እኔና አንተ ከአሁን በኋላ የምንገናኘው የግጥም መጽሀፍህ ሲታተም ብቻ ነው፡፡ ደህና ሁን! እርምጃውን ቀጠለ፡፡ ፀጋዬም በዓይኑ ሸኘው። ይህ ከሆነ ከአምስት አመት በኋላ በ1966 ዓ.ም የዘጋዬ ገብረ መድህን እሳት ወይ አበባ የሚባለው የግጥም መጽሀፍ ታተመ፡፡ ‹እሳት ወይ አበባ ለህትመት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በገባበት ዕለት ከሰአት በኋላ ማተሚያ ቤቱ ውስጥ አንድ መነኩሴ ታይተው ነበር፡፡ መነኩሴው ካሜራ ክፍል የገቡት ሰቆቃወ : ጴጥሮስ : የሚለው ግጥም በዛ ጥራዝ : ውስጥ መካተቱንና ቃሉም አለመለወጡን አረጋግጠው ለመውጣት ቢሆንም ወደ ማተሚያ ቤቱ ሲገቡ ግን ለህትመት የተዘጋጀ «አክሳፎ/ የሚል ርዕስ ያለው መጽሀፍ ይዘው ስለዚሁ መጽሀፍ የህትመት ጉዳይ ሰመነጋገር በሚል ሰበብ ነበር። «አክሳፎስ» የሚባል መጽሀፍ ግን እስካሁን ድረስ ታትሞ ለንባብ አልበቃም። ይህ ከሆነ ከብዙ አመታት በኋላ ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን በራሱ ድምፅ አንብቦ አብረን ዝም እንበል» በሚል ረዕስ ባሳተመው የግጥም ሲዲ ካሴት መግቢያ ላይ ሰቆቃወ ጴጥሮስን የፃፈበትን ምክንያት እንዲህ ብሎ ሲያብራራ ተደመጠ። ሌሊቱን “ሰቆቃወ ጴጥሮስ የጴጥሮስ ያችን ሰዓት መዝጊያ የታሪካዊ ጀግናው የመጨረሻ ቃል ነው። የመጨረሻውን ቃል ለጀግናው ተውለት፡፡ ይላሉ፡ ጥንታውያን የታሪካዊ ቴአትር ፀሐፍት..... እነ ኢከራን ኤፍራት.....እነ ዩሩፒድዩስ፡፡.....አቡነ ጴጥሮስ በግራዚያንና በባንዶቹ በባንዶች አሽከሮች አኮርባሽነት በገነተ ልዑል ጉድጓድ ቤት ውስጥ ሲገረፍ ሲመረመር ኢትዮጵያን ከድተህ በሞሶሎኒ እመን ተብሎ ሲተለተል አድሮ በማግስቱ : ጠዋት በአደባባይ በጥይት ተደበደበ፡ በግራዚያኒ ትዕዛዝ የጥይት እሩምታ ተኩሰው የጠቀጠቁት ጣሊያን ) ያሰለጠናቸው :: የሰሜን ባንዳዎች ወንድሞቻችን ናቸው፡፡ ጴጥሮስ እንኳንስ ህዝቡ ምድሪቱ ጭምር ለፋሽስት እንዳትገዛ አውግዞ ሞተ። ...... ለመጀመሪያው ጊዜ በ15 ዓመቴ ክቡር ዘበኛ ካዴት ልገባ ጠፍቼ በልጅነቴ ከአምቦ ከተማ ስመጣ አዲስ አበባ እምብርት መዳረሻ | አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ከትሬንታኳትሮ ወርጄ.....አባቱ ሰለአቡነ ጴጥሮስ የእረኝነት እድሜና የጀግንነት ጀብድ ህይወት በከፍተኛ አድናቆት ያጫውቱኝ የነበረው ትዝ ብሎኝ ሐውልቱ ሥር ቆሜ ቀረሁ፡፡ ......ይህ በሆነ ከአሥር ሙት በኋላ አለቃችን የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ክቡር ደጃዝማች ግርማቸው ተክለ ሐዋርያት ማስታወቂያ ሚኒስትር እዛው አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት አጠገብ ስብሰባ ጠርተውን ቢሮአቸው አምሽተን ስንወጣ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ አንድ ሞቅ ...እ... ያለው የተበሳጨ ጀብራሬ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ላይ ሽንቱን እየሸና “አንተ ድንጋይ ጓደኞችህ ተመችቷቸው በማርቼዲስ ሲንሽራሸሩ ይኸው አንተ ድንጋይ ሆነህ ቀረህ ድንጋይ! እሸናብሃለሁ!.... ሲል በልጅነት ደም ፍላት ዘልዬ ከጀብራፊው ጋር ግብግብ ገጠምኩ፡፡ ድንጋይ ነው ... ድንጋይ አይደለም!...በሚል በቡጢም ተቃመስን፡፡ ከስብሰባው የተበተነ ሰዎች ገላገሉንና እየተበሳጨሁ ቤቴ ገባሁ። ሌሊቱን አልተኛሁም፡፡ ጴጥሮስ ህያው ነው ለማለት፣ ጴጥሮስ ድንጋይ አይደለም ለማለት ይመስለኛል፤ ጴጥሮስ ያችን ስአትን ስጭር አርክ፡፡ እንዳልኩት ይህ ስነግጥም የታሪካዊ ጀግናው የመጨረሻ ቃል ነው....” ይህ የራሱ የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን - የምስክርነት ቃል ነው፤፤ ይህን ንግግርም ብዙ ኢትዮጵያውያን አዳምጠዋል፡፡ ሎሬቱን ...መጽሀፉን ያነበቡም ያላነበቡም ያደንቁታል፤ ነገር ግን ስለ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንጂ በዚህ ንግግሩ ውስጥ ጀብራሬ ተብሎ ስለተተሰው ኃያል ሰው የሚያውቅ ማንም የለም፡፡ በሎፊቱ ንግግር ውስጥ ግን አንድ ነገር : መገንዘብ ይቻላል፡፡ “ሞቅ....ያለው የተበሳጨ : ጀብራሬ" የሚል የሚያሻማና ብዙ ጥያቄ የሚቆስቁስ ገለፃ አለ፡፡ ሞቅ ያለው፤ ደግሞ የተበሳጨ ደሞ ጀብራራ ደሞ በቡጢ የሚያቀምስ ደሞ ግብግብ ተጋጥሞ የማይወድቅ ደሞ በንግግሩ ውስጥ መረዳት እንደሚቻለው ስለ አቡነ ጴጥሮስ ብዙ የሚያውቅ የሚመስል! ደሞ በራስ በመተማመን የተሞላና ድንጋይ ብሎ የሚሳደብ ደሞ ስንት ቦታ ባዶውን ተቀምጦ ሀውልት ላይ የሚሸና! ባል ሆኖም ቆብ ጣይ መነኩሴ ዲዲሞስ ጀብራራው ባይኖር ኖሮ ሕቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ላይ ሽንቱን ባልሸና አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ላይ ሽንቱን ባይሽና : ጴጥሮስ ያችን ሰአትን የመሰለ : ቴአትር ባልተፃፈ ሰቆቃው ጴጥሮስም ሳይጨመርበት አንድም ቃል ሳይቀነስበት ላለፉት ብዙ አመታት ሲኮም የኖረው ባለ 105 ስንኝ ነው፤፤ ቃላቱም 497 ናቸው፡፡ ቃላት ያቁትን ምስጢር - ሰመታት ኣልተገኘም፤፤ አንድም ቃል የታተመውና በጣፋጭነቱ ሰቆቃወ ጴጥሮስ ግጥም ሎሬቱን ጨምሮ 48ቱ የቻለ ግን እስካሁን ካሊፎርኒያ፥ አሜሪካ 2007 ዓ.ም ሳይንቲስት ኢንጂነር ሻጊዝ እጅጉ ራሱን ስቶ ከተኛበት የማደንዘዣ ክፍል ውስጥ ከሰመመኑ ከነቃ ከሰዓታት በኋላ አንድ ከዚህ ቀደም አይቶት የማያውቅ ጠይም ዶክተር ቆሞ በጭንቀት እየተመለከተው ነበር። ብሰ፡፡ እንኳን በሰላም ነቃህ፤ ኢንጂነር ሻጊዝ አለ ዶክተሩ ፈገግ ከነቃሁ እኮ ቆይቻለሁ......ሆኖም ስለፈገግታህ አመሰግናለሁ" አለው ኢንጂነር ሻጊዝ ዓይኖቹን ገርበብ እንዳደረገ፡፡ “እኔም አመሰግናለሁ ኢንጂነር ሻጊዝ፡፡ በእርግጥ ግራ ተጋብቼ ስለነበር ያከምኩትን ገምተኛ ከሰመመኑ ሲነቃ መቀበል በሚባኝ ብሩህ ፊት ስላልተቀበልኩ ይቅርታህን እለምናለሁ። በሽተኞችን የሚፈውሳቸው ከዶክተሩ የህክምና ርዳታ ይልት ብሩህ ፊቱና ፈገግታው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የደመቀ ፈገግታና የፈካ ፊት የማይፈውሰው በሽታ የለም : አለ : ጠይሙ ዶክተር። ፊቱ በብዙ ጥያቄዎች መሀል እንዳለ ያሳብቃል። ግራ መጋባት ይታይበታል፡ በምስጢር ወደ አሜሪካ ከተላከ ረዥም ጊዜ የሆነው የኢትዮጵያ ደህንነት አባል በመጨረሻ ሁሉ ነገር እንደ ጨለመበት ተረዳ፡፡ ቤቱ ተከቧል። እጅህን ስጥ ሲባል እንኳንስ እኔን አንዲት ዘለላ - ፀጉሬን ፡ አታገኟትም ሲል በስልክ ተሳልቋል። ድምፃቸው ይሰማዋል፡፡ ዳናቸው : ወደበሩ እየቀረበ ሲመጣ ሽጉጡን በራሱ ጭንቅላት ላይ ደቀነው፡፡ እቀድማችኋለሁ.....በሱ ጭንቅላት ላይ ምላጭ አልስብም......... የወንዜን - ሰው ትመስላለህ : አለው : ኢንጂነር - ሻጊዝ፡፡ “ከሐበሻ ምድር የመጣህ ሳትሆን አትቀርም፡፡ “አልተሳሳትክም አለ : በይው ዶክተር ብዙ ወረቀቶችን እያተረማመሰ፡፡ ዶ/ር ሚራዥ እባላለሁ። ወደ አሜሪካ ከመጣሁ ረጅም ጊዜ ሆኖኛል፡፡ እዚህ ሆስፒታል ውስጥ ከተቀጠርኩ ግን ጥቂት ጊዜ ነው፡፡ በዛ። ጥቂት ጊዜ ውስጥ ስላንተ የህክምና ሁኔታ አንዳንድ ነገሮችን ለማወቅ ችያለሁ የኢንጂነሩን የህክምና ሁኔታ የሚገልሁ : መረጃዎች የያዙት ብዙ ወረቀቶች እያገላበ ሰማያዊው ወንበር ላይ ተቀመጠ። በጠይም ፊቱ ላይ ያንዣበበውን የጥያቄ ደመና የሚያዘንብበት ጊዜ መድረሱን አምኗል፡፡ “ኢንጂነር ሻጊዝ... ከአሁን በፊት ብዙ ጊዜ የልብ ቀዶ ጥገና ማድረግህን ያወኩት በቅርቡ ባገኘሁት ምስጢራዊ ሰነድ ላይ Auther Name:yesmaheke werkue


Type:Social
👁 :
Ethiopian announces additional passenger flight to India’s Chennai
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/27/2024
Posted By:utopia online

Ethiopian Airlines, the largest African carrier, today announced it will increase its weekly passenger flight to Chennai, Tamil Nadu, India. In a statement published on its social media pages, the Airline reminded that it will add one more additional flight to Chennai, serving its fourth passenger flight destination city in India four times a week. The latest schedule, according to the airline, will be effective as of October 27, 2024. On the 30th of July 2024, Ethiopian Civil Aviation Authority (ECAA) and Indian Ministry of Civil Aviation have signed a memorandum of understanding (MoU) to increase the number of destinations of Ethiopian Airlines in India. The newly signed MoU between both sides will enable Ethiopian Airlines to add three flights to and from Hyderabad, India. According to the Ethiopian Embassy in New Delhi, the MoU will enhance the capacity entitlement of Ethiopian Airlines from 35 to 38 services per week in each direction.


Type:Technology
👁 :
Addis-based Boeing’s Africa Office to Commence Operation in October
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/27/2024
Posted By:utopia online

Addis Ababa-based Boeing’s Africa office will begin operations in October, Boeing Africa Managing Director Henok Teferra announced. Recall that the aerospace company revealed it was in the process of opening its African headquarters in Addis Ababa, Ethiopia. Following the announcement, the Managing Director told ENA that the company’s office will officially start its operation in October 2024. Henok stated that the American aerospace company decided to open its African headquarters in Addis Ababa considering the successful work Ethiopia is achieving in the aviation sector and its African hub status. The opening of Boeing Company’s African office in Addis Ababa will enable Boeing to further strengthen and expand its cooperation with Ethiopian Airlines in various sectors, he explained. The opening of the office will also create more opportunities for Ethiopia to strengthen and maintain its status as Africa’s aviation center, the Managing Director added. Boeing will cooperate with Ethiopian Airlines, especially to strengthen cooperation for joint production of aircraft components, he pointed out. Boeing and Ethiopian Airlines have formed a strategic partnership to manufacture critical aircraft components in two sectors, he stated, pointing out that Ethiopian Airlines has been manufacturing and supplying wire harnesses for Boeing and Boeing is supporting Ethiopian to produce insulation blankets at the Kilinto Industrial Park in Ethiopia. As a leading global aerospace company, Boeing develops, manufactures and services commercial airplanes, defense products and space systems


Type:Technology
👁 :
Japan’s Fukushima-1 Water Discharge Meets Global Safety Standards
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/27/2024
Posted By:utopia online

The release of treated water from Japan’s Fukushima Daiichi Nuclear Power Station remains in line with international safety standards, the International Atomic Energy Agency (IAEA) said on Thursday. “The discharge of treated water from Japan’s Fukushima Daiichi Nuclear Power Station (FDNPS) continues to comply with international safety standards, the International Atomic Energy Agency (IAEA) Task Force confirmed today,” the IAEA said in a statement. This was confirmed in its second report since the water release started in August 2023. Approximately 55,000 cubic meters of water have been discharged up to now, with the seventh batch completed on July 16, according to the statement. “IAEA expert analysis of the seven batches released have confirmed the tritium concentration in each batch of ALPS treated water released to date is far below Japan’s operational limit,” the statement read. Japan started releasing part of the estimated 1.34 million tonnes of Fukushima nuclear power plant treated water into the ocean in August 2023. Treated water is cleared of radioactive substances aside from tritium, so the water is diluted to a lower concentration before being discharged. The entire water release process is expected to take at least 30 years.


Type:Technology

Page 85 of 99