Entertailment Page

Entertainment






👁 :
ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት የ3 ሺህ ሜትር የወንዶች መሰናክል ፍጻሜ ዛሬ ይካሄዳል
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/07/2024
Posted By:utopia online

በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ የዛሬ መርሐ-ግብሮች ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የፍጻሜ እና የማጣሪያ ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡ በዚሁ መሠረት ምሽት 4 ሠዓት ከ43 ላይ በሚካሄደው 3 ሺህ ሜትር የወንዶች የፍጻሜ ውድድር÷ አትሌት ለሜቻ ግርማ፣ ሳሙኤል ፍሬው እና ጌትነት ዋለ ይሳተፋሉ፡፡ እንዲሁም ቀን 6 ሠዓት ከ10 ላይ በሚካሄደው 5 ሺህ ሜትር የወንዶች ማጣሪያ አትሌት ሐጎስ ገብረ ሕይወት፣ ቢንያም መሐሪ እና አዲሱ ይሁኔ ተሳታፊ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል እንዲሁም ትናንት በተካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ከምድቧ ያላለፈችው አትሌት ብርቄ ሓየሎም ዛሬ ቀን 7 ከ45 ላይ በድጋሚ በማጣሪያው የምትወዳደር ይሆናል፡፡ በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምክ ኢትዮጵያ እስከ አሁን ሁለት የብር ሜዳሊዎችን በመያዝ 52ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ አሜሪካ፣ ቻይና፣ አውስትራሊያ እና ፈረንሳይ በቅደም ተከተል ከ 1 እስከ 4 ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡


Type:News
👁 :
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ ከግብፅ አምባሳደር ጋር ተወያዩ
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/07/2024
Posted By:utopia online

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ ከግብፅ አምባሳደር መሀመድ ኦማር ጋድ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸው ÷በሁለትዮሽ፣ቀጠናዊ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ ሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸውና በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ እንዲሁም አልሸባብ በሶማሊያና በቀጣናው ባሳድረዉ ስጋት ላይም ምክክር ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ውይይቱ በድህረ-አትሚስ ተልዕኮ እና በኢትዮጵያ ፍላጎቶች ላይ ያተኮረ እንደነበር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡


Type:Social
👁 :
ኢትዮጵያ በተለያዩ ርቀቶች የምትሳተፍበት የማጣሪያ ውድድሮች ዛሬ ይደረጋሉ
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/02/2024
Posted By:utopia online

በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች የሚሳተፉባቸው የማጣሪያ ውድድሮች ዛሬ ይደረጋሉ። በዚሁ መሠረት ቀን 6 ሠዓት ከ5 ላይ በ1 ሺህ 500 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ አትሌት ሳሙኤል ተፈራ፣ ኤርሚያስ ግርማ እና አብዲሳ ፈይሳ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡ እንዲሁም ምሽት 1 ሠዓት ከ10 ላይ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ መዲና ኢሳ እና እጅጋየሁ ታዬ ይሳተፋሉ። በሌላ መርሐ-ግብር ደግሞ ምሽት 2 ሠዓት ከ45 ላይ በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ፅጌ ዱጉማ፣ ሀብታም ዓለሙ እና ወርቅነሽ መለሰ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ።


Type:Social
👁 :
በሕንድ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 93 ደረሰ
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/02/2024
Posted By:utopia online

በሕንድ ደቡባዊ ግዛት ኬራላ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 93 ሲደርስ ፤ ብዙዎች ከመሬት ስር ተቀብረው ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል፡፡ እየተከናወነ ያለውን የነፍስ አድን ሥራም ከባድ ዝናብና የድልድይ መደርመስ እያስተጓጎለው መሆኑን ተከትሎ አደጋው በተከሰተበት ሥፍራ ያሉ ዜጎችን ለማውጣት አዳጋች እንዳደረገው ተሰምቷል፡፡ በዚህም አደጋ የሟቾች ቁጥር ያሻቅባል የሚል ስጋት እንዳለ የተገለጸ ሲሆን፥ ይህም በአካባቢው በፈረንጆቹ 2018 ከደረሰው ከባድ የጎርፍ አደጋ በኋላ አስከፊው ነው ተብሏል፡፡ የነፍስ አድን ሥራ ለመስራትም ከ200 በላይ የሠራዊት አባላት መሰማራታቸውም ነው የተጠቆመው፡፡ የሀገሪቱ አንድ ባለስልጣን በሰጡት መግለጫም፥ የደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ መላውን አካባቢ ጠራርጎ ወስዶታል ብለዋል፡፡ በአካባቢው ባሉ ሆስፒታሎችም ቢያንስ 123 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፥ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከአካባቢው እንዲለቁ በማድረግ ወደ 45 የእርዳታ ካምፖች መግባቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡ ከክስተቱ በኋላ በተደረገ አሰሳም የ16 ሰዎች አስከሬን በወንዝ ውስጥ መገኘቱ የአደጋውን አስከፊነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ግዛቲቱ በተለይ በክረምት ወራት ለመሬት መንሸራተት አደጋ የተጋለጠች መሆኗም ይገለጻል፡፡


Type:News
👁 :
በጋምቤላ ክልል የባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ እየተካሄደ ነው
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/02/2024
Posted By:utopia online

በጋምቤላ ክልል የባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ እየተካሄደ ነው። የባለድርሻ አካላቱ የፖለቲካ ፓርቲ፣ ሶስቱ የመንግስት አካላት፣ ማህበራትና ተቋማት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተመረጡ 60 ተወካዮች ናቸው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም እንደተናገሩት÷ ከባለድርሻ አካላት የምክክር ምዕራፍ ለክልሉም ሆነ ለሀገር የሚጠቅሙ እንዲሁም መግባባት ላይ የሚያደርሱ ሀሳቦችና አጀንዳዎች ይጠበቃሉ። ተወካዮቹ በአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ ሂደቱ ላይ ጥሩ አስተዋጽኦ ለማድረግና መግባባት ላይ ለመድረስ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል። ሰላምን በማረጋገጥ ልማትን በማምጣት ለትውልድ የሚሻገር ስራ ለመስራት በዚህ የምክክር ምዕራፍ የሚዋጣው ሀሳብ ወሳኝነት እንዳለውም አስገንዝበዋል። ምክክሩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን÷ ባለድርሻዎች አጀንዳዎቻቸውን ለይተውና አደራጅተው ለኮሚሽኑ ያስረክባሉ ተብሎ ይጠበቃል።


Type:Social
👁 :
የአውሮፓ ሕብረት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሽከርካሪዎች ድጋፍ አደረገ
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/02/2024
Posted By:utopia online

የአውሮፓ ሕብረት ዘጠኝ ተሽከርካሪዎችን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስረክቧል፡፡ የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትሕ አስተዳደርን ለመደገፍ በሚደረገው እንቅስቃሴ የተለያዩ የድጋፎች ማዕቀፎችን የያዘ ፕሮጀክት ቀርፆ በትግባራ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ሮናልድ ኮቢያ ለመስክ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎችን ለፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት አስረክበዋል፡፡ አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በዚሁ ወቅት ÷ የአውሮፓ ሕብረት በፍርድ ቤቱ የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሪፎርም ላይ የሚያደርገው ድጋፍ የዳኝነት ስርዓቱ ላይ ደጋፊ ሚና እንዳለው በመግለጽ አመስግነዋል፡፡ አምባሳደር ሮናልድ ኮቢያ በበኩላቸው በአውሮፓ ሕብረት ለፍርድ ቤቱ የተደረገው የተሽከርካሪ ድጋፍ ከታቀደው አንፃር አነስተኛ መሆኑን ገልጸው ፥ የፍትሕ ዘርፉን ለመደገፍና ለማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ የርክክብ ሥነ-ስርዓት ከተከናወነ በኋላ ፍርድ ቤቱ በቅርቡ ያስገነባውንና የዳኝነት አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ በታገዘ ሁኔታ ለመስጠት የሚያስችለውን ስማርት ኮርት ሩም የሥራ ሃላፊዎቹ መጎብኘታውን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡


Type:News
👁 :
Wami Biratu
Catagory:Biography
Author:
Posted Date:07/31/2024
Posted By:utopia online

ዕድሎች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ዕውቀት ለመቅሰምና የበለጠ ግንዛቤ ለማግኘት የቻሉ አንዳንድ | ኢትዮጵያውያን አሉ:: እነዚህ ኢትዮጵያውያን ያገኙትን ዕውቀት ለወገኖቻቸው ለማድረስና አዳዲስ አሠራርንና አስተሳሰብን በሕዝባችን መካከል ለማስረጽ አብዝተው የደከሙና ሕይወታቸውን አሳልፈው እስከ መስጠት የደረሱ ፋና ወጊ ግለሰቦች እንደሆኑም እንደነበሩም ይታወቃል። ሀገራቸውን ከውጭ ወራሪና ጠላት በመከላክል አኩሪ ታሪክ የሠሩ፣ የሕዝባቸው ደኅንነትና አንድነት እንዲጠበቅ ለማድረግ መስዋዕትነት የከፈሉና አንፀባራቂ ታሪክ የሠሩ ጥቂቶች አልነበሩም፤ አይደሉምም: በደራሲነት፣ በሙዚቃ፣ በሥዕል፤ በስፖርት፤ በታሪክ፣ በሳይንስና በእምነት አስተምሮ፣ የኪነ ጥበብና የምርምር ሥራዎችም ኢትዮጵያን በዓለም የበለጠ እንድትታወቅ ያደረጉ ትናንትናም ዛሬም ደምቀው የሚታዩ ደማቅ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ብዙዎች ናቸው:: ከእነዚህ የሀገር ባለውለታ ግለሰቦች መካከል ኢትዮጵያ በስፋት በምትታወቅበት የአትሌቲክስ ስፖርት በተለይ በረዥም ርቀት አትሌክስ በርካታ ውድድሮችን በማሸነፍ ታሪክ መሥራት የቻሉ አንጋፋው አትሌት ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ አንዱ ናቸው። «ኢትዮጵያ ሕዝብና ለሀገሬ በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት ሬሳዬ የሚወጣው ከሩጫ ሜዳ ነው የሚሉት አትሌት ዋሚ፣ የተወለዱት ጥር ህ ቀን 1907 ዓ.ም ነው:: የአቶ ቢራቱ በራቴ እና የወይዘሮ ወርቄ እያና ልጅ የሆኑት ዋሚ፣ የትውልድ ስፍራቸው ከአዲስ አበባ ከተማ በ2 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ሱሉልታ ወረዳ አካኮና መነ አብቹ በተባለው ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ነው::ዋሚ የለድስት ወንዶችና የአምስት ሴት ልጆች አባት፣ ከ20 በላይ ልጆች አያትና ከwo በላይ ልጆች ቅድመ አያት ናቸው:: በኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ስፖርት ታሪክ ፈር - ቀዳጅ ከሆኑት መካከል አንዱ የሆኑት አትሌት ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ በራቱ፣ ዛሬ በ7ኛ ዓመት ዕድሜያቸው መጀመሪያ ላይ ናቸው : ሞሚ፣ ጠንከር እያሉ ሲመጡ በመንደራቸው ላይ ቤተሰባቸውን ከብት በመጠበቅ እንዲሁም አንዳንድ የእርሻ ሥራዎችን በማከናወን ይረዱ ነበር። ተሮጦ ዝነኛ እንደሚኮን አንዲሁም ሰዎችን ሌሎች ተፎካካሪዎችን መብለጥ እንደሚችሉ ያውቁት ባጋጣሚ ነበር። በሩ ህገር ማስጠራት እንደሚቻልም እንደዚሁ። አጋጣሚውን የፈጠሩት ደግሞ እናታቸው ናቸው። ወይዘሮ ወርቄ፣ አንዳንድ ነገሮች ለመሸማመት ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ። አስፈላጊውን ሁሉ ካከናወኑ በኋላም ወደ ቀዬአቸው ይመለሳሉ። ልጅ ዋሚ ደግሞ እናታቸው ሸክፈው የመጡትን እቃ ተቀበለው ወደ ቤት ይገባሉ። በዚህ እቃ ተጠቅልሎብት የመጣ ጋዜጣ እጃቸው ላይ ይገባል። ጋዜጣው የአንድ ሯጭ ምስልን ይዟል። ዋሚ ደግሞ በመንደራቸው ጋራ ተራራውን፣ ቁልቁለት ዳገቱን በሩ ሲቦርቁ ነው የሚውሉት። ሩጫ ስፖርት መሆኑን ተገንዝበውም እርሳቸው ጥሩ ሯጭ መሆን እንደሚችሉ በማመናቸው ልባቸው ይህን ማድረግ ይመኝ ጀመር።ይህ ከሆነ ከሁለት ዓመት በኋላ ወንድማቸውን ሊጠይቁ ወደ አዲስ አበባ ጎራ አሉ። የወንድማቸው መኖሪያ አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ ሲሆን፣ በዚያች ገጠመኝም አዲስ ወታደሮች ሲመለመሉ ተመለከቱ። ምልመላውን ቆመው ሲመለከቱ እንድ ሃምሳ አለቃም ዋሚን ለምን አትገባም ብሎ ጥያቄ አቀረቡላቸው። ከመስከረም 5 ቀን 1945 ዓ.ም ጀምሮ ወታደር ሆነው ተቀጠሩ። ስልጠናቸው ሲጨርሱ ዋሚ ሁለተኛ ከፍለ ጦር ተመድበው ወደ አስመራ ሄዱ። በወቅቱ ምልመላ ወታደሮችና ነባሮች በህብረት ሩጫ ይወዳደሩ ነበር። በ ኪሎ ሜትር ዋሚ አንደኛ ሆነው ማሸነፍ ቻሉ። በዚህም ምክንያት ስፖርት ላይ በመደበኛነት ቆዩ። 1947 ዓ.ም ለዋሚም ሆነ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዩ ዓመት ነበር። ለሜልቦርን ኦሎምፒክ ማጣሪያ የሙሉማራቶን ውድድር ተዘጋጀ:: ከዚያ በፊት ማራቶን ተብሎ ይሮጥ የነበረው 5 ኪሎ ሜትር ብቻ ነበር። በዚህ ዓመት ግን ማራቶኑ በመደበኛ 42 ኪሎ ሜትር ከ950 ዓ.ም ሊሮጥ ተወሰነ። እያንዳንዱ ክፍለ ጦር ሶስት ሶስት ተወዳዳሪ ተመርጦ ከ8ኛ ክፍለ ጦሮች 24 ተወዳዳሪ ተመረጠ። በኋላ ግን የጦር ኃላፊዎቹ የሚፈልግ ሁሉ ይሩጥ ብለው እዘዘ። የተወዳዳሪዎቹ ቁጥር 50 ደረሰ። ውድድሩ ተጀመረ፤ ዋሚ ያለ ምንም ችግር አንደኛ ሆነው አሸነፉ በቦታው የነበሩት ንጉሠ ነገሥቱ አፄ ኃይለሥላሴ ለአሸናፊዎቹ ዋንጫ እንዲሰጥ እዘዙ። ቀድሞ በአምስት ሺህ እና በo ሺህ አሸንፈው የነበሩት ዋሚ ሶስት ዋንጫ ተሸለሙ። በማራቶኑ ውድድር ዋሚን ተከትለው ሁለተኛ እና ሶስተኛ የሆኑት ነጋሽ ቤኛ እንዲሁም ገብሬ ብርቄ አንድ እንድ ዋንጫ ተሸለሙ። የመጀመሪያው የማራቶን ውድድር በዋሚ ቢራቱ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በተዘጋጀው የማራቶን ውድድር አሸናፊ የሆኑት አትሌት ሻለቃ ዋሚ ቢራቱ ናቸው። ከዚያን በኋላ እነ አበበ ቢቂላ ማሞ ወልዴ መድረኩን ነግሰውበታል።ይሁንና የዋሚ እና የመጀመሪያው መሥሪያ ቤታቸው ጦር ኃይሎች ጋር ብዙም መቆየት አልቻሉም ነበር። በአጋጣሚ ከቀዬአቸው ውጥተው የጦር ኃይሎች አባል የሆኑት ዋሚ ቤተሰቦቻቸውን ለማየት ፈቃድ ጠየቀ። የፈቃድ ጥያቄው ግን ተቀባይነት አላገኘም ነበር። ዋሚና ጦር ኃይሎች ተኳረፉ። በዚህ የተነሳ በ1948 ዓ.ም ዋሚ ክብር ዘበኛ ተቀጠሩ። 1949 ዓ.ም በልዑል መኮንን ሞት እንዲሰረዙ ተደረገ። ከ950 እስከ 1952 ዓ.ም በእምስት ሺህ በ ሺህ እና በማራቶን ዋሚን የሚረታ ጠፋ። በተለይ በ1952 ዓ.ም ኖሚ፣ የማራቶን አንደኛነቱን ሲይዙ አበባ በቂላ 2ኛ ሆኖ ጨረሰ። ስለዚህም ዋሚ ቢራቱ እና አበበ ቢቂላ በሮም ኦሎምፒከ ኢትዮጵያን እንዲወከሉ ተመረጡ። በወቅቱ ይህንን ሁሉ ስኬት ሊያስመዘግቡ ፌዴሬሽንም ሆነ አሰልጣኝ አልነበራቸውም፡፡ የስፖርት ትጥቅ የሚባል ነገርም አንደዚሁ። ይሁንና ዋሚ ራሳቸውንም ሆነ አበበ ቢቂላን አያሰለጠኑ አዲስ ታሪክ መስራቱን ቀጠሉ:: በወቅቱ በኦሎምፒከ ሕግ መሠረት አንድ ሰው አሰልጣኝም ተወዳዳሪም መሆን ስለማይችል አሰልጣኝ መቅጠር ግድ ሆነ። ስለዚህም ስዊዲናዊው ሜጆሮኒ ስካና አበበን እና ዋሚን ለማሰልጠን ተቀጠሩ። ስዊዲናዊው እሰልጣኝ በጥቂት ጊዜ ውስጥ የዓለም ምርጥ አትሌቶች የሚሆኑ ብላቴናዎችን እያሰለጠኑ መሆንን ለመረዳት ጊዜ አልወሰደባቸውም።እኚህ የባህር ማዶ አሰልጣኝ፣ ቢአበበ እና በዋሚ ኢትዮጵያ አማካኝነት በረጅም ርቀት ሩጫ ድል እንደምታስመዘግብ ርግጠኛ ሆነው ነበር። ይህንንም ለንጉሡ በወቅቱ ቀርሰው ተናግረው ነበር። ይሁንና ያን ሁሉ ተስፋ ተጥሎባቸው የነበሩት ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ በድንገት ታመሙ። የሮም ኦሎምፒክ ውድድር ስድስት ቀን ሲቀረው ኢትዮጵያ የተማመነችባቸው ጀግና 9 ቦታ ብጉንጅ ወጣባቸው። አሰልጣኙ ሁለተኛውን ምርጥ አትሌታቸውን አበበ ቢቂላን ለማሳለፍ ተገደዱ። ስለዚህም አበበ በሮም ጎዳናዎች ታላቁን ተልእኮ ለመሸከም እና ለመፈውም ተገደደ። አበበ ኢትዮጵያን ሮም ላይ ወከሎ ሮጠ። ኢትዮጵያውያንን አላሳፈረም ባለድል ሆነ። በዋሚ መንገድ አበበ ቢቂላ ማሞ ወልዴ ምሩፅ ይፍጠር፤ ኃይሌ ገሥላሴ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ቀነኒሳ ቡቀለ፣ ፋጡማ ሮባ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ ጌጤ ዋሚ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰረት ደፋር፣ ስለሺ ስህን ገንዘቤ ዲባባ የመሳሰሉ ጀግኖች መፍራታቸውን ብዙዎች ይናገራሉ። ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ፣ በተለያዩ የሩጫ መድረክ ላይ ሀገራቸውን ያስጠሩበት ድል አስመዝግበዋል። ከነዚህ መካከል በአንድ ሺsoo ሶስት ሺ፣ አምስት ሺ፤ 10ሺ፣ 2ኪሎ ሜትር፣ 25 ኪሎ ሜትር፣ ብ32 - ኪሎ ሜትር በሀገር አቋራጭ እና የተለያዩ የማራቶን ውድድሮች ላይ በመሳተፍ 5 የወርቅ፣ 44 የብር እና 30 የነሀስ ሜዳሊያዎችን ማገኘት ችለዋል። ከዚህም ሌላ 2 ሰርተፍኬት፣ አራት ዲፕሎማ እና ከ40 በላይዋንጫዎችን ወስደዋል። በተለያየ ወቅትም የኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አስችለዋል። የሶምሶማ ሩጫ በሀገራችን እንዲለመድ ለማድረግ ጥረት ያደረጉ መሆናቸውም ይነገርላቸዋል። ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ፣ በጃፓን ቶኪዮ ማራቶን ተሳትፎ አድርገው ከአበበ ቢቂላ በመቀጠል 2ኛ ሲወጡ ያጋጠማቸው ሁኔታ በግላዊ የሕይወት ታሪካቸው ውስጥ ጉልህ ሥፍራ አለው:: 42 ኪሎ ሜትር ከ90 ሜትር ይሸፍን የነበረውን ርቀት እስከ 40ኛው ኪሎ ሜትር ድረስ ሲመሩ ቆዩ። ነገር ግን ከነበረው ሙቀት የተነሣ እግራቸው መላላጥ ጀመረ:: የሚሮጡት ባዶ እግራቸውን ነበርና ይፈስ የነበረው ደም የሚሮጡበትን መንገድ አቀሰመው:: ሆኖም መሮጣቸውን ቀጠሉ፤ አበበን አሳልፈው ሁለተኛ ወጡ። በመላላጥ ለተጐዳው እግራቸውም የጃፓን ሐኪሞች ወደ ሆስፒታል ወስደው የሕከምና ርዳታ አደረጉላቸው:: ይህንን የተመለከቱ የሀገሪቱ ጋዜጠኞችም፣ «የኢትዮጵያዊው አትሌት የዋሚ ቢራቱ እግር የሰው አይደለም ብለው ጻፉ:: ይህም ከረጅም ዓመታት በፊት ገጥሟቸው ለነበረውና እርሳቸውም ለሰጡት ምላሽ ሌላ ትውስታን ይጭራል፦ እኚህ ፋና ወጊ አትሌት በእግራቸው ሲጓዙ፣ ጎረቤታቸው የሆኑት አንድ ኮሎኔል ያገኟቸውና፣ “ዋሚ ና በመኪና ልሸኝህ" ቢሏቸው፣ «የለም እቸኩላለሁ፤ ከእርስዎ ኮሣሣ መኪና ይልቅ የእኔ እግር ይሻላል → በማለት የሰጡት ምላሽ እስከ ዛሬም ድረስ የሚወሳ የታሪካቸው አካል ሆኗል:: ጊዜው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1960 ሮም ፣ አበበ ቢቂላ የሮም ማራቶንን አሸነፈ። በመግቢያው ጫፍ ያገኘው ጋዜጠኛ - “በማሸነፍህ ምን ተሰማህ?አበበ - “እኔ አይደለሁም አሸናፊ፣ አሸናፊው ቤቱ ታሞ ተኝቷል” ሲል መመለሱ ይታወሳል:: በወቅቱ ለኦሎምፒክ የተደረገውን የሀገር ውስጥ ማጣሪያ ዋሚ ቢራቱ በባዶ እግር ሮጦ አንደኛ ሆኖ ቢያጠናቅቅም በህመም በሮም ኦሎምፒክ መሳተፍ አልቻለም ነበር። አበበ ቢቂላ፣ ለጓደኛው ያለውን ከብር እና አድናቆት በሌለበት ለግሷል። ጀግና እያንዳንዱ ድርጊቱ ከራስ ወዳድነት የተሻገረ ነው። እንዲህ የተባለላቸው የኢትዮጵያ የማራቶን አባት ጋሽ ዋሚ ቢራቱ፣ ዛሬ 107 ዓመት ሞልቷቸዋል። አንደበታቸውአሁንም አይጠገብም ዛሬም አመስጋኝ የሀገራቸው እና አህጉራቸውን ድል ናፋቂ ናቸው። በ1896 እኤአ ላይ የግሪኳ _ አቴንስ ከተማ ካስተናገደችው የመጀሪያው ኦሎምፒድ አንስቶ ባለፉት 128 ዓመታት ውስጥ በተካሄዱት 32 ኦሎምፒያዶች ኢትዮጵያ በ4 ተሳትፋለች:: በኦሎምፒክ መድረከ ሁሉንም ሜዳልያዎችን የሰበሰበችው በአትሌቲክስ ስፖርት ብቻ ሲሆን፣ በከፍተኛ የውጤት ታሪካቸው ከሚጠቀሱ ስምንት ሀገራት አንዷ ናት። አፍሪካን በመወከል ደግሞ ከኬንያ ቀጥሎ ከፍተኛውን ስኬት አስመዝግባለች ኦሎምፒክ የዓለም ሀገራትና ሕዝቦቻቸውን በአንድ መንፈስ የሚያስተባብር መድረክ ነው:: በስፖርት መድረኩ በድህነት የተጎሳቆሉ፤ በበቂ የስፖርት መሠረተ ልማት ዝግጅታቸውን ያላከናወኑ፤ በየሀገራቸው ባሉ የፖለቲካ አለመረጋጋቶች የተረበሹ፤ በጦርነት እና በኢኮኖሚ ቀውስ የሚገኙ ሀገሮቻቸውን የወከሉ ኦሎምፒያኖች ሲሳተፉ ሁሉምአንድ ዓላማይኖራቸዋል:: ይህ ዓላማ በሜዳልያ ከብር ሀገራቸውን ማኩራትና ሰንደቅ አላማቸውን ማውለብለብ ነው:: የኦሎምፒክ የሜዳልያ ክብር መጎናፀፍ ደግሞ የየትኛውም የዓለም ስፖርተኛ ህልም እንደሆነ ይታወቃል። ባሳለፍነው ሳምንት በተጀመረው በፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በ800 ሜትር ሴቶች፣ በአንድ ሺህ 500 ሜትር ወንዶች፤ በአንድ ሺህ 5o0 ሜትር ሴቶች፣ በአምስት ሺህ ሜትር ወንዶች፣ በአምስት ሺህ ሜትር ሴቶች፣ በo ሺህ ሜትር ወንዶች፣ በo ሺህ ሜትር ሴቶች፤ በሶስት ሺህ ሜትር የወንዶች መሰናከል፣ በሶስት ሺህ ሜትር የሴቶች መሰናከል፣ በሴቶች ማራቶን፣ በወንዶች ማራቶን እና በ20 ኪሎ ሜትር የወንዶች የርምጃ ውድድር የምትካፈል ይሆናል። እኛም መልካም ዕድል ለኢትዮጵያ እንመኛለን። እኛም በዚህ የሀገርና የሕዝብ ባለውለታ የሆኑ ግለሰቦች በሚመሰገኑበት ዓምዳችን ወቅቱን በማስታወስ በአትሌቲክስ ስፖርት ዘርፍ ለኢትዮጵያ አርአያ በመሆን ከሮም ኦሎምፒክ ጀግናው አበበ ቢቂላ ዘመን ጀምሮ ለበርካታ አትሌቶች የጽናት ምልክት በመሆን የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ባሻ ዋሚ ቢራቱን አመሰገንን ሰላም!


Type:Social
👁 :
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከ7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ አገኘ
Catagory:News
Author:
Posted Date:07/31/2024
Posted By:utopia online

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2016 በጀት ዓመት 7 ነጥብ 02 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ÷ አየር መንገዱ የዓለም አቀፍ መዳረሻውን ወደ 139 ማሳደጉን ተናግረዋል፡፡ የሀገር ውስጥ በረራ መዳረሻውም 22 መድረሱን ነው የገለጹት፡፡ ፈጣን፣ ተመራጭ እና አስተማማኝነቱን እያረጋገጠ የመጣው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእድገት ጉዞው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡ የያቤሎ፣ ሚዛን አማን፣ ጎሬ መቱ፣ ነጌሌ ቦረና እና ደብረ ማርቆስ የአውሮፕላን ማረፊያዎች በቀጣይ ዓመት አጋማሽ ጀምሮ አንደሚጠናቀቁ ተመላክቷል፡፡


Type:Technology

Page 94 of 99