Entertailment Page

Entertainment






👁 :
የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ የ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ብድር አጸደቀ
Catagory:News
Author:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አስፍጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ ለአራት ዓመት የ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የተራዘመ ብድር አገልግሎት አቅርቦትን አጽድቋል፡፡ አይ ኤም ኤፍ ጉዳዩን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አስፈጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ የሚሆንና መጠኑም 2.556 ቢሊየን SDR (የኮታው 850% ወይም ወደ 3.4 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ) የሆነ፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መፋለስን መፍታትን እና በግል ዘርፉ ለሚመራ እድገት መሠረት መጣልን አላማው ያደረገውን የመንግሥትን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አፈጻጸም የሚደግፍ የአራት ዓመት የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት(ECF) አጽድቋል። የአስፈጻሚ ቦርዱ ውሳኔም ኢትዮጵያ ከባላንስ ኦፍ ፓይመንት ጋር የተያያዙ ፍላጎቶቿን እንድታሟላ የሚረዳትን እንዲሁም በጀቷን የሚደግፈውን የ766.75 ሚሊየን SDR ወይም 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ክፍያ ወዲያውኑ እንዲለቀቅ የሚያስችል ይሆናል። በአራት ዓመቱ የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት የሚደገፈው የመንግሥት የኢኮኖሚ ፕሮግራም የግል ዘርፉን እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ ሁለገብ የፖሊሲ ፓኬጅን እንዲሁም የላቀ እና በይበልጥ አካታች የሆነ እድገትን ማምጣትይቻል ዘንድ ኢኮኖሚውን ክፍት ማድረግን ኢላማው ያደረገ ነው። ማሻሻያው ተጋላጭ በሆኑ ቤተሰቦች/አባዎራዎች ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ ለማለዘብ ይቻል ዘንድ የማህበራዊ ሴፍቲ ኔቶችን ማጠናከርም የመንግሥት የማሻሻያ ፕሮግራም አንድ ወሳኝ ክፍለአካል ነው። ቁልፍ የሚባሉት ፖሊሲዎችም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ 1) ውጫዊ ኢሚዛናዊንትን ለመፍታት እና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለማስታገስ በገበያ ወደሚወሰን የምንዛሪ ዋጋ መሄድ፤ 2) የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍን በማዘመን የዋጋ ግሽበትን መዋጋት፤ 3) የሀገር ውስጥ የገንዘብ ምንጮችን በማሰባብሰብ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ሕዝባዊ ወጪዎች ማዋል፤ 4) ከውጪአበዳሪዎች ጋር የሚደረጉ ወቅታዊ የእዳ ሪስትረክቸሪንግ ስምምነቶችን በመፈጸም ጭምር የእዳ አከፋፈል ዘላቂነትን መመለስ እንዲሁም 5) ወሳኝ የሆኑ የማክሮ ፋይናንሺያል ተጋላጭነቶችን ለመቀነስ የመንግሥት ኢንተርፕራይዞችን የገንዘብ አቋም ማጠናከር። ፕሮግራሙ ከልማት አጋሮች የሚገኝ ተጨማሪ የገንዘብ አቅርቦትን በማፋጠን እንዲሁም በመካሄድ ላይ ያለው የእዳ ሪስትረክቸሪንግ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የሚያደርግ ማዕቀፍ በመስጠት ረገድ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።


Type:News
👁 :
Automatic Test Equipment and Why They are Widely Used?
Catagory:Education
Author:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

The need to offer high-quality standard while improving functionalities has pushed manufacturers toward automatic test equipment (ATE) that are reliable and guarantees repeatability. ATEs aid manufacturers to perform several accurate tests and reducing the incidence of failures and errors, offering test results faster than the conventional manual testing methodology. For the years to come, the global automatic test equipment market is expected to boom owing to advancements in technologies, innovation in highly integrated electronic components, and the emergence of complex electric devices. What is automatic test equipment? ATE is computerized machinery that utilizes test instruments to complete and evaluate the results of functionality, quality, performance, and stress tests performed on electronic devices. Furthermore, it automates the traditional manual electronic testing processes and demands less to no human intervention. Automatic test equipment is often known as automated test equipment or automated testing equipment. On the other hand, the devices that are assessed by ATE are referred to as a device under test (DUT), equipment under test (EUT), or unit under test (UUT). Today, several electronic devices are tested by ATE to ensure the performance, functionality, and safety of those who would ultimately use them in workplaces. ATE include printed circuit boards (PCBs), integrated circuits (ICs), hard disk drives, and other several electronic systems and line-replaceable units that support aircraft, satellite, and spacecraft. How does ATE work? ATE monitors, controls, and captures data using an array of test instruments and signal sources such as digital multimeters, LCR meters, digital storage oscilloscopes, radiofrequency, and arbitrary waveform generators. A high-performance data acquisition (DAQ) computer runs special test software or DAQ software that controls the test station’s instruments and signal sources. The raw data captured by test instruments are analyzed and stored using signal sources and test software and these readings essentially determine whether the device needs correction or not. Is ATE beneficial? The purpose of ATE is to ensure the performance and functionality of electronic devices once they are in the customer’s hands. Moreover, the automatic test prevents faulty devices from entering the market. And one step further, if a fault occurs during testing procedures, ATE helps diagnose why the devices are found at fault and allows manufacturers to correct their procedures. In a long run, ATE systems help save a colossal amount of money and cut down the testing time by digitizing traditional manual testing equipment that often relies on humans. ATE system’s automation factor ensures test and cycle time by eliminating variable troubleshooting on behalf of engineers. It eliminates human intervention and thus, human errors. These systems are efficient and cost-effective and allow engineers to focus on occasional testing instead of testing every electronic device manually. Most importantly, ATE systems are much faster and offer more accurate test results as compared to manual testing that relies on the speed and skill of the engineer. In the last couple of years, the use of ATE systems has skyrocketed across various industries and companies. In fact, everything from missile launches to avionic systems is validated by automatic test equipment, and in the future, the user will surely increase even further.


Type:Technology
👁 :
Science, Technology, and Innovation
Catagory:Education
Author:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

Science, technology, and innovation are cornerstones of the American economy. They are also dominant forces in modern society and international economic development. Strengthening these areas can foster open, transparent, and meritocratic systems of governance throughout the world. The Department of State executes public diplomacy programs that promote the value of science to the general public. It also implements capacity-building programs in emerging markets that train young men and women to become science and technology entrepreneurs, strengthening innovation ecosystems globally. The Department’s efforts contribute to scientific enterprises that hasten economic growth and advance U.S. foreign policy priorities. Read more about what specific bureaus are doing to support this policy issue Office of Science and Technology Cooperation (STC): STC, part of the Bureau of Oceans and International Environmental and Scientific Affairs (OES), cultivates science, technology, and innovation (STI) ecosystems to support U.S. foreign and economic policy priorities. It leverages a wide variety of tools and foreign partnerships to strengthen STI around the world Office of the Science and Technology Adviser to the Secretary of State (STAS): STAS provides a focal point for the integration of science, technology, and innovation into U.S. foreign policy. It anticipates the foreign policy impacts of STI research and development and the effects of discoveries emerging from the high-technology and private sectors. It is a central bridge between the Department and the U.S. and global STI communities.Office of Space Affairs (SA): SA carries out diplomatic and public diplomacy efforts to strengthen American leadership in space exploration, applications, and commercialization by increasing understanding of, and support for, U.S. national space policies and programs and to encourage the foreign use of U.S. space capabilities, systems, and services


Type:Technology
👁 :
Second Annual Symposium on Accelerating Science, Technology, and Circular Innovation in Southeast Asia: Smart Cities Innovation, Biotechnology, and Circularity
Catagory:Education
Author:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

The U.S. Department of State hosted the second annual Symposium on Accelerating Science, Technology, and Circular Innovation in Southeast Asia: Smart Cities Innovation, Biotechnology, and Circularity in Vientiane, Lao People’s Democratic Republic (Lao PDR) on July 17-19. The U.S.-ASEAN Smart Cities Partnership (USASCP), Arizona State University (ASU)-implemented U.S-ASEAN Science, Technology, Innovation and Cooperation Program (STIC), and Rochester Institute of Technology (RIT) jointly developed this event, which underscored the importance of education and training, circular economy and innovation, and climate resilience to the region. The event convened public, academic, and private sector actors across multiple disciplines. Throughout the Symposium, discussions highlighted programs across multiple sectors, including Water Smart Engagements (WiSE), which pairs water utilities from U.S. and Southeast Asian cities to improve water security in ASEAN cities through sustainable water management solutions. The Symposium showcased WiSE partnerships in the Mekong sub-region, demonstrating the outcomes of the city partnerships and success in the program’s final year. These partnerships exemplify U.S. cooperation on water and natural resources management under the Mekong-U.S. Partnership (MUSP). USASCP also announced its intent to launch the Smart Cities Business Innovation Fund 2.0, capitalized at $3 million, to catalyze net zero urban innovation and sustainable business practices. ASU hosted the U.S.-ASEAN STIC business venture pitch competition and research project presentations, which culminated in the disbursement of $100,000 in awards supporting proposals that advance technology innovations across ASEAN member states. Several research proposals spotlighted biotechnology, reflecting its crucial role in advancing scientific knowledge and addressing contemporary challenges in the ASEAN region. The Circular Entrepreneurship program, a flagship initiative of RIT, expanded its training partnerships across the entire ASEAN region and presented its material flow analysis research as well as its ongoing work to better understand the role of the informal sector in the ASEAN e-waste life cycle. This integrated event with public and private sector partners demonstrated the U.S. commitment to advancing science, innovation, and resiliency across ASEAN


Type:Technology
👁 :
ላሊበላ
Catagory: History
Author:
Posted Date:07/29/2024
Posted By:utopia online

ላሊበላ በኢትዮጵያ፣ በአማራ ክልል በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሀገር የምትገኝ ከተማ ነች። በ12.04° ሰ 39.04° ምዕ ላይ የምትገኘው የላሊበላ ከተማ ከባሕር ጠለል በላይ 2,500 ሜትር ከፍታ ያላት ስትኾን የሕዝቡም ብዛት ወደ 11,152 ነው። 1 ላሊበላ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ከተማዎች መካከል ከአክሱም ቀጥላ በኹለተኛነት ደረጃ የምትገኝ ከተማ ስትኾን፣ ለአብዛኞቹ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንደ ዋና የእምነት ማእከል በመኾን ታገለግላለች። የላሊበላ ነዋሪዎች በአብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ናቸው። የላሊበላን ከተማ በዋነኛነት ታዋቂ ያረጉዋት ከክ.ል. በኋላ በ13ኛው መቶ ክፍለዘመን እንደ ተሰሩ የሚነገርላቸው 11 አብያተ-ክርስቲያናት ናቸው። በኢትዮጵያ ትውፊት መሰረት እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት በንጉሥ ላሊበላ ዘመን በቅዱሳን መላዕክት እረዳትነት እንደተሰሩ የሚታመን ሲኾን ግርሃም ሃንኮክ የተባለው እንግሊዛዊ ጸሓፊ ግን እኤአ በ1993 ዓ.ም ባሳተመውና The Sign and the Seal በተባለው መጽሃፉ አብያተ-ክርስቲያናቱን በማነፁ ሥራ ላይ ቴምፕላርስ የሚባሉት የመስቀል ጦረኞች ተካፍለዋል ሲል አትቷል ነገር ግን ማረጋገጫ አልነበረውም። እነዚሀ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ አርባ ትንንሽ ቤተ ክርስቲያኖች አሉ። ንጉሡ ላሊበላ የሚለውን ስም ያገኘው፣ ሲወለድ በንቦች ስለተከበበ ነው ይባላል። ላል ማለት ማር ማለት ሲኾን፤ ላሊበላ ማለትም -ላል ይበላል (ማር ይበላል) ማለት አንደሆነ ይነግራል። ውቅር ቤተ ክርስቲያናቱን ንጉሡ ጠርቦ የስራቸው ከመላእክት እገዛ ጋር እንደሆነ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ይነግራል። በ16ኛው ከፍለ ዘመን አውሮፓዊ ተጓዥ ላሊበላን ተመልክቶ «ያየሁትን ብናግር ማንም እንደኔ ካላየ በፍጹም አያምነኝም» ሲል ተናግሮ ነበር። በላሊበላ 11 ውቅር ዐብያተ ክርስቲያናት ያሉ ሲኾን ከነዚህም ውስጥ ቤተ ጊዮርጊስ (ባለ መስቀል ቅርፁ) ሲታይ ውሃልኩን የጠበቀ ይመስላል። ቤተ መድሃኔ ዓለም የተባለው ደግሞ ከሁሉም ትልቁ ነው። ላሊበላ (ዳግማዊ ኢየሩሳሌም) የገና በዓል ታህሳስ 29 በልዩ ኹኔታ ና ድምቀት ይከበራል፣ "ቤዛ ኩሉ" ተብሎ የሚጠራው በነግህ የሚደረገው ዝማሬ በዚሁ በዓል የሚታይ ልዩ ና ታላቅ ትዕይንት ነው።የሚደረገውም ከቅዳሴ በኋላ በቤተ ማርያም ሲኾን ከታች ባለ ነጭ ካባ ካህናት ከላይ ደግሞ ባለጥቁር ካብ ካህናት በቅዱስ ያሬድ ዜማ ቤዛ ኩሉ እያሉ ይዘምራሉ። 11ዱ የቅዱስ ላሊበላ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት 1.ቤተ መድኀኔ ዓለም፣ 2.ቤተ ማርያም፣ 3. ቤተ ደናግል፣ 4.ቤተ መስቀል፣ 5. ቤተ ደብረሲና፣ 6.ቤተ ጎለጎታ፣ 7.ቤተ አማኑኤል፣ 8.ቤተ አባ ሊባኖስ፣ 9.ቤተ መርቆሬዎስ፣ 10. ቤተ ገብርኤል ወሩፋኤል፣ 11. ቤተ ጊዮርጊስ


Type:Social
👁 :
የንጉሰ ነገስቱ እናት
Catagory:Fiction
Author:
Posted Date:07/29/2024
Posted By:utopia online

(ከተስፋዬ ገብረአብ) ሳቂታ ውብ ጥርሶችና ታማኝ አይኖች ያሏት ሸዋረጋ የምትባል አንዲት ልጅ ነበረች። ነዋሪነቷ ወሎ ላይ ነበር። ገናየስምንት አመት ህፃን ሳለች ወላጅ እናቷ ስለሞተችባት ለአንዲት አሮጊት በግርድና ለማገልገል ተቀጠረች። ይህች እድለቢስልጅ አባቷን አታውቀውም። እንጀራ ጋጋሪ ከነበረች ወላጅ እናቷ የተገኘ ውርስም አልነበራትም።አሮጊቷ በበቅሎ ሲጓዙ፣ እየተከተለች ከበቅሎዋ እኩል መስገር ዋና ስራዋ ሆነ። ምሽት ላይ የአሮጊቷን እግርታጥባለች። ማለዳ ቤት ትጠርጋለች። ገረድ እንደመሆኗ የታዘዘችውን ሁሉ ትሰራለች። በዚያን ዘመን ሰሜን ኢትዮጵያጦርነት ልማዱ ነበር። ወታደሮች ወሎን እያቋረጡ ያልፋሉ። ወታደሮች ወደ ዘመቻ ሲሄዱና ሲመለሱ ማየት ለሸዋረጋየእድገት ትዝታዋ ነው። አንዳንድ ጊዜ ስሜቷ እየተነሳሳ፣ የተቀጠረችበትን የግርድና ስራ በመተው ከወታደሮቹ ጋር ወደዘመቻ ትሄድ ነበር።በዘመኑ አስተሳሰብ ለአቅመ አዳም እንደደረሰች ከምስራቅ ኢትዮጵያ ከመጡ ወታደሮች አንዱ ሸዋረጋን ወደዳት።ምንም እንኳ ችግር ያደቀቃት ገረድ ብትሆንም፣ ቁንጅናዋን በማስተዋል፣ ልበሙሉ ፈገግታዋን በማጤን ሚስቱ አደረጋት።እሷም ቢሆን ከግርድና ይልቅ የአንድ ወታደር ሚስት መሆን እንደሚሻል በማመን ሳታመነታ ወደ ትዳር አለም ገባች።ወታደሩም ግዳጁን ፈፅሞ ሲያበቃ ሚስት ይዞ ወደ ሃረርጌ ተመለሰ። እነሆ! ያቺ ተስፋ አልባ የነበረች ምስኪን ልጅ አሁንየተሻለ ህይወት መኖር ጀመረች።አንድ ቀን ከባልዋ ጋር ሲጨዋወቱ፣“ሸዋ! ምንድነው ይሄ አንገትሽ ላይ ያለው ድግምት?” ሲል እንደ ዋዛ ይጠይቃታል።“ምንም” ትላለች።“አለምክንያትማ አላንጠለጠልሽውም?”መልስ ሳትሰጥ ዝም ትላለች፣ባሏ ጠረጠረ። መስተፋቅር ሊሆን ይችላል ብሎ ስለገመተ ወደ ንስሃ አባቱ ሄዶ ሚስቱ አንገት ላይ ስለታሰረውድግምት ይናዘዛል። ቄሱ ሚስትየውን ለማነጋገር ይፈቅዱና ባልየው በሌለበት እለት ወደቤት በመምጣት ሸዋረጋን ያነጋግሯትጀመር።“እንዲያው ይሄ አንገትሽ ላይ ያሰርሽው ምን ይሆን?”ሸዋረጋ በልቧ የያዘችው ምስጢር ቢሆንባትም፣ ቄስ ጠይቆ መልስ መስጠት ግዴታ ነውና እናቷ ከመሞቷ በፊትየነገረቻትም ምስጢር ተነፈሰች፣“እናቴ ናት ያሰረችልኝ…”“ምን ይሁንሽ ብላ አሰረችልሽ ልጄ?”“የማን ልጅ መሆኔ ተፅፎበታል ብላ ነገረችኝ…”“ማናት እናትሽ? ወዴት አለች አሁን?”“እንጀራ ጋጋሪ ነበረች። የሰባት አመት ልጅ ሳለሁ ሞተችብኝ…”“እስኪ ወዲህ በይው ልጄ?”ሸዋረጋ አንገቷ ላይ የታሰረውን ክታብ ፈትታ ለቄሱ አቀበለች። ቄሱ እያማተቡና አንዳች የማይሰማ ነገርእያጉተመተሙ የታሰረውን ክታብ በጥንቃቄ ፈቱት። የተጣጠፈውን ወረቀትም በርጋታ ዘረጋጉት። እናም አነበቡት።በማንበብ ላይ ሳሉ በድንጋጤ ብዛት ትንፋሻቸው ሊያመልጥ ምንም አልቀረውም። በተቀመጡበት ተፈንግለውእንዳይወድቁ፣ መከዳውን ደገፍ ብለው አቀርቅረው ቀሩ። ሸዋረጋ ከቄሱ ድንጋጤ ጋር አብራ ስለደነገጠች አባቷ ማንእንደሆነ እንዲነግሯት ተጣድፋ የጠቀች። ቄሱ ግን የተጠየቁትን በመመለስ ፈንታ መልሰው ለልጅቱ ጥያቄ ያቀርቡላትጀመር፣“እናትሽ ስላባትሽ ምን ነግራሻለች የኔ ልጅ?”“ምንም አልነገረችኝም፣ እሷ ስትሞት ትንሽ ነበርኩ…”“ምን ትዝ የሚልሽ ነገር አለ?”“ምንም የለም።”“መቼም ምንም አልነገረችሽም አይባልም። እስኪ አስታውሺ?”“ምንም አልነገረችኝም አባቴ። ድሃ ነሽና ከሰው ተጠግተሽ እደጊ! ካደግሽ በሁዋላ ግን ይህን በአንገትሽ ላይ በቆዳሰፍቼ ያሰርኩልሽን ወረቀት ለምታምኛቸው ሰዎች አሳዪ’ ብላኝ ሞተች…”“ከእናትሽ ጋር የት ነበራችሁ?”“ወሎ ነበርን። እስላሞች ቤት…”“እናትሽ እስላም ናት?”“ለመኖር ብዬ ነው እስላም ቤት የገባሁት ብላኛለች።”“እናትሽ ማንነበር ስሟ?”“ደስላ”ሸዋረጋ ልቧ ተሰቅሎ እንደገና ጠየቀች፣“ወላጅ አባቴ ማነው?”“አጤ ምኒልክ ናቸው የኔ ልጅ….” * * *እነሆ! ሸዋረጋ እና ባልዋ ከሃረርጌ ወደ አዲስአበባ ጉዞ ጀመሩ።አንዲት መጠጊያ ያጣች ወላጅ አልባ ሴት ያገባ የመሰለው ወታደር ከንጉሰ ነገስቱ ሴት ልጅ ጋር ጋብቻ መፈፀሙንማመን ቸግሮታል። ህይወት እድል ናት። እድል እያዋከበ ወስዶ የንጉስ ልጅ ባል አድርጎታል። በዚህ ምክንያትም ከንግዲህህይወቱ ይለወጣል። በርግጥም ሹመት እንደሚያገኝ አምኖአል። የልእልት ባል እንደመሆኑ ተራ ሰው ሆኖ ሊቀጥልአይችልም። ቢያንስ ደጃዝማችነት ማግኘት እንደሚገባው ሳያሰላስል አልቀረም። የንስሃ አባቱ የመከሩትና የነገሩትም ይህንኑነው፣“እድለኛ ነህ። ከንግዲህ ኑሮህ ይለወጣል። ሚስትህን ወደ ንጉሱ ውሰዳት። የእሳቸው ልጅ ነች…”ባላገሩ ወታደር ይህንኑ ጣፋጭ ህልም እያኘከ፣ ሸዋረጋ ምኒልክን ይዞ ከመናገሻዋ ከተማ አዲስአበባ ገባ። * * *እቴጌ ጣይቱ በጥሞና ካዳመጡ በሁዋላ፣“አስገቧቸው” ሲሉ አሽከራቸውን አዘዙ።የተጎሳቀሉ ባልና ሚስት ባላገሮች ከንግስቲቱ እልፍኝ ገብተው ለጥ ብለው እጅ ነሱ። እቴጌ ጣይቱ ልጅቱንአተኩረው መረመሯት። የእናቷን ቁንጅና ይዛ መወለዷን ሳያስተውሉ አልቀሩም። ፈገግ ስትል ፀሃይ ብልጭ ያለ ይመስላል።አይኖቿ የአባቷን እንደሚመስሉም ታዝበዋል። እናቷ ከቤተመንግስቱ ስትባረር ይህች ልጅ የ7 ወር ፅንስ እንደነበረችያስታውሳሉ። የተፈፀመውን ዝርዝር ነገር ሁሉ ያስታውሳሉ። አሁን ግን ፀፀት ቢጤ ልባቸውን ጫር ሳያደርገው አልቀረም።በርግጥ በዚያን ዘመን፣ ቅናት በልምጩ ሸንቁጧቸው የነበረ ቢሆንም በጊዜ ብዛት አሁን ያ ስሜት ጠፍቶአል።ደስላ ከወሎ የመጣች ኦሮሞ ነበረች። አንገቷ እንደ ኪሊዮፓትራ ነበር። ደርበብ ሞላ ያለች በጣም ቆንጆ። አንድ ቀን ከአጤምኒልክ ገረዶች አንዷ እመኝታ ክፍላ ድረስ በመምጣት እንዲህ አለቻት፣“የይሁዳው አንበሳ ፈልገውሻል”“ምነው በዚህ ሰአት?”ደስላ ገረዲቱን ተከትላ በጨለማ ውስጥ ወደ ንጉሱ የመኝታ ክፍል በመጓዝ ላይ ሳለች፣“ንጉሱ ለምን ፈለጉኝ?” ብላ ጠይቃ ነበር።“ወደውሻል! እድለኛ ነሽ” የሚል ምላሽ አገኘች።ንጉሰ ነገስቱ ከዚያን ቀን ጀምሮ ከዚህች ውብ የወሎ ኮረዳ ጋር የፍቅር ግንኙነት ነበራቸው። በመካከሉ ደስላፀነሰች። ማርገዟም ይታወቅ ጀመር። ሆኖም ፍርሃት ይዟት ለንጉሱ ሳትናገር ቀረች። በቤተመንግስቱ ዙሪያ የደስላ ማርገዝበሹክሹክታ ይወራ ጀመር። ከአጤ ምኒልክ ልጅ መውለድ የሚመኙ ሁሉ፣ ደስላ ከንጉሱ በማርገዟ በቅናት ጦፈዋል። እቴጌጣይቱ በወቅቱ ይህን ሁሉ ዝርዝር ቢያውቁም፣ አንዳች ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር አልነበራቸውም። ደስላ ማርገዟንለንጉሱ ከመንገሯ በፊትም አጤ ምኒልክ ወደ ሰሜን ዘመቱ። ከዘመቻ ሲመለሱ ደስላ ቤመንግስት ውስጥ አልነበረችም።… ርግጥ ነው፣ ደስላ ከቤተመንግስት ከተባረረች በሁዋላ አጤ ምኒልክን ፍለጋ ወደ ሰሜን ተጉዛ ነበር። በጉዞዋ ላይግን ወለደች። ህፃኗ የንጉሱ መሆኗን መናገር አደጋ ይኖረዋል ብላ ሰጋች። የጣይቱ ሰዎች ይህን ከሰሙ ከነልጇእንዳያስገድሏት መፍራቷ አልቀረም። ስለሆነም፣ ለራሷም ሆነ ለልጇ ህይወት ስትል ንጉሱን በአካል እስክታገኝ ምስጢሯንበሆዷ መያዝ መረጠች። የምትጠጋበት ወገን ስላልነበራትም እንጀራ ጋጋሪ ሆና ማገልገል እጣ ክፍሏ ለመሆን በቃ።እንዳለመችው ግን አልሆነም። ታመመችና ህይወቷ አለፈ።እቴጌ ጣይቱ ለአሽከራቸው ትእዛዝ ሰጡ፣“ሰውነቷን ታጥባ ንፁህ ልብስ እንድትለብስ አድርጉ።”ደጃዝማችንትን እያለመ ረጅም መንገድ የተጓዘው ወታደር ታሪክ ግን ከዚያ በሁዋላ ከምድረገፅ ጠፋ። ‘እኩያህንፈልገህ አግባ’ ከሚል ምክር ጋር ለኑሮ የሚሆን ድጎማ ተሰጥቶት ተሰናብቶ ሊሆን ይችላል።በዚያው ሰሞን አጤ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ እንደተለመደው እያወጉ ሳለ፣“ያቺ ይወዷት የነበረች ገረድ ትዝ ትሎታለች?” ሲሉ ይጠይቃሉ።“የትኛዋ?”“ወደ ሰሜን በዘመቱ ጊዜ እዚህ ትተዋት የሄዱት። ከዘመቻ ሲመለሱ እንኳ ‘የት ሄደች?’ ብለው ጠይቀው ነበር።ልናገኛት ስላልቻልን ግን ልናመጣልዎ አልቻልንም”“አስታውሳለሁ። የወሎዋ ልጅ አይደለችም? ተገኘች እንዴ?”“የርስዎን ሴት ልጅ በወለደች በሰባት አመቷ ሞታለች።”አጤ ምኒልክ ክፉኛ አዘኑ። ልባቸው ሳይሰበር አልቀረም። መረር ባለ አነጋገርም ለእቴጌ ጣይቱ ትእዛዝ ሰጡ፣“ያለፈው አልፎአል። ስለ እግዚአብሄር ብለሽ ልጄን ፈልጊልኝ?”“ንጉሰ ነገስት ሆይ! ደስ ይበልዎ! ልጅዎ ተገኝታለች”እቴጌ ጣይቱ እልፍኙን ለቀው ወጡ። ሲመለሱም ስምንት ተመሳሳይ ልብስ የለበሱ፣ በተመሳሳይ እድሜ ላይየሚገኙ ኮረዶችን አስከትለው ገቡ። አጤ ምኒልክ ድራማው ገባቸው። ከስምንቱ መካከል አንዷ ከዚያች በጣምከሚያፈቅሯት የወሎ ኦሮሞ ወለዷት ልጃቸው ናት ማለት ነው። አጤ ምኒልክ ከዙፋናቸው ተነስተው እንደ እግር ኳስተጫዋቾች ቡድን በተርታ የተደረደሩትን ኮረዶች አንድ ባንድ ያስተውላቸው ጀመር። እየተጠጉ መረመሯቸው። እናምጥቂት እንኳ ሳያመነቱ፣ ሸዋረጋ ምኒልክን ከሴቶቹ መሃል ለይተው እጇን ያዟት፣“ልጄ ይህቺ ናት!” ሲሉም ጮኸው ተናገሩ። አያይዘውም ጨመሩበት፣ “…ጥርሶቿና ፈገግታዋ ቁርጥ የእናቷ ነው!...” (ሸዋረጋ ምኒልክ ለወሎው ራስ ሚካኤል ተድራ ጥር 25፣ 1888 ወረሂመኑ ተንታ ውስጥ ልጅ እያሱ ሚካኤልን ወለደች። አጤ ምኒልክም ለሚያፈቅሯት ሴት የልጅ ልጅ የንጉሰነገስትነት ስልጣናቸውን አውርሰው አረፉ…)


Type:Social
👁 :1
አንዲት: አህያ፡ ርኀራኄን፡ አስተማረች
Catagory:Tell story
Author:
Posted Date:07/29/2024
Posted By:utopia online

ሁለት፡ ልጆች፡ በመንገድ፡ ሊያልፉ፡ አንዲት፡ እንቁራሪት፡ አግ ኝተው: ሊገድሏት፡ ዐስቡና፡ ድንጋይ፡ እየወረወሩባት፡ ተከታተ ሏት፡፡ በዚያውም፡ መንገድ፡ አንዲት አህያ፡ ስታልፍ፡ እንቁራሪቷ፡ ላይ፡ በእግርዋ፡ _ ልትቆምባት፡ ስትል፡ አየቻትና፡ እንዳትረግጣት፡ እርምጃዋን፡ በቶሎ፡ አቃንታ፡ በጐን፡ ሳትነካት፡ አለፈች:: ከሁለቱ፡ ልጆች፡ አንደኛው፡ ወዳጁን፡ አለው፡፡ ይህችን: አህያ፡ ተመለከትህት፡ ወይ? እንቁራሪቷን፡ እንዳትረግጣት፡ አዝና፡ መንገ ዷን፡ አሳብራ፡ አለፈች፤ እኛስ፡ የዚችን፡ አህያ፡ ያህል፡ ርኀራኄ፡ ሳይ ኖረን ቀርቶ፡ ነውን፡ ይህችን፡ እንቁራሪት፡ ለመግደል፡ ዐስበን፡ እን ዲህ፡ የምናሳድዳት፤ አይሆንም፡ ተው፡ ይቅርብን፡ ብሎ ወዳጁን: መልካም፡ ምክር፡ መክሮ፡ እንቁራሪቷን፡ በሰላም፡ ትተዋት፡ ተመለሱ፡፡ ******************************************************************************************* እኔና ጨረቃ እኔና ጨረቃ ተጓድነን ወጥተን ፣ ልንደምቅበት አደባባዩን ቀን በቀን ሽተን፣ ተመለስን፤- እነፀሓይን አድንቀን ባይሆንልን ጨለማውን እየተመኘን፡፡ ታማኝነት ' ከሁሉ ' የበለጠ ፡ ነገር ፡ ነው ። የንጉሥ ' ግምጃ ፡ ቤት ፡ ሆኖ ፡ የሚሠራ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ነበር ። እሱም ፡ የንጉሡን ፡ ገንዘብ ፡ እየሰረቀ ፡ በጥቂት ፡ ጊዜ ፡ ውስጥ ፡ ብዙ ፡ ሀብት ' ሰብስቦ ፡ ከበረ ። ኋላም ፡ ከንጉሡ ፡ ዘንድ ፡ ቀርቦ ፡ ከእንግዲህ ወዲያ ፡ እየነገድሁ ፡ ለመኖር ፡ ዐስቤያለሁና ፡ ግርማዊነትዎ፡ ፈቅዶልኝ ቢያሰናብተኝ ፡ እወድ ፡ ነበር ፡ ብሎ ፡ ለመነው ። ንጉሡም ፡ መልሱን ፡ በኋላ ' እሰጥሃለሁ ፡ አለውና ፡ አሰናበተው ። እሱም ፡ ከወጣ በኋላ ፡ የእሱ ፡ ተቈጣጣሪ ፡ ሆኖ ፡ የሚሠራውን ፡ ሰው ፡ አስጠርቶ ' ይህ ' ግምጃ' ቤት ፡ ሥራውን ' በትክክል ' ይሠራል ፡ ወይ ፡ ብሎ ' ጠየቀው ። ተቈ ጣጣሪውም ፡ የጐደለውን ፡ ገንዘብ ' ሁሉ ' በመዝገቡ ፡ አመልክቶ ' የሰ ረቀውን ' የገንዘብ ፡ ልክ ' ለንጉሡ ፡ አስረዳው " ንጉሡ ፡ ከዚህ፡ በኋላ፡ ግምጃ ' ቤቱን አስጠርቶ፡ እንዲህ' አለው። አንድ ፡ ሰው ፡ ከዕለታት ፡ አንድ ቀን ' ከገበታው ፡ ላይ ፡ አንድ ' ጠር ሙስ ፡ ወተት ' ▪ አስቀምጦ ፡ ሳይወትፈው ፡ ረስቶ፡ ትቶት ሄደ ። አንድ ' እባብ ' በጠርሙሱ ፡ አፍ ፡ ገብቶ ፡ ወተቱን ፡ ሁሉ ፡ ጭልጥ ፡ አድ ርጎ ፡ ጠጣው ። ከጠጣውም ፡ በኋላ ፡ ተመልሶ ፡ በዚያው ፡ በጠርሙሱ ፡ አፍ ፡ ሊወጣ ' ቢሞክር ፡ ሰውነቱ ፡ በጣም ፡ ደነደነና ፡ የጠርሙሱ'አፍ' አላስወጣህ ' አለው ። ምንም ' ቢታገል ' ለመውጣት ' የማይቻል ' ሆነበት " እንግዴህ ፡ አንዳንተ' ዐሳብ ' ይህ ' እባብ ፡ ከጠርሙሱ ' ውስጥ ' ለመውጣት እንዲችል ' ምን ፡ ማድረግ ፡ ይገባዋል'ይመስልሃል፡ብሎ፡ ጠየቀው ። የጠጣውን ' ወተት ፡ ሁሉ ፡ መመለስ ' ያሻዋል ፤ ይህን ' ያደ ረገ ' እንደ ' ሆነ ' ሰውነቱ ፡ እንደ ፡ ቀድሞው ፡ ተመልሶ ፡ ይቀጥንና ' የጠርሙሱ ፡ እፍ ፡ ያስወጣዋል ፤ አለዚያ ፡ ግን ' ለመውጣት ' አይች ልም ፡ ብሎ ፡ ግምጃ ፡ ቤቱ ' መለሰለት ። ንጉሡም ፡ ያንተም ፡ ነገር ፡ እንደዚሁ ' ያለ ' ነው ' ብሎ ' በምሳሌ ፡ አስረዳው " አደራ ' በተረከበው'ሥራ፡ላይ፡ለመንግሥቱና ለንጉሡ ፡ ታማኝ ሆኖ ' መገኘት ፡ ለሰው ፡ ከቀረው ፡ ሙያ ፡ ሁሉ ፡ የበለጠ ' ቁም ፡ ነገር ፡ ነው ። *******************************************************************************************************


Type:Social
👁 :
አይ መርካቶ
Catagory:Phoeme
Author:
Posted Date:07/27/2024
Posted By:utopia online

አይ መርካቶ አገር ከየጐራው ወጥቶ አንቺን ብሎ ነቅሎ መጥቶ ግሣንጉሡን ጓዙን ሞልቶ ኁልቈ መሣፍርትሽ ፈልቶ ባንቺ ባዝኖ ተንከራትቶ እንደባዘቶ ተባዝቶ ተንጠራውዞ ዋትቶ ዋትቶ አይ መርካቶ የምድር ዓለም የእንጀራ እናት ላንዱ ርካሽ ለሌላ እሳት ላንዱ ፍትሃት ላንዱ ምትሃት ላንዱ ሲሳይ ላንዱ ፍርሃት ላንዱ ተስፋ ላንዱ ሥጋት የግርግር የሆይታ ቋት አይ መርካቶ፥ ያንዱን ወስዶ ላንድ ስጥቶ ያንዱን ገፍፎ ላንዱ ኣብልቶ አንዱን ነስቶ ላንዱ አድልቶ ስንቱን ፈርቶ ስንቱን ሸሽቶ ባፈ-ጮሌ ተሸልቶ አይ መርካቶ፥ ቢያዋጣ ወይ ባያዋጣ ከስንቱ ተንጣጥቶ ጣጣ ተነታርኮ ተገዛግዞ ተብለጥልጦ ተበዛብዞ መርካቶ ያገር ድግሱ የገጠር ስንቅ አግበስብሱ ለከተሜው ለአባ ከርሱ በትሬንታው በአውቶቡሱ በቁሳቁስ ግሣንጉሱ ለቱጃር የጥጋብ ቅርሱ ለኔ ብጤም የቀን ጉርሱ አባ መስጠት እጦት ቢሱ አይ መርካቶ፥ ተሻምቶ ተገበያይቶ ወይ ተፈራርሶ ተጣልቶ በአንካ ስላንቲያ ተማትቶ አንዳንዴም ተፈነካከቶ ወይ ተመራርቆ ተስማምቶ አይ መርካቶ የኤስፔራንቶ የቋንቋ አገር ያ ሲነገር ያ ሲሰበር የስንቱ ልሣን ሲቀመር ያንዱን ሲያከር ያንዱን ሲያቀር ያንዱን ሲያውስ ያንዱን ሲያስቀር ያ ሲደቀል ያ ሲፈጠር የልሣን ሽማች ለብቻ ከዕቃው ጭምር በስልቻ ሲመዠርጥ እንደግቻ ቶሎ በል ቶሎ በል ብቻ፥ ዝግ በሉ እማይባልበት መርካቶ የአንደበት ፍላት ግርግር አሚባልባት ክርክር እሚሞቅባት ወዝ እሚንጠፈጠፍባት ሽቀጥ እሚታመቅባት ደላላ የሚያውጅባት ቸርቻሪ እሚተምምባት ሌባ ላብክን የሚያልብባት አይ መርካቶ* መርካቶ የገበያ ጎራ ላንዱ ምድር ላንዱ ጣራ ያ ሲዘረፍ ያ ሲደራ ያ ሲወስን ያ ሲፈራ ያ ሲሽሽግ ያ ሲያወራ የንግድን ጠፍ ወይ የአዝመራ የነጋዴን ምጥ መከራ፥ የከበረ እንደመረዋ+ ረብጣ አፍኖት ሲያስገመግም የከሰረ እንደ ፈላስፋ፥ በቁም ቅዠት ሲያልጐመጉም የኔ ብጤም ጠብሻን መቶት፥ በየጥሻው ሲያስስመልም ቸርቻሪ ዝርዝሩን ቋጥሮ፥ ቅንጣቢውን ሲቃርም የወር ሸማች ስንቁን ጭኖ፥ ሲመርቅና ሲረግም ማጅራት መቺ ከጀርባው፥ ጥሻውን ዘሎ ሲያዘግም ከዚህ በርሮ እዚያ ስብሮ፥ ያዝ ሲባል ሲሸሽ ሲጣጣር ካማኑኤል እራጉኤል ሾልኮ ዶሮ ማነቂያ ዳር ከመስጊድ እስከበረንዳ፥ ከአራተኛ እስከነፍስ ይማር የኡኡታው የጡሩምባው፥ የጩኸቱ የፊሽካው ሣግ የሰው የመኪና የከብት፥ የፍግ የቁሳቁስ ትንፋግ ሲገፋተር ሲመዣረጥ፥ ላቦት ለላቦት ሲላላግ ትንፋሽ ለትንፋሽ ሲማማግ አባ ሽብሩ መርካቶ፥ ያለውን በገፍ አጣጥቶ የሌለውን ከሌስበት፥ አስጐልጉሎ አስወጥቶ ስንቱን ከዳር ዳር አዛምቶ በግድም በውድ አስማምቶ አገርን ካገር አካትቶ ሁሉን አቀፍ ባይ መርካቶ ያቻችለዋል አሻምቶ፥ አይ መርካቶ ፲፱፻፷፭ - መርካቶ by Kibure Getami Tsgegaye G/Medhine


Type:Social

Page 96 of 99