Entertailment Page

Entertainment






👁 :
2ኛው ዙር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ፓሪስ ገባ
Catagory:News
Author:
Posted Date:07/31/2024
Posted By:utopia online

በተለያየ ርቀት ለወርቅ ሜዳሊያ የሚጠበቁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ያካተተው ሁለተኛው ዙር የኦሊምፒክ ልዑክ ፈረንሳይ ፓሪስ ገባ፡፡ ትናንት ምሽት ከአዲስ አበባ የተነሳው ልዑኩ የአጭር፣ መካከለኛና ረዥም ርቀት ተወዳዳሪዎችን ያካተተ ነው፡፡ በልዑኩ ከተካተቱ አትሌቶች መካከልም÷ የ5 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ጉዳፍ ፀጋይን ጨምሮ ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ሐጎስ ገ/ሕይወት፣ ሰለሞን ባረጋ እና ፅጌ ዱጉማ ይገኙበታል፡፡ በዚህም በወንዶች 10 ሺህ ሜትር፣ 1 ሺህ 500 ሜትር እንዲሁም በሴት 800 ሜትር እና 5 ሺህ ሜትር የሚወዳደሩ አትሌቶች ፓሪስ መግባታቸውን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡ ልዑኩ ቻርልስ ደጎል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ማህሌት ኃይሉ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እና በፈረንሳይ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያን አቀባበል አድርገውለታል፡፡ በጉጉት የሚጠበቀውና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለአሸናፊነት ቅድመ ግምት ያገኙበት የ20 ኪሎ ሜትር የርምጃ ውድድርም በአትሌት ምስጋና ዋቁማ ተሳታፊነት የፊታችን ሐሙስ ይካሄዳል፡፡ እንዲሁም ዓርብ የ800 ሴቶች፣ 5 ሺህ ሴቶች፣ 1 ሺህ 500 ሜትር ወንዶች ማጣሪያዎች ሲካሄዱ÷ በዕለቱ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር እንደሚካሄድ የወጣው መርሐ-ግብር አመላክቷል፡፡


Type:News
👁 :
ድሚትሪ ሜድቬዴቭ በጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለፁ
Catagory:News
Author:
Posted Date:07/31/2024
Posted By:utopia online

የዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ሊቀመንበር ድሚትሪ ሜድቬዴቭ በጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል። ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ሰዎች መሞታቸውን በመስማቴ ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶኛል ብለዋል። ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን የተመኙ ሲሆን÷ ለተጎዱትም ቶሎ እንዲያገግሙ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።


Type:News
👁 :
87 በመቶ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና አላላፉም ተባለ
Catagory:News
Author:
Posted Date:07/31/2024
Posted By:utopia online

በመቶ የሚሆኑት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የዘንድሮውን የመውጫ ፈተና ማለፍ አለመቻላቸውን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡ እንዲሁም 22 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ነው የገለጹት፡፡ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል ማሳለፍ የቻሉት 13 በመቶ ብቻ ነው ማለታቸውን የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን መረጃ አመላክቷል፡፡ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ ማሳለፋቸውን ገልጸዋል፡፡


Type:News
👁 :
በተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የተጣለው የባንክ የውጭ ምንዛሪ ገደብ ተሻረ
Catagory:News
Author:
Posted Date:07/31/2024
Posted By:utopia online

ሙሉ በሙሉ በነዳጅ የሚሰሩ በታሪፍ መፅሐፉ አንቀፅ 87.03 የሚመደቡ ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ የቤት አውቶሞቢል እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው እገዳ እንደተጠበቀ ሆኖ በተቀሩት ዕቃዎች ላይ የተጣለው የውጭ ምንዛሪ ገደብ ውሳኔ ከነማሻሻያው መሻሩ ተገለፀ፡፡ መንግስት በቁጥር ክሂገ 1/7/252 በቀን 04/02/2015 በተላለፈ ውሳኔ እና በቁጥር ታፖመ/ፖ/29/16 በቀን 28/6/2016 በተሻሻለው በተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የባንክ የውጭ ምንዛሪ ገደብ እንዲጣል ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ስለሆነም ሙሉ በሙሉ በነዳጅ የሚሰሩ በታሪፍ መፅሐፉ አንቀፅ 87.03 የሚመደቡ ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ የቤት አውቶሞቢል እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው እገዳ እንደተጠበቀ ሆኖ በተቀሩት ዕቃዎች ላይ የተጣለው የውጭ ምንዛሪ ገደብ ውሳኔ ከነማሻሻያው ከሐምሌ 21 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ የተሻረ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡


Type:Social
👁 :
እስራኤል በ9 የሊባኖስ ከተሞች ላይ ከበድ ያለ ጥቃት መፈፀሟ ተገለፀ
Catagory:News
Author:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በሚገኙ ዘጠኝ ከተሞች ላይ ከበድ ያለ ጥቃት መፈፀሟ ተገለፀ፡፡ እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በሚገኙት ሁዎላ፣ ማርካቢ፣ አይታ አል ሻብ፣ ኪሃም፣ ሻኸን፣ ያሩን፣ ማይስ አል ጀበል፣ ኬፈርኬላ እና ቦር አል ሻማሊ በተባሉ ከተሞች ነው መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሯ የተገለፀው። ጥቃቱ ሂዝቦላህን ለማዳከም ያለመ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የእስራኤልን መጠነ ሰፊ ጥቃት ተከትሎ በአካባቢው ያለው ውጥረት የበለጠ መባባሱ ተገልጿል፡፡ ጥቃቱ ባለፈው ቅዳሜ በእስራኤል ጎላን ተራሮች ላይ ከሂዝቦላህ ተተኩሷል በተባለ የሚሳኤል ጥቃት 12 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የተወሰደ የአፀፋ ምላሽ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ እስራኤል በጎላን ተራሮች በምትገኘው የማይዳል ሻምስ ከተማ ላይ የተፈፀመው የሚሳኤል ጥቃት ከሂዝቦላህ የተተኮሰ መሆኑን አስታውቃለች። ሂዝቦላህ በበኩሉ ጥቃቱን እንዳልፈፀመ ገልፆ፤ በጉዳዩ ላይ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቋል፡፡ ጥቃቱን ተከትሎ የሊባኖስ መንግስት ባወጣው መግለጫ÷ ንፁሃንን የቀጠፈውን የማይዳል ሻምስ ከተማ ጥቃት በማውገዝ በሂዝቦላህ እና በእስራኤል መካከል የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል። ሬውተርስን ጠቅሶ አረብ ኒውስ እንደዘገበው÷ ሂዝቦላህ ከምስራቅ እና ደቡባዊ ሊባኖስ ከሚገኙ ቁልፍ ወታደራዊ ቦታዎች ለቆ ቢወጣም ቡድኑ በእስራኤል ላይ ጥቃት ለመፈፀም አሁንም በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ በቡደኑ እና በእስራኤል መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በቀጠናው ከባድ ውጥረት መፈጠሩ የተገለፀ ሲሆን፤ ፈረንሳይ እና ኖርዌይ ዜጎቻቸው ወደ እስራኤልና ሊባኖስ እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡


Type:Social
👁 :
እስራኤል በጎላን ተራራ ሂዝቦላ ያደረሰባትን ጥቃት ተከትሎ ሊባኖስን በቦንብ ደበደበች
Catagory:News
Author:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

እስራኤል በጎላን ተራራ ሂዝቦላ አድርሶብኛል ያለችውን ጥቃት ተከትሎ ሊባኖስን በቦንብ መደብደቧ ተነግሯል፡፡ የእስራኤል ጦር በማእከላዊ ዴር ኤል ባላ ውስጥ ለመስክ ሆስፒታል እና ለመጠለያነት በሚያገለግል ትምህርት ቤት ላይ ጥቃት በመሰንዘር 15 ህጻናትን ጨምሮ 30 ሰዎችን ለህልፈት ዳርጓል ነው የተባለው። ሂዝቦላህ በእስራኤል በተያዘው ጎላን ተራራ በሚገኘው ማጅዳል ሻምስ ከተማ ሮኬት በመተኮስ 12 የድሩዝ ማህበረሰብ ወጣቶችን መግደሉ ተመላክቷል፡፡ ጥቃቱን ተከትሎም የእስራኤል ጦር በደቡብ እና ምስራቅ ሊባኖስ የሚገኙ መንደሮችን እና ከተሞችን በቦምብ ደብድቧል። እስራኤል ለተፈፀመባት ጥቃት ሂዝቦላን ተጠያቂ ታድርግ እንጂ የሊባኖስ ቡድን ለሮኬት ጥቃቱ ኃላፊነት አለመውሰዱን አልጀዚራ ዘግቧል።


Type:Social
👁 :
ቻይና ሙቀት የሚያመርት 4ኛ ትውልድ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ የማስፋፊያ ሥራ ጀመረች
Catagory:News
Author:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

ቻይና በዓለም የመጀመሪያ የተባለውን ከፍተኛ ሙቀት አምራች አራተኛ ትውልድ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የማስፋፊያ ሥራ ጀምራለች። የማስፋፊያው ሥራ በምስራቅ ቻይና ሻንዶንግ ግዛት በትናንትናው እለት መጀመሩም ተመላክቷል፡፡ ቻይና ሙሉ በሙሉ ነፃ የሆነና የአዕምሮአዊ ንብረት መብት ባለቤት የሆነችበት ፕሮጀክት በሮንግቼንግ ግዛት በዌይሃይ ከተማ ውስጥ ይገኛል። ፕሮጀክቱ በቻይና ሁዋንግ ግሩፕ፣ በስንጉዋ ዩኒቨርሲቲ እና በቻይና ብሔራዊ ኒውክሌር ኮርፖሬሽን በጋራ የለማ መሆኑ ተመላክቷል። በዓለም የመጀመሪያው የሆነውና አራተኛው ትውልድ በመባል የሚታወቀው ይህ የኒውክሌር ጣቢያ ባለፈው ታህሳስ ወር ወደ ንግድ ስራ መግባቱ ተገልጿል። የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ የማስፋፊያ ምዕራፍ ሌላ በሀገር ውስጥ የበለጸገ በውሃ ሃይል የሚሰራ ሶስተኛ ትውልድ ሁዋሎንግ ዋን የተሰኘውን ማመንጫ በጋዝ ማቀዝቀዝ ስርዓት ከሚሰራው ጋር በማገኛኘት ማሰራት መሆኑን የኩባንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ዣንግ አይጁን ተናግረዋል። ይህ ማስፋፊያ የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነት መብት ያላቸው የሁዋሎንግ ዋን ሁለት ክፍሎችን ያካተተ ሲሆን÷ ማመንጫዎቹ እያንዳንዳቸው 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ኪሎ ዋት አቅም እንዳላቸው ዣንግ ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በዓመት 20 ቢሊየን ኪሎ ዋት ሰዓት በማመንጨት የሙቀት አቅርቦቱን በ20 ሚሊየን ካሬ ሜትር እንደሚያሳድግና 600 ሺህ ነዋሪዎችንም ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አክለዋል፡፡ ወደፊት የተያዘው የማስፋፊያ ዕቅድም እያንዳንዳቸው ከ1 ሚሊየን ኪሎ ዋት በላይ አቅም ያላቸው በውሀ ግፊት የሚሰሩ አራት ተጨማሪ ማመንጫዎችን እንደሚጨምር መናገራቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።


Type:Technology
👁 :3
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ
Catagory:News
Author:
Posted Date:07/30/2024
Posted By:utopia online

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመጪው ረቡዕ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል፡፡ በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 58 ( 4) እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራርና የአባላት ሥነ- ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 15 ( 1 ና 2) መሰረት ምክር ቤቱ በዕረፍት ላይ እያለ የምክር ቤቱን ውሳኔ የሚሹ አስቸኳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ በዚህ መሰረትም ለረቡዕ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡ ስለሆነም የ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በዕለቱ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ ሪፖርት በማድረግ በአስቸኳይ ስብሰባው እንዲገኙ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡


Type:News

Page 95 of 99