Entertailment Page

Entertainment






👁 :
ኢትዮጵያ አሸባሪ ቡድኖች ላይ የተገኘውን ውጤት አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን እንደማትታገስ አስታወቀች
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/29/2024
Posted By:utopia online

አሸባሪ ቡድኖች ላይ የተገኘውን ውጤት አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን ኢትዮጵያ እንደማትታገስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወቅታዊ ቀጣናዊ ጉዳይ ላይ ማምሻውን በአወጣው መግለጫ÷ ኢትዮጵያ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ከሶማሊያ ሕዝብ እና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር በመሆን በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን ለመከላከል አሁንም ቁርጠኛ አቋም አላት ብሏል፡፡ ሚኒስቴሩ ያወጣው መግለጫው ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል፡- በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የተሰጠ መግለጫ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) በቀጣይ የሚኖረው አዲስ የሰላም ተልዕኮ አወቃቀር ሁኔታ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ላይ አዲስ ስጋት ይዞ መምጣቱ ኢትዮጵያን የሚያሳስብ ሆኗል፡፡ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለዚሁ አዲስ ሽግግር እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ቀጣናው ሊተነበይ ወደማይቻል ፈተና ውስጥ እየገባ ይገኛል፡፡ በሁኔታው ላይ ቀደም ሲል ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ውስጥ ወታደር ያዋጡ አገሮች ተደጋጋሚ ጥሪዎችና አስተያየቶች ትኩረት አልተሰጣቸውም፡፡ የመከላከያ ሠራዊታችንን መልካም ስምና ዝናን እንዲሁም መስዋዕትነት የሚያጠለሹ ተከታታይ መግለጫዎች ሲወጡ ኢትዮጵያ በዝምታ እንድታልፍ ከአንዳንድ ወገኖች በኩል ፍላጐት መኖሩ ይታያል፡፡ ሌሎች ተዋናዮች የአፍሪካ ቀንድ ክልልን ለማተራመስ እርምጃ ሲወስዱ ኢትዮጵያ በዝምታ አትመለከትም፡፡ ይህም በመሆኑ በቀጣናው የብሄራዊ ደህንነቷን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን ሁሉ በንቃት እየተከታተለች ትገኛለች፡፡ ኢትዮጵያ ለሶማሊያና ለአካባቢው ሰላምና ፀጥታ መስፈን፣ ለጋራ ዕድገት እና በክልሉ ያሉ ህዝቦች መካከል ያለውን የጠበቀ የእርስ በርስ ትስስር ይበልጥ እንዲጎለብት ያላሰለሰ ጥረት ስታደርግ ቆይታለች፡፡ ኢትዮጵያ ከሶማሊያ መንግስት ጋር ያለውን ወቅታዊ አለመግባባት ለመፍታት እንዲያስችል በተዘጋጁ የውይይት መድረኮች ላይም በንቃት ተሳትፎ አድርጋለች፡፡ በእነዚህ ንግግሮች ተጨባጭ ውጤቶችም ታይተዋል። የሶማሊያ መንግስት እነዚህን ሰላም ለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶች ከማጠናከር ይልቅ ቀጣናውን ለማተራመስ ከሚሹ የውጭ ኃይሎች ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ በሶማሊያ ለማሰማራት የታቀደውን አዲስ የሰላም ተልዕኮ የማዘጋጀት እና የመፍቀድ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት ሁሉ በቀጣናው የሚገኙና ቀደም ሲል ወታደር አዋጭ የሆኑ አገራትን ተገቢ የሆኑ ስጋቶች ሁሉ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል፡፡ ለአጭር ጊዜ ፍላጎታቸው እና ከንቱ አላማቸው ሲሉ በክልሉ ውጥረትን ለማቀጣጠል የሚሞክሩ ኃይሎች ዕኩይ ተግባራቸው የሚያስከትሏቸዉን መዘዞች መሸከም ይኖርባቸዋል፡፡ ቀደም ሲል አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አሸባሪ ቡድኖች ላይ የተገኘውን አበረታች ውጤት አደጋ ላይ የሚጥሉና የሚቀለብሱ ድርጊቶች ኢትዮጵያ አትታገስም፡፡ ኢትዮጵያ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ከሶማሊያ ህዝብ እና ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመሆን በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን ለመከላከል አሁንም ቁርጠኛ አቋም አላት፡፡ ነሐሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ጽ/ቤት አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


Type:Social
👁 :
Chinese Premier Li Qiang Begins 3-Day Visit to Russia
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/28/2024
Posted By:utopia online

Chinese Premier Li Qiang will kick off his three-day official visit to the Russian capital of Moscow on Tuesday upon the invitation of Russian Prime Minister Mikhail Mishustin. Li is expected to engage in the in-depth discussions with Mishustin regarding Chinese-Russian business cooperation and to address issues of mutual interest during his visit. The bilateral talks will run under the auspices of the 29th Regular Meeting of the Prime Ministers of China and Russia. Li will also hold a meeting with Russian President Vladimir Putin during the visit. The Chinese premier is also scheduled to visit Belarus from Thursday to Friday.


Type:Technology
👁 :
Maktub Paulo Coelho Dedicated to Nha Chica PART 10
Catagory:Fiction
Author:
Posted Date:08/28/2024
Posted By:utopia online

dawn,” the woman says. “The legend says that it was this that the builders of the church wanted to teach us: that God has a particular time for showing us His glory.” The master says: “There are two gods. The god that our professors taught us about, and the God who teaches us. The god of whom people always speak, and the God that speaks to us. The god we have learned to fear, and the God who speaks to us of compassion. There are two gods. The god who is on high, and the God who takes part in our daily lives. The god who makes demands upon us, and the God who pardons our debts. The god who threatens us with the fires of Hell, and the God who shows us the best path. There are two gods. A god who crushes us under our sins, and a God who liberates us with His love.” The sculptor, Michelangelo, was once asked how it was that he could create such beautiful works. “It's very simple,” he answered. “When I look at a block of marble, I see the sculpture inside it. All I have to do is remove what doesn't belong.” The master says: “There is a work of art each of us was destined to create. That is the central point of our life, and -no matter how we try to deceive ourselves -we know how important it is to our happiness. Usually, that work of art is covered by years of fears, guilt and indecision. But, if we decide to remove those things that do not belong, if we have no doubt as to our capability, we are capable of going forward with the mission that is our destiny. That is the only way to live with honor.” An old man who is about to die calls a young man to his side and tells him a story of heroism: in wartime, he had helped a man to survive. He provided the man with shelter, food and protection. When the man who had been saved was once again in a safe place, he decided to betray his saviour and turn him over to the enemy. “How did you escape?” the young man asked. “I didn't escape. I was the betrayer,” said the old man. “But in telling the story as if I were the hero, I can understand everything he did for me.” The master says: “We all need love. Love is a part of human nature, as much as eating, drinking and sleeping. Sometimes we find ourselves, completely alone, looking at a beautiful sunset, and we think: 'This beauty isn't important, because I have no one to share it with. ' At such times, we should ask: how often have we been asked to give love, and turned away? How many times have we been fearful of approaching someone and saying, unmistakably, that we love them? Beware of solitude. It is as much of an addiction as the most dangerous narcotic. If the sunset no longer makes sense to you, be humble, and go in search of love. Know that -as with other spiritual blessings -the more you are willing to give, the more you will receive in return.” A Spanish missionary was visiting an island when he came upon three Aztec holy men. “How do you pray?” the padre asked. “We have only one prayer,” one of the Aztecs answered. “We say, 'God, you are three and we are three. Have pity on us. '” “I'm going to teach you a prayer that God will hear,” said the missionary. And he taught them a Catholic prayer, and went on his way. Shortly before returning toSpain , he stopped again at the same island. When his ship approached the shore, the padre saw the three holy men walking across the water toward him. “Father, father,” one of them said. “Please teach us again that prayer that God listens to. We have forgotten the words.” “It's not important,” the padre answered, having witnessed the miracle. And he asked God's pardon for not having understood that He speaks all languages. Saint John of the Cross teaches us that, along our spiritual path, we should not look for visions, or believe the statements we hear from others on the same path. Our only support should be our faith, because that faith is clear, transparent and born within us. It cannot confused. A writer was conversing with a priest, and asked what it was to experience God. “I don't know,” the priest answered. “The only experience I have had so far is the experience of my faith in God.” And that is the most important. The master says: “Forgiveness is a two-way street. Each time we forgive someone, we are also pardoning ourselves. If we are tolerant of others, it is easier to accept our own mistakes. That way, without guilt or bitterness, we are able to improve our approach to life. When, out of weakness, we allow hatred, envy and intolerance to vibrate around us, we wind up being consumed by the vibrations. Peter asked Christ: 'Master, should I forgive the other person seven times?' And Christ answered: 'Not just seven, but seventy times. ' The act of forgiving cleanses the astral plane, and shows us the true light of the Divinity.” The master says: “The ancient masters were accustomed to creating “personages” to help their disciples to deal with the darker side of their personality. Many of the stories about the creation of such personages have become well-known fairy tales. The process is simple: you have only to place your anxieties, fears and disappointments within an invisible being who stands at your left side. He functions as a “villain” in your life, suggesting attitudes that you would not like to adopt -but wind up doing so. Once that personage is created, it is easier to reject his advice. It's extremely simple. And that's why it works so well.” “How can I know what is the best way to act in my life?” a disciple asked his master. The master asked that the disciple build a table. When the table was almost finished -needing only the nails driven into the top -the master approached the disciple. The disciple was driving the nails with three precise strokes. One nail, though, was more difficult, and the disciple had to hit it one more time. The fourth blow drove it too deep, and the wood was scarred. “Your hand was used to three blows of the hammer,” the master said. “When any action becomes habitual, it loses its meaning; and it may wind up causing damage. Every action is your action, and there is only one secret: never let the habit take command of your movements.” Near the city ofSoria , inSpain , there is an ancient hermitage carved into the rocks. Some years ago a man who abandoned everything to dedicate himself to contemplation lived there. The wanderer is trying to find the place one autumn afternoon, and, when he does, he is received with total cordiality. After sharing a piece of bread, the hermit asked that the wanderer go with him to a small stream nearby to collect some edible mushrooms. As they walk, a boy approaches them. “Holy man,” he says, “I have been told that, in order to achieve, we should avoid eating meat. Is that true?” “Accept with joy everything that life offers you,” the man answered. “Do not commit sins against the spirit, but do not blaspheme the earth's generosity.” The master says: “If your journey is difficult, listen to your heart. Try to be as honest as possible with yourself, and see whether you are really following your path and paying the price for your dreams. If you do this, and nevertheless your life is hard, the moment comes when it is right to complain. But do it with respect, as a child complains to a parent. But do not fail to ask for more attention and help. God is Father and Mother, and parents always want the best for their children. It may be that the learning process is being pushed too hard, and it costs nothing to request a pause, some affection. But never exaggerate. Job complained at the proper time, and his belongings were returned to him. Al Afid complained too much, and God stopped listening”. A pious man found himself suddenly deprived of all of his wealth. Knowing that God would help him no matter what, he began to pray: “Lord, please let me win the lottery,” he asked. He prayed for years and years, but was still poor. One day he died, and -since he was a very pious man, he went straight to heaven. When he arrived there, he refused to enter. He said that he had lived his entire life according to his religious teachings, and that God had never allowed him to win the lottery. “Everything You promised me was a lie,” the man said, disgusted. “I was always ready to help you win,” the Lord responded. “But, no matter how much I wanted to do so, you never bought a lottery ticket.” An aged Chinese wise man was walking through a field of snow,


Type:Social
👁 :
በብራዚል የተከሰተው ሰደድ እሳት በ30 ከተሞች ላይ ተፅዕኖ ማስከተሉ ተገለጸ
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/28/2024
Posted By:utopia online

በብራዚል ሳኦ ፖሎ ግዛት የተከሰተው ሰደድ እሳት እስከ አሁን ሁለት ሰዎችን ለህልፈት ሲዳርግ በ30 ከተሞች ላይ ደግሞ ተፅዕኖ ማስከተሉ ተገልጿል፡፡ የግዛቱ ባለስልጣናት÷ የተከሰተው ሰደድ እሳት በ30 ከተሞች ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን ገልጸው፤ ከተሞቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደረቅና ሞቃት የሆነ የአየር ጠባይ የታየባቸው መሆኑን አስታውሰዋል። በአካባቢው የተቀሰቀሰውን ሰደድ እሳት ለመከላከል ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። የግዛቱ አስተዳደር ከሚነፍሰው ኃይለኛ ነፋስ የተነሳ የሰደድ እሳት በፍጥነት ሊዛመት እንደሚችልና ይህም ዕፅዋትን በስፋት ሊያወድም ይችላል ሲል አስጠንቅቋል። በአሁኑ ጊዜ ሰደድ እሳቱ ከ11 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች ወዳሉባት ሳኦ ፖሎ ከተማ እየተዛመተ ስለመሆኑ መንግሥት ያለው ነገር አለመኖሩ ተመላክቷል። ይሁን እንጂ የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን የአንዳንድ የግዛቱ ከተሞች ሰማይ በጭስ እየተሸፈነ እንደሆነ ዘግበዋል። መንግሥት በኡሩፔስ ከተማ በሚገኝ አንድ የኢንዱስትሪ ፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩ ሁለት ሠራተኞች እሳቱን ለመከላከል ሲሞክሩ ህይወታቸው ማለፉን የገለጸ ሲሆን÷ ተጨማሪ ማብራሪያ አለመስጠቱን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡ የዓለማችን ትልቁ የሸንኮራ አገዳ ማቀነባበሪያ የሆነው ራይዘን÷ በሸንኮራ አገዳ ማሳዎች ላይ በተነሳ ቃጠሎ ምክንያት በሰርታኦዚኖ በሚገኝ አንድ ፋብሪካ የኢንዱስትሪ ስራዎች መቋረጣቸውን አስታውቋል። የሳኦ ፖሎ ግዛት አስተዳደር እሳቱን ለመቆጣተር የድንገተኛ አደጋ ኮሚቴ ያቋቋመ ሲሆን÷ ይህም ወደ 15 የሚጠጉ አውራ ጎዳናዎችን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መዝጋቱ ተነግሯል። በብራዚል የሰደድ እሳት ክስተት በአብዛኛው በነሐሴና በመስከረም ወር ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚደርስም ዘገባው አስታውሷል።


Type:Social
👁 :
አምባሳደር ዮሐንስ አብርሃም የካማላ ሀሪስ የፕሬዚዳንታዊ ሽግግር ቡድን ሀላፊ ሆነው ተመረጡ
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/28/2024
Posted By:utopia online

የትውልድ ሀረጋቸው ከኢትዮጵያ የሚመዘዘው አሜሪካዊው አምባሳደር ዮሐንስ አብርሃም የካማላ ሀሪስ የፕሬዚዳንታዊ ሽግግር ቡድን ሀላፊ ሆነው መመረጣቸው ተነገረ። ዴሞክራቶችን ወክለው በመጪው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚፎካከሩትን ካማላ ሀሪስ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የመምራት ሃለፊነት የተሰጣቸው አምባሳደር ዮሐንስ የፕሬዚዳንታዊ ሽግግር ቡድን በመምራት ልምድ ያላቸው መሆኑም ገልጸዋል። ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዮሐንስ መቀመጫውን ጃካርታ ባደረገው የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ ሲሆን÷ በቀጣይ ቀናት ስራቸውን አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ ተብሏል። አምባሳደር ዮሐንስ በአዲሱ የስራ ሀላፊነት ምክትል ፕሬዚዳንቷ ካማላ ሀሪስ በሚደረገው የምርጫ ሂደት ተፎካካሪያቸው ዶናልድ ትራምፕን ማሸነፍ ከቻሉ የአዲሷን ፕሬዝዳንት የሽግግር ቡድን በማዋቀር ከመሳተፍም በላይ ፖሊሲ ማርቀቅ ላይም ሚና ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ እንዳሉት፤ አምባሳደር ዮሐንስ አብርሃም የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት የአሜሪካ አምባሳደር ሆኖ በቆዩባቸው ሁለት አመታት የአሜሪካን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። አምባሳደር ዮሐንስ ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 2020 የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሽግግር ቡድን ዋና ሀላፊ እንደነበሩ ኤንቢሲ ኒውስ በዘገባው አስታውሷል። ዮሐንስ በባራክ ሁሴን ኦባማ አስተዳደር ዘመንም ለስምንት ዓመታት በኋይት ሃውስ ውስጥ ሙያዊ አገልግሎት ሰጥተዋል። የ42 ዓመቱ አምባሳደር ዮሐንስ አብርሐም በፖለቲካ ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በቢዝነስ አስተዳደር የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በከፍትኛ ማዕረግ ተመርቀዋል።


Type:Technology
👁 :
የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ስቬን ጎራን ኤሪክሰን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/28/2024
Posted By:utopia online

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ የነበሩት ስቬን ጎራን ኤሪክሰን በ 76 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ባጋጠማቸው የካንሰር ሕመም ምክንያት በሕይወት የመቆያ ጊዜያቸው አንድ ዓመት ብቻ እንደነበር በሐኪሞቻቸው ተነግሯቸው እንደነበር ተመላክቷል፡፡ አሰልጣኝ ስቬን ጎራን ኤሪክሰን በክለብ ደረጃ ማንቼስተር ሲቲ፣ ሌስተር ሲቲ፣ ሮማ እና ላዚዮን ጨምሮ 12 ክለቦችን ማሰልጠናቸው ይታወሳል፡፡ በአሰልጣኝነት ጊዜያቸውም 18 ዋንጫዎችን ማንሳት እንደቻሉ ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡


Type:Social
👁 :
በ2024 አጋማሽ የሩሲያ ኢኮኖሚ በ4 ነጥብ 6 በመቶ ማደጉ ተገለጸ
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/28/2024
Posted By:utopia online

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በፈረንጆቹ 2024 የመጀመሪያ አጋማሽ የሩሲያ ምጣኔ ሀብት (ጂዲፒ) በ4 ነጥብ 6 በመቶ ማደጉን አስታወቁ፡፡ ፕሬዚዳንቱ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ አስመልክቶ ባደረጉት የቪዲዮ ኮንፈረንስ ላይ “እንዳለፈው ዓመት ሁሉ የሩሲያ ምጣኔ ሀብት ከፍ ባለ ፍጥነት ማደጉን ቀጥሏል” ማለታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ የሥራ አጥ ቁጥሩም በሰኔ ወር ይፋ እንደተደረገው ከእስከ አሁኑ በተለየ ሁኔታ በ 2 ነጥብ 4 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅሰዋል፡፡


Type:Technology
👁 :
አሜሪካ ከፌስቡክ ላይ የኮቪድ-19 የተወሰኑ ይዘቶች እንዲነሱ ግፊት አድርጋ ነበር ተባለ
Catagory:News
Author:
Posted Date:08/28/2024
Posted By:utopia online

የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አሥተዳደር በ2021 የኮቪድ-19 የተወሰኑ ይዘቶች ከፌስቡክ እንዲወገዱ ለወራት በተደጋጋሚ ግፊት ማድረጉን የሜታ ኩባንያ መስራች ማርክ ዙከር በርግ አመላከቱ፡፡ ዙከር በርግ ለሀገሪቱ ምክር ቤት የፍትሕ ኮሚቴ በጻፉት ደብዳቤ÷ በባይደን አሥተዳደር ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት አስቂኝና ቀልድ አዘል መልዕክቶችን ጨምሮ አንዳንድ የኮቪድ-19 ይዘቶችን ሳንሱር ለማድረግ ግፊት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የባይደን አሥተዳደር የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች ጎጂ የሆኑና የተሳሳቱ መረጃዎችን እንዲያስወግዱ መጠየቁን ደግፎ እንደነበርም ዘ ኢንዲፐንደንት ዘግቧል፡፡ በተደጋጋሚ የተደረገውን ግፊት ተቋማቸው ለዓለም አለማሳወቁ የቆጫቸው ዙከርበርግ÷ እንዲህ ያለ ተጽዕኖ ድጋሜ ከተፈጠረ እንደማይታገሱ አስጠንቅቀዋል፡፡


Type:Technology

Page 101 of 116